@alhamdulilahealakulihal2: ◼ (ቱልት /ዉሻ ምላስ ተብሎ ይጠራል) ከሣር የሚመደብ ዕፅ መጠሪያ ስም ነው ይህ ዕፅ ለማመን የሚከብዱ ከዘመናዊው ህክምና አቅም በላይ የሆኑ 8 የበሽታ ዓይነቶችን በሚደንቅ ሁኔታ የመፈወስ አቅም ያለው ዕፅ ነው። ✅✅ በማንኛውም ቦታ የሚበቅል ቅጠሉ የውሻ ምላስ የሚመስል ሰፋፊ አገዳው ቀይ የሆነ ከሣር የሚመደብ የሳር አይነት ነው። የውሻ ምላስ የሚለውን ስያሜ በአማረኛ ቋንቋ ያገኘውም የቅጠሉ ቅርፅ የውሻ ምላስ የሚመስል ቅርፅ ስላለው ነው ይላሉ ። ቱልት/ የውሻ ምላስ ከሚፈውሳቸው የበሽታ ዓይነቶች መካከል ጥቂቶቹ፦ 1) ለቋቁቻ ወይም ለባርሌ በሽታ ይሆናል። በሽታው ብዙ ጊዜ የአንገት አካባቢን ያጠቃል ለዚህ የበሽታ ዓይነት ቅጠሉን ወቅጦ ትንሽ በእሳት ሞቅ እያደረጉ ለ7 ቀን ቢቀብት ያጠፋል። 2) ለፊት ማድያት በሽታም ለቆዳችን ከሚስማማ ቅባት ጋር ለውሶ ቢቀቡት ይፈውሳል። 3) ለቁርጥማት ህመም ፍሬውን ደቁሶ ለ1 ቀን 1የሻይ ማንኪያ ሙሉ በማር ለውሶ መውሰድ በቂ ነው። ለ10 ቀን ከምግብ በፊት ቢሆን ይመረጣል። 4) ስሩን ካኘክነው ጊንጥ የምትባለዋ የበረሐዋ ተናካሽ አውሬ ብትነክሰንም አያመንም መርዟን ያከሽፈዋል ማለት ነው። 5) ለዓይነማዝ ወይም ለማንኛውም የዓይን_ህመም ሥሩን ከፍትግ ገብስና ከምስር ገለፈት ጋር ወቅጦ በቅቤ አንጥሮ መቀባት ነው ፈፅሞ ይድናል። 6) ሆዱን_እየነፋው ለሚቸገር ሰው ለሥራይ ወይም ሌላ በሽታ ስሩን ከቀጠጥና ሥር ጋር ወቅጦ በማር ወይም በወተት አፍልቶ ማጠጣት ነው፦ መጠኑን በሚመለከት ከሁለቱም ዓይነት ውህድ 1የሻይ ማንኪያ ዱቄት በቂ ነው፡፡ 7) ለሽንት_ማጥ በሽታና የከፋ የሐሞት_ጠጠርን ለማውጣት ሥሩን በውኃ ቀቅሎ ከወተት ጋር ቀላቅሎ መጠጣት ወይም ከሰመሬታ ገብስ ጠላ ጋር ቀላቅሎ ለ፩ ቀን ፩ የውሃ ብርጭቆ መጠጣት በቂ ነው። በሽታው ዕስኪድን ድረስ መደጋገም ይቻላል፡፡ 8) ለድክመተ_ወሲብ ብቻውን ይሆናል፡፡ አጠቃቀም ስሩ ተቆርጦ እንዳይቀር በአንካሴ ወይም በማንኛውም መቆፈሪያ በጥልቀት ቆፍሮ ማውጣት ተቆፍሮ ከወጣ በኋላ ላም አርጎ ወቅጦ በተወቀጠ ኑግ ለውሶ በገብስ ጠላ ለ7 ተከታታይ ቀናት በቀን 1ጊዜ 1የውሃ ብርጭቆ መጠጣት በቂ ነው። ስሩ ከመሬት ተቆርጦ ከቀረ አይሠራም፡፡ 9) ለሪህ_በሽታ ስሩን ወቅጦ በሱፍ ውኃ በጥብጦ አጥልሎ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል በትንሽ በትንሹ እየጨመሩ በቀይ ጤፍ እንጀራ እየፈተፈቱ መብላት። 10) በሆድ ውስጥ ላለ ኪንታሮት እና በፊንጥጣ ዙሪያ ጎልቶ ላልወጣ ኪንታሮት ፍቱን መፍትሔ ነው። አጠቃቀም፦ ቅጠሉን እንደሐበሻ ጎመን በዕርጥቡ ለቅሞ በደንብ አጥቦ ልክ ዕንደጎመን ድቅቅ አርጎ ከትፎ ለአልጫ ጎመን ወጥ የሚገቡትን ግባቶች አስገብተው ከሠሩ በኋላ በጥቁር ጤፍ ዕንጀራ ከምግብ በፊት እየፈተፈቱ መብላት ነው፡፡ አወሳሰዱ እንደ ኪንታሮቱ ጥንካሬ ይለያያል። ፎሎ ሼር ላይክ እያረጋቹ
Kሪ organic 🌿☘️
Region: ET
Tuesday 02 June 2026 10:22:03 GMT
Music
Download
Comments
💯𝓴𝓲𝔂𝓪@𝔀.𝓴&𝓳𝓸.🇪🇹 :
🥰🥰🥰
2026-06-07 04:09:38
0
To see more videos from user @alhamdulilahealakulihal2, please go to the Tikwm
homepage.