@jgggjkhgffgjijgtyiiiji: የእስራኤል ጦር ከኢራን ጋር የነበረው ግጭት በቆመ ማግስት ለሊባኖስ ከተሞች የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ የእስራኤል ጦር የተኩስ አቁም ስምምነት ባለበት ሁኔታ እና ከኢራን ጋር የነበረው ግጭት በቆመ ማግስት፤ለሊባኖስ ከተሞች ነዋሪዎች የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አቪቻይ አድራኢ በኤክስ ገጻቸዉ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‹‹በሄዝቦላህ አባላት፣ ተቋማት ወይም ወታደራዊ ቁሳቁሶች አቅራቢያ መገኘታችሁ ለህይወታችሁ አደገኛ ነው››ሲሉ ገልጸዋል። ቀደም ሲል ሰኞ ዕለት ኢራን በእስራኤል ላይ የምታደርገውን ጥቃት ማቆሟን አስታውቃ ነበር፤ ሆኖም የእስራኤል ጥቃት በሊባኖስ ላይ የሚቀጥል ከሆነ ‹‹አሰቃቂ›› ምላሽ እንደምትሰጥ አስጠንቅቃለች። ቀጣናዊ ውጥረቱ የናረው እሁድ ዕለት እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ባለበት ሁኔታ የሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩትን በቦምብ መደብደቧን ተከትሎ ነው። ይህ ድርጊት ኢራን ወደ ሰሜናዊ እስራኤል የአጸፋ ሚሳኤሎችን እንድትተኮስ ያነሳሳት ሲሆን፤ ይህም በምላሹ እስራኤል በኢራን ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት እንድትሰነዝር ምክንያት ሆኗል። #creatorsearchinsights #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ethiopian_tik_tok🇪🇹 #ethiopian_tik_tok #ethiopia

peace media (ሰላም ሚድያ)
peace media (ሰላም ሚድያ)
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 09 June 2026 19:29:32 GMT
4402
61
2
5

Music

Download

Comments

user1523979145131
kuba :
bire.nozmd
2026-06-09 20:32:52
0
akimel.smart
Birr ነው ዘማዴ :
🥰🥰🥰
2026-06-09 20:18:59
0
To see more videos from user @jgggjkhgffgjijgtyiiiji, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About