@amanenyew: በነጻ ድራፍት የታደለበት አዘጋጆች የከሰሩበት ኮንሰርት በግዳጅ የተካሄደው፥ የከሰረው ኮንሰርት‼️ ቅዳሜ ግንቦት 29/2018 በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው አነጋጋሪው የአርሴናል ድል ማክበሪያ ኮንሰርት ከእቅዱ እስከ ፍፃሜው ምን ይመስል ነበር? የተወሰኑ መረጃዎችን እነሆ፦ 🔷 ከአራት ወራት በፊት..... ተስፉ ኪሮስ የቫርዳስ ክለብ ባለቤትና ታላላቅ የሙዚቃ መድረኮችን በማዘጋጀት የሚታወቅ የኪነጥበብ ቤተሰብ ነው፤ ከአራት ወራት በፊት አርሴናል የሊጉን ዋንጫ ከወሰደ የሚካሄድ ኮንሰርት የሚል የእቅድ ሰነድ ይዞ ወደ ከተማ አስተደሩ ቢሮ ለፍቃድ አቀና፤ ለባህልና ስፖርት ሚንስቴር ደግሞ በጋራ የመስራት ጥያቄ አቀረበ፤ አርሴናል ዋንጫ ባይወስድስ ብለው ሲሞግቱት የአርሴናሉ ተስፈኛ ደጋፊ ተስፉ በቡድኑ እርግጠኛ ሆኖ አሳመናቸውና በአዲስ አበባ ስታዲየም ግዙፍ የሙዚቃ ድግስ እንዲያደረግ ፈቃድ ተሰጠው፤ ኮሚቴ አዋቅሮ ለአራት ወራት ቅድመ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆየ የተስፉ ተስፋ ተሳክቶ አርሴናል ዋንጫ ወሰደ፤ ለኮንሰርቱ ቀን ተቆረጠለት፤ ቲክቶከሮችን አስቀድሞ የማስተዋወቅ ስራው በስፋት ተካሄደ፤ ከ10 በላይ ታዋቂና ሌሎች አዳዲስ ድምፃዊያን ስራዎቻቸውን ለማቅረብ ውል ፈረሙ፤ 30ሺህ የመግቢያ ትኬትና 30ሺህ ማሊያ ተዘጋጀ፤ 11 ሚሊየን ብር የወጣባቸው የድምፅ መሳሪያ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ተገጠመ፤ ትኬት መሸጥ ተጀመረ፤ በጥቅሉ 30 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጪ ለኮንሰርቱ ፈሰሰ 🔷 ከአንድ ሳምንት በፊት... ኮንሰርቱ አንድ ሳምንት ሲቀረው አርሲ ላይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ፤ መኖሪያ ቤቶችና አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፤ ባለ ማህተቦቹም ተሰደዱ፤ ይህም ኢትዮጵያዊያንን አስቆጣ፤ በዚህ ምክንያት ኮንሰርቱ እንዲሰረዝ አልያም እንዲራዘም ከፍተኛ ዘመቻ ተከፈተ፤ ሰሚ ግን አልነበረም፤ በኮንሰርቱ ዋዜማ ድምፃዊያኑ በስታዲየም ተገኝተው ልምምድ አደረጉ፤ ብዙዎች በውሳኔያቸው ተከፉ 🔷 የኮንሰርቱ እለት ማለዳ.... አዘጋጆቹ ከለንደን የመጡ የቀድሞ የአርሴናል ተጫዋች ኢማኑኤል ኢቦዬና የአርሴናል ደጋፊ ቲቪ አቅራቢዎችን ተቀብለው አዲስ አበባን ሲያስጎበኙ ከተሳታፊ ድምፃዊያን መካከል ጥቂቶቹ በጠነከረው ህዝባዊ ግፊት ምክንያት ራሳቸውን ከኮንሰርቱ አገለሉ፤ ታደለ ሮባ፣ ሳሚ ዳንና ራሄል ጌቱ ቀደሙ፤ ዮ ማሪዮስ ተከተለ፤ አራቱ ድምፃዊያን አዘጋጆቹንና ታዳሚውን ይቅርታ ጠይቀው ስራዎቻቸውን እንደማያቀርቡና እንደማይገኙ በይፋ አሳወቁ፤ ይህንን ተከትሎ አዘጋጆቹ ለከተማ አስተደሩ እንዲሁም ለባህልና ስፖርት ሚንስቴር ኮንሰርቱ እንዲራዘም ሃሳብ አቀረቡ፤ ምክንያቶቻቸው ደግሞ የተወሰኑ ድምፃዊያን አንሳተፍም እንዳሉ፥ ቀሪዎቹም እንዲራዘም እንደጠየቁ፥ በዘመቻው ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል ትኬት እንዳልተሸጠና የገዙትም በሀዘኑ ምክንያት እንደማይገኙ በተለያዩ መንገዶች እንዳሳወቁ፥ የሚዲያና የህዝቡ ጫና እንደጨመረ በማስረዳት በመጨረሻው ሰዓትም ቢሆን ለሌላ ቀን እንዲተላለፍ ጠየቁ፤ ሆኖም ኮንሰርቱ መካሄድ እንዳለበት ከመንግስት አካላት አስገዳጅ መመሪያ ተሰጣቸው፤ መሰረዙ ለገፅታ ግንባታ ጥሩ እንዳልሆነና እኛ ተመልካች እናመጣለን አታስቡ ተባሉ፤ ኮንሰርቱን የማካሄድ ግዴታ ተጣለባቸው፤ ቀድመው አንሳተፍም ካሉት ድምፃዊያን ውጪ ያሉት አብዛኞቹ አርቲስቶችም በአካል ተገኝተው የተወሰኑት ማናጀሮቻቸውን ልከው የመግቢያ ባጅ ወሰዱ፤ ከአዘጋጆቹም ጋር ተወያዩ፤ አንዳንዶቹ የአዘጋጆቹን ጭንቀት ተረድተው ስራዎቻቸውን ለማቅረብ ሲስማሙ አንዳንዶቹ በመገኘትና ባለመገኘት መሃል ተንሳፈው ለአመሻሹ ኮንሰርት ተቀጣጥረው ተለያዩ 🔷 የኮንሰርቱ ምሽት.... የተመልካች ድርቅና ህዝባዊ እምቢተኝነት ያላስደሰተው መንግስት የኮንሰርቱን ሃላፊነት ከአዘጋጆቹ ነጥቆ መዘወር ጀመረ፤ የከተማው አስተዳደር የፓርቲውንና በተለያየ ክንፍ ያደራጃቸውን የማህበር አባሎቹን እያሰለፈና የተዘጋጀውን የአርሴናል ማሊያ እያደለ በነፃ ስታዲየም አስገባቸው፤ እነዚህ ሰዎች በነፃ ገብተው አዘጋጆቹን ለኪሳራ ከመዳረጋቸው በተጨማሪ ነፃ የመጠጥ ኩፖን እየተሰጣቸው በድራፍት ቺርስ ሲባባሉ አመሹ ቀድመው እንደማይመጡ ካሳወቁ አራት አርቲስቶች በተጨማሪ ቀን ላይ የመግቢያ ባጅ የወሰዱ ሌሎች አራት ድምፃዊያን ደግሞ ደብዛቸው ጠፋ፤ ልጅ ሚካኤል፣ ሮቤል ሚደቅሳ፣ አማኑኤል የማነና ሚክዋን ኮንሰርቱ ላይ አልመጡም፤ በጥቅሉ ከአስር ተጠባቂ ድምፃዊያን መካከል ስምንቱ አልተገኙም፤ ከእነዚህ ውስጥ በቅርቡ አልበም ያወጣው ሚካኤል አትክልት(ሚክዋን) ለዚህ ኮንሰርት ብሎ ከአሜሪካ ሲያትል ተነስቶ አዲስ አበባ ቢመጣም መጨረሻ ላይ ሃሳብ ከቀየሩትና ከቀሩት ውስጥ ይገኝበታል እናም የኮንሰርቱ ከሰማንያ ከመቶ በላይ ቆይታ በዲጂዎች ሙዚቃዎችና በቲክቶከሮች ጭፈራ ተሸፈነ፤ በእለቱ ተገኝተው ስራዎቻቸውን ያቀረቡት ድምፃዊያን ደግሞ አስገኘው አሽኮ(አስጌ ዴንዴሾ)፣ አዲስ ሙላት፣ ሊያ ግርማና ኪስማው ብቻ ሆኑ 🔷 ክስረት ከኮንሰርቱ በኋላ.... አነጋጋሪው ኮንሰርት በትርፍ ሳይሆን በበዛ ክስረት ተፈፅሟል፤ አዘጋጆቹ ያወጡትን ሩብ ያህል ሳያገኙ የለፉትን ሲሶ ያህል ሳይካሱ ድግሳቸውን ለበላተኛ አስረክበው በገንዘብም በሞራልም ከስረው ወጡ፤ ከመንግስት ጫና በተጨማሪ ለውሳኔ በመዘግየታቸውና ኮንሰርቱን ወደ ሌላ ቀን የማሸጋገር እድላቸውን በማበላሸታቸው ዋጋ ከፍለዋል፤ ብዙ ወጪ አውጥተናል የሚሉት አዘጋጆቹ ስኬትና ትርፍን ሳያሳኩ መና ቀርተዋል፤ ከህብረተሰቡ ጋር እልህ የተጋባውና ለገፅታ ግንባታ ተጨንቆ ኮንሰርቱን የተቆጣጠረው መንግስትም አብዝቶ ከስሯል፤ የህዝብ መቀለጃ ሆኖ ራሱን አስገምቷል፤ ለአርሴናል የደጋፊዎች ቲቪ የታሰበው መልካሙን የማሳየት እቅድም ሰዎቹ ሁኔታውን ተረድተውና በሚዲያዎቻቸው ብዙዎች ተቃውሞን በመላካቸው መንግስት የታሰበውን ያህል ሙገሳ ሳያገኝ ከስሮ ጨርሷል፤ ከቅዳሜው ኮንሰርት ያተረፉት ሳይመጡ የቀሩት ድምፃዊያንና በነፃ ገብተው፥ በነፃ ድራፍታቸውን ጨልጠው፥ በተዘጋጀላቸው የነፃ መኪና ወደ ቤታቸው የተመለሱት የመንግስት ገፅታ ገንቢዎች ብቻ ሆነዋል (ታምሩ ዓለሙ) የ"የካቲት" ሚዲያ የመረጃ አማራጮች:- ዩቲዩብ:- http://www.youtube.com/channel/UC2PqwMOdmlpqMal8TVVmzOA ቴሌግራም:- https://t.me/mteirdc2014 ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61564713743239

ክብሪት
ክብሪት
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 08 June 2026 04:34:29 GMT
104574
1561
54
346

Music

Download

Comments

l.m.not.robot
ሞት ይብቃ :
አዘጋጁ እኮ መንግስት ነው አገርን ሰላም ለማስመሰል የቀበሌ ካድሬና የገጠሩን ሰው ትራንስፖርት መድቦ ከተማውን አግማማው
2026-06-08 15:27:27
41
arsenal_arsenal7
Ewunet jimma :
እኔኮ ዩናይትዶች በኳስ ብቻ ሚቋጥሩ ይመስለኝ ነበር ለካ በኮንሱርትም ይቋጠራል
2026-06-08 20:05:42
2
yonathanforreal
Yonathan :
By the way hizbu rasu hunetawn meredat neberebet ye sewoch hiwot laymeles neger ye 4 wer plan be 1 ken bado yihun new mitilit
2026-06-08 18:42:56
5
binkades
Binka Des :
ለዘገባው እናመሰግናለን ይመችህ
2026-06-08 13:24:04
10
yonishaaa
Yoni United :
አልከሰረም አዳነች 30million setawalech
2026-06-08 13:53:21
9
e.elmarket
Bty👩‍⚕️ :
ከሰላም ይልቅ ኮንሰርት ሰዉ መምጣት አለመምጣቱ የሚያሳስበዉ የኛ መንግስት¡ ብቻ ነዉ
2026-06-08 19:45:53
2
abi96525
Abi :
በአንዱ ደስታ ሌላው ለምን ይበሳጫል
2026-06-08 15:58:01
5
markafmibabu
marken :
it is absultly false i was there it was so amazing celbration wow vardas thank you also draft jambo was 100 birr.my bro
2026-06-08 14:48:38
2
gadisa.gemechu4
gadisa gemechu aga :
አላማቹ ይሄው ነበር ማበላሸት
2026-06-08 12:00:49
4
bini.boss015
ቢኒ የጌታ ልጅ 🙏🏼 :
እየሱስ ጌታ ነው 💪🏼💪🏼💪🏼💪🏼
2026-06-08 14:42:21
2
chuchu86644
chuchu :
አይ ኮንሰርት ላይም ይቋጠራል 😂😂
2026-06-08 19:40:07
1
tsicat
Nuni💚 :
ay arsenal😂😂🙄
2026-06-08 17:07:55
1
eri.w2
ew :
esey
2026-06-08 20:13:37
0
user3921420261391
user3921420261391 :
እሰይ
2026-06-08 15:58:54
1
seyaunited3
Seya UNITED :
ድሮስ arsenal mnum atrafi ahonim degafiw hoo hoo bay
2026-06-08 13:32:41
2
yggb34
Melihamig :
deseyelale
2026-06-08 12:21:59
2
sami04367
sami :
እሰይ
2026-06-08 18:19:26
0
million327
M-News :
እኔ ኮ ምንተፋጥሮ ነው እያልኩ ነበር እናመስግናለን
2026-06-08 13:41:47
0
user1105015379372
user1105015379372 :
እሰይ
2026-06-08 10:36:33
15
absill120.1
tarik :
አይዞኮ ወንድሜ
2026-06-08 18:30:17
0
yoni42815
yoni :
yes wedikea.mengiaste
2026-06-08 15:55:04
0
ma_ma505
እናቴ ብርሀንዬ! 🇪🇹 :
Sad!
2026-06-08 11:31:08
1
user2329423558554
Dave :
ተሳካልን
2026-06-08 12:28:19
1
jebesa4
Tomas :
ተምቾች እንዳሂካሄድ የተረባረቡበትበምቀኝነት ሪከርድ የሠበረ ምርጥ ኮንሰርት
2026-06-08 14:52:20
1
kalkidanbekele629
Kalkidan Bekele :
ምን አይነት ቡድን ነው እላይ ድረስ ሰው አለው
2026-06-08 15:06:53
1
To see more videos from user @amanenyew, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About