@melakufekadu1: የኢትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!!! ******** 1ኛ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡ 2ኛ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡ 3ኛ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:- 1=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው 2=በራሱ ፈቃድ 3=በጤና ጉድለት 4=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት 5=በሞት ናቸው፡፡ 4ኛ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:- 1= በእርጅና 2=በህመም 3= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ 4= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ 5=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡ 5ኛ የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:- 1=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡ 2=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም):: 6ኛ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:- = ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡ 7ኛ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡ 8ኛ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡ 9ኛ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡ 10ኛ ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:- 1=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2) 2=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ 3= የጡረታ መለያ ቁጥር 4= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ 5= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ 6= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ 7= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ ናቸው፡፡

መላኩ ፍቃዱ - Melaku Fekadu
መላኩ ፍቃዱ - Melaku Fekadu
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 11 June 2026 07:56:31 GMT
114712
1361
41
877

Music

Download

Comments

onjayfet
yafet :
አናመሰግናለን
2026-06-11 12:58:41
4
ruth58121
ruth :
ዳረጎት ማለት ምን ማለት ነው
2026-06-12 10:25:00
1
tariku.dibaba4
Tariku Dibaba :
thanks
2026-06-11 17:26:02
0
debela.legesse
Debela Legesse :
Thanks🥰
2026-06-11 17:22:40
0
alexadanr3531
Alex Adane :
tnx
2026-06-12 08:59:00
0
indalkachewdesale
indalkachewdesale :
እናመስግናለን
2026-06-12 06:53:44
0
user62202012058751
Mhamed Ebrahim :
thank
2026-06-11 17:12:17
0
tilahwilyyu
tilah :
እናመሰግናለን
2026-06-11 19:33:08
0
ume9372
umer.moh :
thanks🥰🥰🥰
2026-06-11 16:22:02
0
yetayewashagera
ኢትዮጵያ ትቅደም :
እናመሰግናለን
2026-06-11 17:56:15
0
abenezer.tadesse3
Sosna Tadesse :
አመሰግናለሁ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-11 16:11:18
0
mareg.bogale
mareg bogale :
እናመሰግናለን
2026-06-11 20:03:41
0
emuye5769
Emuye :
እናመሰግናለን🙏🙏🙏
2026-06-11 18:33:17
0
getalem.mekuanint
Getalem Mekuanint :
አመሰግናለሁ
2026-06-11 15:37:13
0
yeabreshlij
Bini 🦅 Man🇪🇹 :
(10*30%)+(18*1.25)=30+22.5=52.5% its calculation correct????
2026-06-11 20:22:45
0
idfosa
Idossa 4578 :
thanks
2026-06-11 18:17:25
0
meseretterefe543
meseret :
thanks
2026-06-11 15:55:58
0
genh315
gen@h :
አናመሰግናለን
2026-06-11 14:19:06
0
muluneh874
Haile :
እናመሰግናለን
2026-06-11 18:12:25
0
seidseid496
seidseid496 :
east.Tv
2026-06-11 18:22:36
0
manisha.makonen
ሁሉ በእርሱ ሆነ :
እናመሰግናለን
2026-06-11 18:08:25
0
setegndagnewwored
setu dagnew worede :
የግል ሰራተኞችንም መረጃ ስጡን??🙏
2026-06-11 19:23:59
0
yonaskebede44
ክርስቶስ የማምለጫ ዓለት የወንጌል አገልግሎት :
ሚስተ ወይም ባል አይወርሱም ነው ማብራርያው?
2026-06-11 18:53:21
0
abena.arere
Abena Arere :
tibelaleh
2026-06-11 18:01:29
0
awilemon3
Awi-Lemon :
ይሄ ስሌት መጠነኛ ስህተት ይዟል? "10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው" ምክንያቱም 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 3+22.5= 25.5% ስለሚሆን:: ስለዚህ የመጀመሪያው አስር ዓመት በ30% ከሚባል ይልቅ 10ዓመት×3 + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ትክክል ያደርገዋል::
2026-06-11 20:04:30
0
To see more videos from user @melakufekadu1, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About