@arsu..21: ለምን እንደተገናኘን እንጂ ለምን እንደተለያየን እስካሁን አይገባኝም። ጠግቦኝ አልያም ጠግቤው አልነበረም። ያው አንዳንዴ ደሀ ሳይጠግብ ይጠግብ የለ .. ኩራት እራት ይሆንልኛል በማለት። እንደዛ ሆነና የኛም ነገር ህህ። እየተራብኩት በቃኝ አልኩ። እየተጠማኝ አንስቶ ደፋኝ (ኧረ እንደውም የጓሮ አትክልት ጥም መቁረጫ አደረገኝ)። አሁን አሁን .. እፍ እፍ ባልንበት ጊዜ በ'ወይኔ ስታስቀኑኑ' የጥምረታችንን ፍም ያራግቡልን የነበሩ .. አሁን ላይ በ'ፍቅር የታባቱ' ጎደኞቻችን ለምን ተለያያችሁ ግን?" ሲሉኝ "አጥግቤው .. አጥግቦኝ .. ሳንጠጋገብ ተለያየን" እላቸዋለሁ። እጥር ምጥን ተደርጎ የመተጣጣታችን ታሪክ ሲነገር ከዚህ አያልፍም። ሞኙ .. አፈቃቀሬን አይቶ .. 'በጣም ተፈቃሪ ነኝ' ብሎ አመነ። ሞኟ .. አፈቃቀሩን አይቼ .. 'በጣም ተፈቃሪ ነኝ' ብዬ አመንኩ። ይህ .. የሰው ልጅ በፍቅር ሰሌዳ ላይ እንዳይጠፋ አድርጎ የሚስለው የጅልነት ታሪኩ ነው .. ልቡን ከፍሎ ከሸመተው ሰው ጋር ከግዢ ኋላ የሚደረግ የ"በዚህ አያዋጣም። ዋጋ ጨምር።" ድርድር። ሸቀጥማ ሞኝ ነው .. አንዱ ስለገዛው ሁሉ የጎመዠው ይመስለዋል። አንዱ ስለከፈለበት ሌላው ሁሉ ይጫረተው ይመስለዋል። እኔና እሱ .. ሸቀጦች ነበርን። ጨምረህ ግዛኝ .. ጨምረሽ ግዢኝ ስንባባል ነው የተጣጣነው። ሳት አለኝና .. አንድ ቀን ብድግ ብዬ .. ስልኩን መመለስ ተውኩ። ሳት አለውና .. አንድ ቀን ብድግ ብሎ ባሻኝ ሰዐት መልዕክት ስልክለት ስፍስፍ ብሎ መመለስ ተወ። አንድ ቀን ብድግ ብለን ፍቅረኛሞች እንደሆንነው ሁሉ .. አንድ ቀን ብድግ ብለን የማንተዋወቅ ሰዎች ሆንን። በሰው አፍ ባለ ከረሜላ እየተቁለጨለጨና ከንፈሩን በጉምዥት እየመጠጠ ባደገ ማህበረሰብ ውስጥ .. ከ'ፍቅረኛው የተጣላን ሰው' ያህል የሚያስጎመዥ ነገር የለም። "አፉ ላይ ምን ምን ብላው ይሆን?" በሚል ሰው መከበብም "ከጣዕምሽ ወዲያ ላሳር" በሚል ሰው እንደመከበብ የሚታይበት የሞኝነት ጊዜ አለ። ያንኳኳልኝ ሁሉ ቤተኛ አለመሆኑን ለመረዳት አረፈድኩ። ያንኳኩለት ሁሉ ቤተኛ አለመሆናቸውን ለመረዳት ረፈደበት። ማርታ .. ህሊና .. ሌሊሴ .. ትንቢተ አንዳቸውም እንደኔ አይሆኑለትም። ግንደሞ እንደኔም አይተዉትም። አማን .. ዳዊት .. ምናሴ አንዳቸውም እንደሱ አይሆኑልኝም። ግንደሞ እንደሱም አይተዉኝም። እየተዋደድን መንገድ ከለየን ወራት አለፉ። በወሬ ወሬ ማግባቱን ሰማሁ። ተቃጠልኩ። በወሬ ወሬ ማግባቴን አስነገርኩት። ይቃጠል (የታባቱ)። በወሬ ወሬ ባልተቤቱ ስሟ ማህሌት እንደሆነ ሰማሁ። አይ አዳም .. እኔን "አፈቅርሻለሁ .. መለያየቱን እልቻልኩም" ማለት ዳገት .. በስም ሞክሼዬ የሆነችን ሴት ፈልጎ "በክፉም በደጉም ላልለይሽ" ብሎ መማል ደሞ ሜዳ ይሆንለት ህህ ዳገቱንማ እኔም ድኼበታለሁ .. ሜዳ ላይ መንገድ ለየን እንጂ .. እሱ 'ፍቅሬ' ያለችውን አገባት .. እኔ 'ፍቅሬ' ያለኝን ተለየሁት። እኔ ቀኔ እንጂ ሌሊቶቼ የሱ ናቸው .. እሱ ግን ቀኑንም ሌሊቱንም ሰጣት። የኔን ስም ለያዘች እኔን ላልሆነች ሴት። እልህ አፈር ይብላ .. እኔን እርሜን .. እሱን መሃላ ያበላ። አርብ ማታ ማታ ያስለመደኝን ወይን ልጠጣ 'አለን ግሮሰሪ' አንድ ጥጌን ይዤ ትክዝ ብያለሁ። በራስ እጅ ከራስ የነጠቁት ነገር እንዴት ግን ያንገበግባል? እየተብሰለሰልኩ ሳለሁ .. "ሰው አለው?" አለ አንድ ድምፅ አጠገቤ ያለውን ቦታ በጣቶቹ እያመላከተ (ጣቶቹን አውቃቸዋለሁ። ክራር ገራፊውን መች ያጣል 😏) ቀና አልኩ። አይኑን ሳይ ብርክ ብርክ የሚለኝ ነገር ተነሳብኝ ደሞ። ከሱ በኋላ ስንት አይን አየሁ .. ህህ ለካ ብርክ የሚያስይዝን አይን ነበር ሳቅ በሚያስይዝ አይን የለወጥኩት .. "አዳም" አልኩት ... ኡፍፍ ስሙ አፍ ላይ ሲጣፍጥጥጥ "ማህሌት" አለ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ (ይሄን አጠራር ሌላ ቦታና ጊዜ ላይ አውቀዋለሁ። ሚስቱም ግን ሌላ ቦታና ጊዜ ላይ ታውቀዋለች። እውነታው አንገበገበኝ። .. እሱ ለኔ አንድ 'አዳሜ' .. እኔ ግን ለርሱ የመጀመሪያ 'ማህሌቱ' ብቻ ነኝ።) "ለምን መጣህ?" አልኩት የቀለበት ጣቱ ላይ ያለውን ትኩስ የቀለበት ምልክት ገልመጥ እያደረግኩ "ፈታኋት .. አልቻልኩምምም" አለኝ .. አይኖቹን .. እንባ ያለአንቀልባ አሳዝሎ "መቼም ያቺን መከረኛ የመኪና ጎማህን መሆን አለበት" አልኩት በስላቅ ሳቅ ድባብ "ሚስቴን ነው" አለኝ። በየትኛው ጠርሙስ እንደምፈነክተው ግራ ገባኝ .. በደሙ .. ያለፈ ግፉ .. በደሙ .. የማግስት በደሌ ከተሰረየልን ብዬ .. ምክንያቱም ታውቆኛል .. ሀጥያት ልሰራ ነው። ያቺን ጠማማ መኪና እያንገጫገጭን .. ቀጥ ያለውን መንገድ ይዘን ወደትዝተኛ ሆቴላችን ተጣደፍን። እኔና እሱ ለንሰሀም ለሀጥያትም የምንቸኩል ሰዎች ነን። እግዜሩ ደሞ .. ለምህረትም ለቁጣም የሚዘገይብን አይነት 😏 አሁን የምህረት ሰሞን ላይ ነን .. ከቁጣው በፊት .. ስንቴ በአዳም ሀጥያት ልስራ? 77ቴ? 😏 ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ደር'ሃሲ ከዜሮ

𝑠𝑎𝑟𝑖 የጃንደረባው ትውልድ 🇺🇸
𝑠𝑎𝑟𝑖 የጃንደረባው ትውልድ 🇺🇸
Open In TikTok:
Region: SA
Wednesday 03 June 2026 17:37:31 GMT
35907
2137
16
375

Music

Download

Comments

lij___mekdi
Mekdi Yetewahedo Temari ✅ :
🥰🥰🥰ላይክ አድርጊኝ ስመጣ እንዳነበው አሁን ስራ ነኝ
2026-06-03 21:46:46
23
user2442736739437
አመፀኛው ሸዋ💪 :
🥰የኔ ♥️
2026-06-03 19:42:00
0
muhamedtemamebrah
አንበሳው :
ቅመም
2026-06-03 18:16:24
0
bareche89
bareche :
❤️❤️❤️❤️
2026-06-06 08:25:05
1
yo_ye_lidetaw
yo Der ዘ ልደታ :
✍️✍️✍️🤝🤝🤝🤝
2026-06-03 22:59:04
1
user4149657038611
ፍቅር ከሸዋ ልጅ :
🥰💙
2026-06-04 01:04:37
1
loove516
𝑘𝑎𝑙𝑙🫶🏻የመሲሁ ልጅ🫰 :
❤️❤️❤️
2026-06-03 19:23:12
1
yeledataw1_kk
🔥...K|K...💯 :
🥰🥰
2026-06-03 20:18:18
1
muhamedtemamebrah
አንበሳው :
🥰🥰🥰
2026-06-03 18:16:12
1
user9560076741113
💓ፍፁም➻ቃል☦️ :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-04 19:57:06
0
antsokiya3
ሳሚ :
❤️❤️❤️
2026-06-03 18:56:47
0
To see more videos from user @arsu..21, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About