@mogeshunyalew2: እስመ በእንቲአከ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ:: ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ መዝ 43:22 "ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል። መዝ 43:22 ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ:ም ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ ወረዳ; በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ የ101 ዓመት እድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል። የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል። የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝርም 1. አቶ ደምረው አበራ የ70 ዓመት 2. ከፈለኝ ልክየለው የ56ዓመት 3. ሐይሉ ንጉሴ የ70 ዓመት 4. እሸቴ ዳመና የ42 ዓመት 5. አበባየሁ ዳኜ የ42 ዓመት 6. ሰሙ አባይነህ የ70 ዓመት 7. 1 ሚሊሻ 8. አማረ በላይነህ የ80 ዓመት 9. ተሬ ደሴ የ25 ዓመት 10. ወጣት ገነነ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ 11. ሙርቴሳ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ 12. አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13. አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ በአጠቃላይ የ13 ሰዎች ህይወት አልፈዋል። በተጨማሪ በአሰኮ ወረዳ ከ280 ሰው በላይ ተፈናቅለዋል:: በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል። ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ ስለዚህ በተፈጸመው ጥቃት የተሰማነን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን የሞቱትን ወገኖቻችን (ልጆቻችን) እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን (በመንግሥተ ሰማያት ያሳርፍልን) የዘኑትን እና የተፈናቀሉትን ወገኖቻችን(ልጆቻችን) እግዚአብሔር ያጽናናልን። ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል። © የአርሲ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ጠፈር ሚዲያ(Tefer media)
Region: ET
Tuesday 02 June 2026 13:12:49 GMT
Music
Download
Comments
ሠው lesew :
2026-06-02 15:40:01
11
ጎንደሬው ነኝ :
2026-06-04 08:01:19
1
Meri Mekonene :
አቤቱ ይቅር በለን
2026-06-03 15:24:51
7
@GOD❤️ Me :
አሜን ያፅናልን 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏
2026-06-03 14:40:22
2
ad ad :
አቤቱ ጌታሆይ ማረን
2026-06-03 18:53:08
1
Maki yenatwa :
😭😭😭😭😭😭😭😭🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-03 18:02:46
1
ሣለ የአውዳቱ ገብርኤል 19 :
አቤቱ ይቅር በለን
2026-06-04 02:27:09
1
ኤቅሌስያ :
2026-06-03 18:11:43
1
Mekdi Yejiru Leji :
አቤቱ ይቅር በለን አምላኪ
2026-06-03 05:52:52
5
adoninati :
ጌታ ሆይ ዝም አትበለን ይቅር በለን
2026-06-03 20:18:56
1
አፄወቹ :
አቤቱ ይቅር በለን
2026-06-03 11:21:20
2
አምላኬ ሆይ ጤናየን ስለሰጠኸኝ ደስ አለኝ :
አምላኬ ሆይ ይቅር በለን
2026-06-03 17:59:23
1
rik :
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ🙏🙏🙏
2026-06-03 16:52:27
1
Seble Anteneh :
አቤቱ ጌታ ሆይ አንተ መሃሪ ና ይቅር ባይ ነህ ይቅር በለን😭😭😭😭😭
2026-06-03 19:30:32
1
ruhama :
ይቅር በለን
2026-06-03 13:01:43
1
🅱𝕚🅝𝖎 𝑏𝑖𝑛𝑖 :
2026-06-03 18:38:51
1
shibree (19)&21)♥️🙏⛪️ :
2026-06-03 18:14:28
1
ያቺ ቀን 🌟 :
2026-06-03 15:07:08
1
addi :
አቤቱ ይቅር በለን
2026-06-03 13:33:10
2
Ayeneyea Tadesea :
ፈጣሪሆይይቅርበለን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-03 11:10:33
2
Meaza444🦋 :
2026-06-03 11:13:00
4
chombe legesse02 :
ፍትህ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-03 15:38:17
1
To see more videos from user @mogeshunyalew2, please go to the Tikwm
homepage.