@debrebirhan2222: በኮምቦልቻ ከተማ 145 ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታምርት ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ዛሬ ይካሄዳል። በዚህ መድረክ ላይ ለመታደም ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል። ክልላዊ የንቅናቄ ማጠቃለያ መርሐ ግብሩ "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ መልዕክት ነው የሚካሄደው። በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን አቅርበው የሚያስተዋውቁበት እና የሚሸጡበት ኤክስፖም ተዘጋጅቷል። ንቅናቄው አምራቾች ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ፤ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ እና ችግሮቻቸውን ተቀርፈውላቸው የተሻለ እንዲያመርቱ የሚያስችል ነው። በኤክስፖው 145 ኢንዱስትሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል። ርእሰ መሥተዳድሩ በቆይታቸው "ኢትዮጵያ ታምርት" ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ኤክስፖን ይከፍታሉ፤ ከባለሀብቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋርም ይወያያሉ።

ደብረ ብርሃን Official
ደብረ ብርሃን Official
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 07 June 2026 06:30:33 GMT
2403
27
0
1

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @debrebirhan2222, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About