@yilugg: "ገባር ለመተለም ጀግና ለማለም ሲታደሉ የኔና የሸማኔ ግን ማቅለም ብቻ ነው የጥበብ መጎናፀፊያ ለመሸለም" እንዲል ባለቅኔው በኑሮ እየተለኮሰ ከሰው ልቡ እንደ ጧፍ እያበራ ከጀምበር መፍለቂያ እስከ ጀምበር መጥለቂያ ተጉዟል። "ፀፀትና ጥላ ያንድ እናት መንትያ ልጆች ይመስላሉ ጥላም ይከተልሃል ፀፀትም ያሳድድሃል ሁለቱም ካንተ አይለዩም" ይል ነበር አያ ሙሌ እነሆ ወልድያ እነሆ እኛ ከፀፀት ማምለጫ ሰፊናችንን ተሳፈርን እግር በክንፍ ቢለወጥ ወልድያ ደጃፌ በሆነች ነበር። ትውልድህ ሆድህ ነው አገርህ ነገርህ ባንዲራህ አደራህ ሞትህ ሹመትህ ትንሣዬህ ሱባዬህ መላህ ባላህ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ትውልዴ ልቡ ለሙሉጌታ ተስፋዬ እምቡር እምቡር ማለቻው ሆኖሎታል። ለአያ ሙሌ አገሩ ነገሩ ነበረች። ከማየ ዕንባ እስከ ደም ጠብታ የዋተተላት ውለታ ቢስ ሀገር። ሞቱን ሹመት አድርጋ የሰጠችው የእንጀራ እና የመንቶች እናት። እግዚኦ ከእግዚኦ በቀር ሞቼ ቀባሪ አጥቼ ላይ ታይ የምላጋ አስክሬኔ ተኘቶ ባልጋ አለሁ እየመሰለኝ ለካስ በድን ኖሬያለሁ እንደ ጠይብ ካ'ፈር አብኩቶ ቆርሶ እየኮላ አበሰለኝ በብቸኝነት ሱባዬው ትንሳኤውን እንዲህ እያለ የነገረን የወሎው አበጋር ሸኹ ሙሉጌታ ዛሬ ለዐይን ሙላት ምልዓት የተመላለሰባት ወልድያ መታሰቢያውን አቆመችለት። ይህን ያህል ጊዜ ስስት እንደ ጉጉት ጥንድ ዐይናችንን ጋርዶን በብርሀን ስንድፈነፈን ቀን ቀንን ወልዶ በላይ በላይ እየለየ ይህን ለመመልከት ያበቃን ወርቅ መኖር ምንኛ ቅዱስ ነው። አያ ሙሌ "ንጉሥ ብሆን የምቀመጥበት ዙፋን የሚሰራበት ማቴሪያል ሊሆን የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው" ይላል ዙፋኑን በፍቅር ትጎናበሱት ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው። "የጎዳናው መነኩሴ የዘላለም ሕይወት ምስክርነት" (ይህችን ቅፅበት ኖርኩ) ቸር ያቆየን
𝙮𝙞𝙡𝙖𝙦 𝙜-𝙜𝙞𝙤𝙧𝙜𝙞𝙨
Region: ET
Tuesday 09 June 2026 18:42:20 GMT
Music
Download
Comments
ArAdoM T Yohannes Seyoum :
"የሰከነች ሰፊና"❤🙏
2026-06-10 16:36:28
1
የቀኑ ስራወች :
በጣም ደስ ያለኝ በትውልድ አገሩ ሲታወስ ሲታወስ ይኖራል የባለቅኔው መሀላ አያ ሙሌ ሙጌታ ተስፋየ 🙏🙏🙏
2026-06-10 08:00:44
2
ማይኮ :
አያ ሙሌ🥰🥰🥰.....
2026-06-09 19:05:07
1
₩adu :
በጣም ደስ ብሎናል🎊
ለሙሌ አይበዛበትም ይሄም ሲያንሰው ነው ስለ ሙሌ ገና ነው ገና።
2026-06-10 16:09:15
1
Josh :
ሙሌ💪💪💪
2026-06-09 19:25:59
1
ከ_ገዛኸኝ 🦅 :
ገና ነው ሀውልት መቆም አለበት እላለሁኝ። መቸ ብትሉኝ ሁላችንም ስንረዳው አንድ ቀን እላለሁኝ❤❤😍
2026-06-10 16:16:03
1
To see more videos from user @yilugg, please go to the Tikwm
homepage.