@wasumohammed: "የንጹሃን እልቂት በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል" ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ዋና ፀሃፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በንፁሃን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝ ጥቃት በፅኑ አወገዙ። ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በአርሲ ዞን አሰኮ፣ ሺርካ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች ታጣቂዎች የፈጸሙትን ግድያና ማፈናቀል "ሰይጣናዊ የጥፋት ተግባር" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፤ ጥቃቱ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መፍትሄ አለማግኘቱ እጅግ የሚያሳምም መሆኑን ጠቁመዋል። ይህንን እልቂት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊቆም እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል። በተመሳሳይ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በበኩላቸው፣ የንጹሃን ክርስቲያኖች መገደል እንዲሁም የቤተ ክርስቲያንና የመኖሪያ ቤቶች መቃጠል ልብ ሰባሪ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት መሰል ጥቃቶችን የፈጸሙ አካላትን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋል አለመቻሉ አደገኛነቱን እንዳባባሰው ጠቁመው፣ ለአንዲት ነፍስ መጥፋት ተጠያቂ የሆኑ ወንጀለኞች ሊቀጡ እንደሚገባና ለዘላቂ መፍትሄም ከስሜታዊነት በራቀ መልኩ በጋራ መምከር ግድ እንደሚል አሳስበዋል። ሁለቱም መሪዎች ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን የተመኙ ሲሆን፣ ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መተዛዘን ጸሎታቸውንና ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr ==================== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 #breakingnews #foryoupage #foryou #viralvideo #tiktok
Wasu Mohammed 📌
Region: ET
Wednesday 03 June 2026 18:46:35 GMT
Music
Download
Comments
@meki :
are new
2026-06-04 10:44:49
0
abu sumeya :
በትክክል
2026-06-04 08:24:22
0
ናቲ :
ተባለ አንደ ?
2026-06-04 12:04:19
0
Jemal beke :
😭😭😭
2026-06-03 19:06:28
0
jems :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-03 21:05:03
0
BEKII chala✌🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹👌 :
😭😭😭
2026-06-03 18:54:20
0
Dastew :
😭😭😭
2026-06-03 18:51:50
0
BEKII chala✌🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹👌 :
🥰🥰🥰
2026-06-03 18:54:17
0
abo yusuf :
🥰🥰🥰
2026-06-03 18:49:52
0
Abate wagaya :
🤩🤩🤩
2026-06-05 08:30:35
0
To see more videos from user @wasumohammed, please go to the Tikwm
homepage.