@manendante3: በጫካ ውስጥ "ባሩንዳ" የሚባል ሁለት ራስ ግን አንድ አካልና አንድ ሆድ ያለው ወፍ ነበር። የቀኙ ራስ አስተዋይና ታጋሽ ሲሆን፣ ግራ ኛው ራስ ደግሞ ምቀኛና ቶሎ የሚቆጣ ነበር። አንድ ቀን ቀኙ ራስ በጣም አንድ ጣፋጭ ፍሬ አግኝቶ በልቶ ፍሬው በጣም ጣፋጭ እንደነበረ ይናገራል።ይህንን የሰማው የግራ ኛው ራስ በቅናት 'እንዴት አላካፈልከኝም ከመዋጥህ በፊት?'። ብሎ ቀኙ ላይ ጮኸበት። ቀኙ ራስ "ወንድሜ እኔ ብበላው ወይም አንተ ብትበላው ምን ልዩነት አለው? ሆዳችን እኮ አንድ ነው፣ ለአንተም ይጠቅማል" አለው። ግራው ሊሰማው አልቻለም። በጥላቻ ተሞልቶ በቀልን ያጠነጥን ጀመር። ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ የግራ ኛው ራስ መሬት ላይ መርዛማ ፍሬ ያያል። "ይህንን መርዝ በልቼ ያንን ቀኝ ኛውን ራስ እገድለዋለሁ!" ብሎ ይነሳል። ቀኙ ራስ እየለመነው "እባክህ እንዳታደርገው! መርዙን ከበላኸው የምንሞተው ሁለታችንም ነን!" እያለ ቢጮኽም፣ የግራ ኛው ራስ ግን መርዙን ዋጠው። ብዙም ሳይቆይ መርዙ በአንድ አካላቸው ውስጥ ተሰራጭቶ ሁለቱም ራሶች በስቃይ ህይወታቸው አለፈች። በቤተሰብ፣ በማህበረሰብም ሆነ በሀገር ደረጃ ሁላችንም የተለያየ ሃሳብ (ሁለት ራስ) ቢኖረን፤ የምንጋራው ህይወት ግን አንድ አካል ነው። ሌላውን ለመጉዳት የምንረጨው መርዝ፣ በመጨረሻ እኛኑ መልሶ ያጠፋናል።ሌላው ሲጠፋ አብረን እንደምንጠፋ ካወቅን፣ ጥላቻን ትተን በፍቅር መኖር እንጀምራለን። ፍትህ በግፍ ለታሰሩ መምህራኖቻችን
ኖፊር የክርስቶስ እስረኛ ⛪
Region: AE
Wednesday 10 June 2026 09:27:41 GMT
Music
Download
Comments
eyenorn new besu chernet :
አሁን ያለችበት የኢትዮጲያ ስቃይ
አንድ አካል አንድ ሆድ ኢትዮጲያ ስኮን
ሁለቱ እራሶች እኛነን 😭😭😭😭😭😭አቤቱ ጌታሆይ የግርህን መረገጫ ጎብኛት😭😭😭😭
2026-06-10 18:03:10
24
(Beza)ቃልህ እውነት ነው የሐ ወ 17:17 ⛪ :
እዉነት ነው ማንም ማንም አጥፍቶ ብቻዉን አይኖርም ብንከባበር ይሸላል
2026-06-10 14:46:13
14
seni :
በትክክል ማንም ብቻውን ደስተኛ ሁኖ መኖር አይችልም
ስለዚ መከባበሩ ይበጀናል
2026-06-10 19:25:14
5
beki🦚21beki :
አሁንማ እርስ በእርስ በመበላላታችን ምክንያት ለእግዚአብሔርም ያቃትን ይመስለኛል 😔😔😭
2026-06-11 04:33:34
8
deje :
በጣም ደስ የሚል ፅሁፍ ነው ሰሚ ቢገኝ
2026-06-14 09:12:35
1
memehr deje :
በጣም በሳል እና አስተማሪ ሀሳብ ነው ቅን ማሰብ ላልቻልነው ለኛ ግብዞች ልቦና ይስጠን።
2026-06-11 10:05:47
8
🥀xxx 🇪🇹 🇨🇦 :
ችግሩ ሰለሰላም የምትሰብከው ሰለ መቻቻል የምትሰብከው ይችው ቤተክርስቲያን ብቻ ነች ልጆቿንም በስነምግባር ኮትኩታ ያሳደገች ሰለሀገር በሎም ሰለአለም የምትጨነቀው ሁሉም ሀይማኖት ይህን ቢያሰብ ዛሬላይ የት በደረስን 😥ፍትህ ለመምህሮቻችን ☝️
2026-06-11 13:55:13
1
🦅ንስሯ🩸ከጎንደር💪💚💛❤️ሙሉ ሸዋ :
ትክክል🥺🥺🥺
2026-06-11 12:50:07
1
Adanach :
እውነት ነው ቃል ህይወት ያሠማልን የታሠሩትንም ፉትህን እግዚአብሔር ይሥጣቸው🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-11 14:19:18
1
𝓯𝓸𝔃𝓲 ♥️💫🦋 :
ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ💔💔🥹🥹😭😭😭
2026-06-11 08:22:23
1
@አልሚ የናቷ 21 :
efffff kale hiwet yasemaln🥰🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-11 00:15:56
1
fiseha...🤗 :
wow
2026-06-12 10:39:21
1
S ባለ ማህተቧ🎚 :
🥰🥰🥰🥰 ቃለ ሂወት ያሰማልን
2026-06-10 23:01:23
1
ወዱ አስቻለው ደሴ💪 :
ቃለ ሄወትን ያሠማልን
2026-06-10 18:27:20
1
መ/ር ዲያቆን ታደሰ ፋንታው :
ይሄ መንግስት ግፈኛና ገዳይ ወይም አቅመ ቢስነው
2026-06-11 08:39:32
1
faye :
hulum ye ejun yagnal
2026-06-12 07:33:30
1
user9138465261387 :
masetwale yeseten 🥰🥰
2026-06-11 11:11:12
1
tigr :
ፈትህ የለጥፋት ለታሰሩ መምህሮቻችን
2026-06-11 17:44:22
1
ልቤ በእግዛአቤሔሪ ፀና🦋🌸 :
አሜን ቃለሄውት ያሰማልን🥰🥰🥰🥰
2026-06-10 16:26:39
2
kumneger tilahun/kume/ :
እስኪ አንድ እንሁን
ትልቅ ትምህርት ነው
2026-06-11 13:04:12
3
sara :
እዉነት ነዉ ቃለ ህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-10 18:36:34
3
መባ⛪️ ☦️🛐 :
ahun yalenibet ye ethiopian hizboch ena kirstina🙏🙏🙏
2026-06-11 06:12:15
1
Banch ነኝ የጎንደሯ @የኪድየ ልጅ✝️🕊 :
በትክክል 👍👍👍
2026-06-10 18:20:14
1
እሙዬ☦️ንስሯ🦅ሙሉ ሽዋ🔥 :
በጣም 😭ኡፍፍ
2026-06-10 21:49:59
1
Bነኝ 💞 የልጆቼ ናፋቂ💝 :
በጣም ተምሬበታለሁ ቃለህይውት ያስማልኝ 🙏🙏ፍትህ ላባቶቻችን🙏🙏🙏
2026-06-10 23:06:03
1
To see more videos from user @manendante3, please go to the Tikwm
homepage.