@alhamdulilahealakulihal2: የብሳና ዛፍ አስገራሚ ጥቅሞች‼ ተአምረኛው ዛፍ ብሳና ከዕፀዋት ሁሉ ይለያል።የብሳና ዛፍ ሳይንሣዊ መጠሪያ ስሙ በእንግሊዘኛው (croton macrostachyus tree )ተብሎ ይጠራል። ይህ ዕፅዋት ከሌሎች ዕፀዋቶች በተለየ ሁኔታ ዕጅግ አስገራሚ ጥቅሞች አሉት።ብሳና ኢትዮጵያ ሐገራችን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኝ የዛፍ ዓይነት ነው። በባህላዊ ህክምና የተለመደና ለተለያዩ መድኃኒቶች ግብዓት በመሆንም ያገለግላል።የብሳና ቅጠሉ፣ ልጡ፣ ሥሩ፣ ፍሬውና ግንዱ ለተለያዩ ጥቅሞች ይውላል። ከዚህ በመቀጠል የብሳና ዛፍ ጥቅሞቹንና አጠቃቀሙን በዝርዝር ዕንደሚከተለው አቀርብላችኋለሁ። ለሆድ ውስጥ ሥራይ ያክማል። አጠቃቀም የብሣናውን የሥሩን ልጣጭ ልጦ በመጥረቢያ ከትክቶ አፈሩን በማጠብ ወቅጦ በንጹህ ውሃ ዘፍዝፎ ጧት ጧት ከምግብ በፊት እያጠለሉ በውሃ ብርጭቆ ከ1-- 5 ቀን መጠጣት ነው። የሣል በሽታን ያዳክማል። አጠቃቀም ቅጠሉን እየቀቀሉ ማታ በመኝታ ሰዓት እየታጠኑ መተኛት ነውከ። 1---10 ቀን ቢሆን ሣሉን ነቅሎ ይጥለዋል። ለውሻ ልክፍት በሽታ አጠቃቀም የሥሩን ቅርፊት ከመካን ዕንዶድ ሥር ጋር ወቅጦ አድርቆ ዱቄቱን ከጥቁር ጤፍ ዱቄት ቀላቅሎ ሃምሣ ሳንቲም የሚያክል እየጋገሩ በባዶ ሆድ ለ3 ቀን መብላት ለወፍ በሽታ አጠቃቀም የብሳና ቀንበጡን ከሰንሰል/ከስሚዛ ቀንበጥ ጋር ወቅጦ ዕንደሽሮ በመስራት ቅቤ ጨምሮ በባዶ ሆድ መብላት ነው። ለቋቁቻና ለችፌ አጠቃቀም ፍሬውንና ቀንበጡን ከነጭ ሽንኩርት ጋር ወቅጦ መቀባት ነው። ለማንኛውም ቁስል ልጡን አድርቆ ወቅጦ በቁስሉ ላይ መነስነስ ነው ፈፅሞ ይድናል ለምች ህመም ቅጠሉን ከነጭ ባህሕርዛፍ ጋር ቀቅሎ መታጠን ይበጃል ለኪንታሮት በሽታ አጠቃቀም ሥሩን በመጥረቢያ ላፍ ላፍ አድርጐ በትንሹ ወቅጦ እየቆሰለና ዕየደማ ለሚያስቸግር ኪንታሮት ማታ ኪንታሮቱ ላይ ደምድሞ መተኛት ሁነኛ መፍትሔ ነው ለሆድ ትላትልና ለወስፋት አጠቃቀም በውሃ በጥብጦ አሳድሮ ከምግብ በፊት አጥልሎ መጠጣት ነው። የተክሉ ጥቅም የፍሬዎቹና የሥሮቹ መረቅ ለአባለዘር በሽታ ይጠቅማል። የደቀቀው ልጥ ከኮሶ ወይም መተሬ ጋር ተቅላቅሎ ትልን ያስወጣል። ዘሮቹና ሙጫዎቹ መርዛማ ናቸው፣ ለአሣ መርዝ ይጠቀማሉ። የቅጠሎቹ ልጥ ለእከክ ይጠቀማል። ብሳና ማንኛውም የላይኛው የሰውነታችን ክፍል ቁስል የማድረቅ ትልቅ ኃይል አለው። አጠቃቀም፦ የብሳና ወፍራሙ የግንዱ ቅርፊት መፋቅ ከዛ አድርቆ እስኪልም መፍጨት: ከዛ ቁስሉ በቀን አንዴ ጨው ባለው ሞቅ ባለ ውሀ እያጠቡ የብሳናው ዶቄት በላዩ ላይ መነስነስ ያለ አንዳች ኢንፌክሽን ይድናል። ቅጠሉን ስንቆርጥ በቅጠሉ እንጨት ቁራጭ ላይ የምናገኘው ፈሳሽ ለጭርት በሽታ ፍቱን ነው፡፡ አጠቃቀሙም ጭርት የያዘን ቦታ ላይ ፈሳሹን በደንብ ማሸት ይህንን በተደጋጋሚ በማድረግ ለውጡን ማየት እንችላለን፡፡
Kሪ organic 🌿☘️
Region: ET
Thursday 04 June 2026 15:44:00 GMT
Music
Download
Comments
BLACK :
betkekel
2026-06-26 21:46:13
0
አባይ ራሻ :
🥰🥰🥰
2026-06-05 10:31:24
1
Bezawit Abera :
🙏🙏
2026-06-27 19:14:01
0
To see more videos from user @alhamdulilahealakulihal2, please go to the Tikwm
homepage.