@tofiklawyer: በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱ የተሽከርካሪዎች መለያ ሰሌዳ (ታርጋ) ዋጋ ስንት ነው ? ዛሬ በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ለተመዘገቡና ወረፋ እየጠበቁ ላሉ አዲስ መኪና ለገዙ ተገልጋዮች አዲሱ ታርጋ መሰጠት ተጀምሯል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአዲሱ ታርጋ የተተመነውን ታሪፍ ዶክመንት ተመልክቷል። የነዳጅ (የፊትና የኋላ ታርጋዎችን ጨምሮ) እንዲሁም የኤሌክትሪክ እና የተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪዎች ታሪፍ በየደረጃው በዝርዝር ተቀምጧል። በዚህም ፥ - የከተማና የሃገር አቋራጭ አውቶቡሶች፣ - የአካል ጉዳተኞች (PD) ተሽከርካሪዎች፣ - የመንግሥት ተሽከርካሪዎች፣ - ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) የሰሌዳ ዋጋ ለነዳጅ 9,400 ብር ሲሆን፣ ለኤሌክትሪክና ተፈጥሮ ጋዝ ደግሞ 7,100 ብር ሆኖ ታሪፍ ወጥቶለታል። ለሕዝብ ታክሲ ትራንስፖርት ለነዳጅ 11,700 ብር ለኤሌክትሪክ ደግሞ 9,400 ብር ክፍያ ተቆርጦለታል። በከፍተኛው የዋጋ ተመን የተመደቡት ፦ - የግል መገልገያ፣ - የንግድ፣ - የዲፕሎማቶች፣ - የዕርዳታ ድርጅቶች፣ - ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም የልዩ ተንቀሳቃሽ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳዎች ሲሆኑ ለእነዚህ ዘርፎች ለነዳጅ ታርጋ ዋጋ 56,000 ብር፣ ለኤሌክትሪክና ተፈጥሮ ጋዝ ታርጋ ዋጋ ደግሞ 44,500 ብር ተቆርጧል። በተጨማሪም የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ሰሌዳ 28,500 ብር ፣ የኤሌክትሪክ ሰሌዳ 15,200 ብር ታሪፍ ተቆርጦላቸዋል። ዝቅተኛው የዋጋ ተመን የተቆረጠው ለባለ ሁለት እግር (ሞተር ሳይክል) ተሽከርካሪዎች ሲሆን ዋጋውም ለነዳጅ 4,700 ብር እንዲሁም ለኤሌክትሪክ 3,550 ብር መሆኑ ታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
Tofik Bedru(ጠበቃና የህግ አማካሪ)
Region: ET
Thursday 11 June 2026 10:47:19 GMT
Music
Download
Comments
abebegemeda71 :
ኢትዮጵያ ግን በመንግስት ነው የምትተዳደረው ወይስ ታግተናል
2026-06-11 18:50:34
29
Ronaldo :
ከአምስት ሺ በላይ ዘረፋ ነው
2026-06-11 17:26:33
22
Habtamu 🥀💚💛❤️🇨🇬 :
the cause of IMF Administration
2026-06-11 21:44:43
0
Berhanu D :
ማጅራት መችነት ብቻ ነው ሊባል የሚችለው።
2026-06-11 17:39:55
13
Kaf :
ሌባ መንግስት፣ መንግስት አገልጋይ እንጂ አትራፊ ድርጅት አደለም።
2026-06-11 19:08:08
12
Yoni physio :
ከአንተ መስማት የምንፈልገው ከህጉ አንጻር እንዴት ይታያል, ምንም ያልተበላሸ በደምብ የሚታይ ታርጋ እያለን መንግስት ለራሱ አሰራር ብሎ ለቀየረው እኛ ይህ ያክል መክፈል አለብን ወይ ምን ያክል ህጋዊ ነው?
2026-06-11 18:54:04
6
Abel :
ወደድክም ጠላህም የIMFን ብድር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በምክንያት ይከፍላታል !
2026-06-11 19:59:20
1
gedi :
ከሌባ መንግስት የሚጠበቅ ነው
2026-06-11 19:03:50
5
jemal :
ውድ ወንድሜ አክባሪህ ነኝ ነገሮች እንደዚህ በባለሙያ ሲነገር አግባብ ነው በደንብ ንገርልን ለራሱ የአሰራር ለውጥ ባለ መኪናው ምን አገባው
2026-06-11 19:44:03
5
Matias Zewdu :
👉 ዘረፋ ነው። እንዴት መንግሥት የታርጋ ችርቻሮ ውስጥ ይገባል?🤔
2026-06-11 18:14:29
5
Mamilaa :
አሁን ገና ኢትዬጲያ በቀኝ ግዛት ተያዘች
2026-06-11 18:56:48
3
ቢኒ ህትመት+ጋርመንት ሥራዎች :
ልክ አይደለም ማሥተካከያ ይደረግበት።
2026-06-11 18:16:45
4
soIomone markos :
በጣራራ ፀሐይ ዘራፈ አራ ሼም ነው
2026-06-11 19:28:27
2
Tad :
መንግስታዊ ዝርፍያ
2026-06-11 18:46:17
2
adu :
ህዋት በሰንት ጣሙ
2026-06-11 20:12:25
2
The mind :
thank you
2026-06-11 20:06:31
0
Judy Haile :
Daylight robbery🥰
2026-06-11 19:17:28
0
Shiloh Speciality :
At a time when fuel prices and the overall cost of living continue to rise, asking citizens to pay up to 56,000 birr for a license plate replacement seems unreasonable. While modernization may be necessary, the fee should be affordable and take into account the economic challenges many people are currently facing. I respectfully urge the authorities to reconsider the pricing and adopt a more fair and practical approach.
2026-06-11 19:22:49
0
Anteneh Tasfaye :
ትክክል አግባብ አይደለም
2026-06-11 17:53:40
3
ezra ermiyas :
የዜጎችን ሰርቶ የማግኘት (የመለወጥ) መብት የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም መጋፋት(መቀማት) ነው
2026-06-11 18:49:57
4
Alemayehu taye :
ህዝቡን ፋራ አረጋችሁት ደስ ባለህ ግዜ ህግ ቀያይሩ አብሽር ያዋጣል
2026-06-11 19:22:39
1
A.c.d :
አረ በወርቅ ነዉ
2026-06-11 18:45:14
1
cantry693 :
ለኛስ ማነው የሚያስበው ተጨነቅን
2026-06-11 19:51:50
1
Right :
የወርቅ ታርጋ ነውዴ
2026-06-11 21:20:01
1
አሜን :
ሲጀመር የታርጋው አገልግሎት አንዱን ተሽከርካሪ ከሎላው ተሽከርካሪ ለመለየት ነው ጥቅሙ ! ይቀየር በብሄር መለየት የለበትም ኢት ይሁን ከተባለ ሀሳቡ ጥሩ ቢሆንም አሁን በታርጋ ሳይሆን በቋንቋ ሆኗል መለየት የተጀመረው እሱ እንዳለ ሆኖ የታርጋው ጥር እቃ ወጪው አንድ አይነት ሆኖ ክፍያው የሚለያይበት ምክንያት አልገባኝም ከሆነ የሁሉም ተሽከርካሪ እኩል ክፍያ መሆን አለበት ኧረ እንተሳሰብ
2026-06-11 20:38:25
1
To see more videos from user @tofiklawyer, please go to the Tikwm
homepage.