@thamngocnga988: #66topgia

Thắm Ngọc Ngà
Thắm Ngọc Ngà
Open In TikTok:
Region: VN
Friday 05 June 2026 16:20:27 GMT
359
3
0
3

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @thamngocnga988, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

‎የስራ ስንብት ክፍያ መብት እና አሰላሉ  ከአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ምን ይላል? ‎********** ‎በአሁኑ ወቅት በሃገራችን የግል ቀጣሪ ድርጅቶች በስፋት በመኖራቸው ምክንያት ቁጥራቸው የበዛ ዜጎች በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ኑሮ የሚደግፉ ቢሆንም፣ የሥራ ዓለም ተለዋዋጭ በመሆኑ አንድ ሠራተኛ በገዛ ፈቃዱ፣ በድርጅቱ የሥራ መቀነስ፣ በዲሲፕሊን ግድፈት ወይም በጤና መታወክ ምክንያት ከሥራው ሊለይ ይችላል።  ‎ ‎በመሆኑም በዚህ ወቅት ለወደፊት ሕይወቱ መደጎሚያ የሚሆንና ላገለገለበት ዘመን የሚሰጠው
‎የስራ ስንብት ክፍያ መብት እና አሰላሉ  ከአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ምን ይላል? ‎********** ‎በአሁኑ ወቅት በሃገራችን የግል ቀጣሪ ድርጅቶች በስፋት በመኖራቸው ምክንያት ቁጥራቸው የበዛ ዜጎች በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ኑሮ የሚደግፉ ቢሆንም፣ የሥራ ዓለም ተለዋዋጭ በመሆኑ አንድ ሠራተኛ በገዛ ፈቃዱ፣ በድርጅቱ የሥራ መቀነስ፣ በዲሲፕሊን ግድፈት ወይም በጤና መታወክ ምክንያት ከሥራው ሊለይ ይችላል። ‎ ‎በመሆኑም በዚህ ወቅት ለወደፊት ሕይወቱ መደጎሚያ የሚሆንና ላገለገለበት ዘመን የሚሰጠው "የስንብት ክፍያ" በአግባቡ መታወቁ ወሳኝ ነው። ይህ የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ድንጋጌ የሚገዛው ከመንግሥት ሠራተኞች ውጭ በሆኑ የግል ድርጅቶችና የልማት ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞችን ብቻ ሲሆን፣ ክፍያውም በዋናነት በሠራተኛው የአገልግሎት ዘመን፣ ሥራው የተቋረጠበት ምክንያት እና ሲሰናበት በነበረው የመጨረሻ የወር ደመወዝ ላይ ተመስርቶ የሚሰላ ነው። ‎ ‎የዚህ ክፍያ ዋና ዓላማ ሠራተኛው አዲስ ሥራ እስኪያገኝ ድረስ ለሚያጋጥመው የኢኮኖሚ መናጋት እንደ ዋስትና በማገልገል፣ ለቆየበት የአገልግሎት ዘመን ተገቢውን የድካም ዋጋ በመስጠት የሽግግር ወቅት ድጋፍ እንዲሆነው ማድረግ ነው። ይህም ሠራተኛው ወደ ድንገተኛ ድህነት እንዳይገባ በመከላከል ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነቱን ለማረጋገጥ ያለመ ነው። ‎ ‎*​​​​​​​ ክፍያውን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ‎ ‎1.የሙከራ ጊዜን ማጠናቀቅ፦ ሠራተኛው የሙከራ ጊዜውን (45 የሥራ ቀናት) አጠናቆ ቋሚ መሆን አለበት። (አንቀጽ 11 እና 39) ‎ ‎2. የጡረታ መብት (ብቁ አለመሆን)፦ የስንብት ክፍያ የሚከፈለው ሠራተኛው በጡረታ ሕግ መሠረት የጡረታ አበል ለመቀበል ብቁ ካልሆነ ብቻ ነው። (አንቀጽ 39/2) ‎ ‎3. የውል መቋረጥ ምክንያቶች፦ ውሉ በሚከተሉት ምክንያቶች ሲቋረጥ ክፍያው ይፈጸማል፦ ‎ ‎* ​​​​​​​​​​​​​ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሲዘጋ። ‎* ​​​​​​​​​​​​​ በአዋጁ መሠረት የሠራተኛ ቅነሳ ሲደረግ። ‎* ​​​​​​​​​​​​​  ሠራተኛው በጤና መታወክ ምክንያት መሥራት እንደማይችል በሕክምና ሲረጋገጥ። ‎* ​​​​​​​​​​​​​አሰሪው ሕገ-ወጥ ድርጊት ፈጽሞ ሠራተኛው ውሉን ሲያቋርጥ። ‎* ​​​​​​​​​​​​​ሠራተኛው ሲሞት (ለወራሾች የሚከፈል)። (አንቀጽ 39/1 ከሀ-ረ) ‎* 5 አመት አገልግሎ​​​​​​​​​​​​​ በገዛ ፈቃድ ሥራን ሲለቁ፦ በአዋጁ መሠረት በገዛ ፈቃድ (በመልቀቂያ) ለሚለቅ ሠራተኛ የስንብት ክፍያ ይከፈላል ‎-የፕሮቪደንት ፈንድ ግን የሠራተኛው የግል ቁጠባ በመሆኑ፣ እንደ ድርጅቱ የውስጥ መመሪያ መሠረት የተጠራቀመውን ድርሻውን የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው። ‎       II. ክፍያው በአዋጁ መሠረት እንዴት ይሰላል? ‎ ‎በአዋጅ አንቀጽ 40 መሠረት ስሌቱ የሚከተለውን ቀመር ይከተላል፦ ‎ ‎* ​​​​​​​​​​​​​ ለመጀመሪያው 1 ዓመት፦ የ30 ቀን አማካይ የዕለት ደሞዝ። ‎* ​​​​​​​​​​​​​ከ1 ዓመት በላይ ለሠራ፦ ለመጀመሪያው ዓመት ከተሰላው ላይ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ዓመት የ30 ቀኑ ሲሶ (1/3ኛ ወይም የ10 ቀን ደሞዝ) እየታሰበ ይታከላል። ‎ ‎* ​​​​​​​​​​​​​ከ1 ዓመት በታች ለሠራ፦ ከአገልግሎቱ ጋር ተመጣጣኝ በሆነ ስሌት ይታሰባል። ‎* ​​​​​​​​​​​​​አጠቃላይ ክፍያው ከሠራተኛው የ12 ወር (የአንድ ዓመት) ደሞዝ መብለጥ የለበትም። ‎          ‎

About