@mulukal_kal: እዚህ እኛ ጂም ውስጥ እየገረመኝ ከመጣው ነገር ውስጥ የአብዛኞቹ ሴቶች ስፖርት የመስሪያ ሰዐት ነው። ልብ ብሎ ላስተዋለው ሰው ጂም ውስጥ ብዙ አይነት ክፍፍል አለ! ያላገቡ ወጣት ሴቶች ፣ ወልደው ሰውነታቸውን ለማስተካከል የሚሮጡ እናቶች ፣ እርጅና ሊነካካቸው ሲል በስፖርት ሊፋለሙት የመጡ ጎልመስ ያሉ ቆነጃጅቶች በዘርፍ በዘርፍ ሆነው እያወሩም ትንሽ ትንሽ እየሰሩም ያዘግማሉ። ባለፈው እንዳጫወትኳችሁ መቀመጫቸውን ለማወፈር እንደሚሰሩት ለኛ ለቀሪዎቹ የተሰጠ መዝናኛ የለም። ከትንሽ ቁጭ ብድግ በኋላ በመስታወቱ ውስጥ የመቀመጫቸውን እድገት በአይናቸው ይመዝናሉ። ለምን ይዋሻል? እኛም ሲመዝኑ አብረን እንመዝናለን 😊 ታዲያ ሰውነቴን ድክምክም ብሎኝ ጂም በገባው ባንዱ ቀን አጠገቤ ካለ የመሮጫ ማሽን ላይ ሶምሶማ የምትሰራ ሴት ስልኳን አንስታ ምንም ሰላምታ ሳትለዋወጥ " እራቱን ሰጠሽው?" የሚል ጥያቄ ወረወረች። ከዛኛው ጫፍ "አልበላም" ብሏል የሚል መልስ ተመለሰላት መሰል "ለምን?" ብላ ጠየቀች። አሁን ምን ይመለስላት እንጃ ፊቷን ቅጭም አርጋ ስልኩን ዘጋች። ልጇ ቢሆን ነው በሚል ግምት ውስጥ ሆኜ አሁንም ስልኳን አንስታ "ለምንድነው እራት ያልበላኸው" በሚል አንባረቀች? አሁንም ጥቂት ቆይታ " እኔ ከእንግዲህ በኋላ እራት አልበላም። እሱን ደሞ ነግሬሃለው። እዚህ የምደክመው በከንቱ ነው እንዴ ?" ብላ እየተነጫነጨች ስልኩን ዘጋችው። ከዚህ ቀን በኋላ ልጅቷን ማስተዋል ጀመርኩኝ። እንደምትለው ሰውነቷ በጣም ወፍሮ እራት የሚያስበላ አይደለም። መጥታም ስፖርቱን ነካ ነካ ብታረገው እንጂ ብዙም አትለፋም። ትንሽ ሰርታ ስልኳ ላይ ትንሽ ተንቀሳቅሳ ትካዜ ውስጥ ነች። ብቻ በዚም በዛ ጂሙ እስከሚዘጋበት ሰዐት ድረስ ታዘግማለች። አሁን መቼ ለት ጂም ውስጥ ትንሽ ተፍ ተፍ ብዬ ምግብ ለመቀማመስ ከህንፃው ስር ካለ ካፌ ብገባ እራት የማትበላዋ ቆንጆ ስቴክ ሳንዱቿን ከጁስ ጋር እያጫወተች ነው። አስተናጋጁ መጥቶ "ምን ልታዘዝ?" እስኪለኝ ቁጭ ባልኩበት አይኔን መንቀል አቅቶኝ ነበር። የምበላውን አዝዤ በግርምት ዞር መለስ እያልኩ ሳያት በፈገግታ " እንብላ" አለችኝ። አጋጣሚው እንዲያልፈኝ ስላልፈለኩ "እንደውም እርቦኛል" ብዬ ወንበር ስቤ ቁጭ አልኩኝ። በፈርጥ የተንቆጠቆጠ የጋብቻ ቀለበቷን አርጋለች። ጠረጴዛ ላይ ያለውን የመኪና ቁልፏንና ቦርሳዋን ወደ ወንበሩ እየወሰደች አንዱን ቁራጭ ሳንዱች ወደ ፊቴ ገፋችልኝ። ሳንዱቼን አንስቼ እየገመጥኩ "እኛስ የሚያበስልልን አጥተን ነው። ደክሞሽ ነው ወይስ ሙያ አጥተሽ ነው ውጭ የምትበይው?" ብዬ ፈገግ አልኩኝ። " ሙያው እንኳን ነበረ ምን ዋጋ አለው?" ብላኝ ጨዋታችንን ቀጠልን። ውስጧ ያለውን ጩኸት መተንፈሻ ቦታ አጥታ ሰበብና አጋጣሚ ብቻ ስትፈልግ እነደነበር የገባኝ ሰዐት ከማይሞላ ቆይታ በኋላ ካፌው ሊዘጋ መፀዳት ሲጀምር ነው። ታሪኳ እንዲህ ነው። ካገባች ገና ወራት አልተቆጠሩም። በትዳሯ የገንዘብ ችግር የለባትም። ባሏም ይሄንን አጎደለብኝ ይህንን በደለኝ የምትለው ነገር የላትም። በኑሮዋ ምንም ባይጎልም እሷ ጋር ደስታ የሚባል ጓዙን ጠቅልሎ ጠፍቷል። ጭራሽ ከባሏ ጋር የምታሳልፈው ጊዜና የምታወራው ሁሉ ይጨንቃታል። ጂሙ ለጊዜው ያገኘችው ማምለጫ ሰበቧ ነው። ምን መወሰን እንዳለባት ግራ የገባት ሴት። እናቷ ከመቼ መቼ ታረግዣለሽ? ብለው በጉጉት የሚጠብቋት እህቶቿ እንደ አርአያ የሚከተሏት ሴት ማንም ያለችበትን የስሜት ውዥንብር አያውቅላትም። የምትፀልየውንና አጥብቃ የምትፈልገውን እንኳን የማታውቅ ግራ የገባት ምስኪን ሴት! ትልቅ ቤት ያማሩ ፈርኒቸሮች ቆንጆ መኪናና ምቾት የከለሉት ባዶነት። የሰዎችን ፍርድ ሸሽቶ ፣ ሰው ላለማሳዘን ብሎ ከራሱ ጋር ትግል የያዘ ማንነት። ከራሷ ጋር ለመታረቅ ራሷ ውስጥ የመሸገች ነፍስ። ጊዜ ስሜቱን ካከመልኝ ብላ ልትወደው ያቃታትን ሰው ሳትፀንስ አምጣ ለመውደድ የምትታገል በራሷ ትግል ውስጥ ተሸንፋ የምትኖር ፣ ምናልባት ቀን ካከመኝ ብላ የምትዋትት ነፍስ። ጥሎብኝ ሰውን መስማትና ስሜቱን መረዳት እወዳለው ። በማንም ላይ ፍርድ አይስማማኝም። ያጠፋ ሰው ከምንም በላይ ከራሱ በሚቀበለው ቅጣት ያሳዝነኛል እንጂ የምፈርድበት ፅድቅ የሌለኝ ዱርዬ ነኝ። ስንቱ በስሜት ትግል ውስጥ ራሱ ለራሱ መወሰን አቅቶት "አንተ አውጣኝ" በሚል ፀሎት ውስጥ እንዳለ ቤቱ ይቁጠረው! ስንቱ በየቤቱ ያቀፈውን ክንድ የተንተራሰውን ደረት ተፀይፎ አለ? ስንቱ መኝታ ለይቷል። ስንቱስ በየቤቱ ብቸኝነት መሮት በሰው ረሃብ ይብሰለሰላል? ስንቱ ራሱ ተጣድፎ ከገባበት ጉድ "አንተ አውጣኝ" እያለ ነው? ሁላችን በራሳችን ምኞት ተጠልፈን የወደቅን። ሁላችን በአስጨናቂ ዘመን ውስጥ ግራ የገባን መፍትሄ የጠፋብን አይደለንም?። ሁላችንም ሽንቁራችንን በጨርቅ ለመጠቅጠቅ የምንሞክር እሱ ደርሶ ካላወጣን ከሱም ጋር ካልተጣበቅን በቀር በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ የምንገኘ ነን። እግዜሩ ግን ይገርመኛል "አጋባኝም" " አፋታኝም" የሚሉ ድምፆች ወደሱ ናቸው። የደስታውም ፣ የመሪር ሃዘኑም እንባ ከፊቱ ይፈሳሉ። መቻሉ ፣ ማኖሩ ፣ ይቅር ማለቱ ፣ ነውራችንን መሸፈኑ እንዴት ባለ ፍቅርና መቻል ነው? ብቻ አይታችሁ የምትቀኑበት አይኑር! #ethiopian_tik_tok #mulukal #ሙሉቃል #habeshatiktok #kesrabehuala
Mulukal_ ሙሉቃል
Region: ET
Thursday 11 June 2026 11:21:55 GMT
Music
Download
Comments
Tofik mah :
🥰🥰🥰በቃ አሁን ላይ ሁሉም ሚኖረው ህይውት ነው ክበርልኝ ብቻ ለሁሉም ነገር አልሃምዱሊላህህ በሰው ምንም ምቀናው የለኝ በሰጠኝ እጅግ አመስጋኝ እንድሆን ምለፍ ነኝ
2026-06-11 18:07:55
17
Emuka🇪🇹 :
how i love your storytelling
2026-06-12 21:09:36
4
Kal_ኪዳን 🤍 :
Captain 👌😍
2026-06-13 00:21:14
2
Learn English with RB :
beautifully written.🥰🥰
2026-06-12 19:06:59
2
Brukti :
caption🥺
2026-06-13 11:10:17
1
Betty Mimi461 :
ትክክል🙏❤️
2026-06-13 07:14:21
1
AMEN WOUNDU FAMILY :
ተባረክ ወንድሜ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-12 15:41:43
0
sweet cookies :
የምፈርድበት ፅድቅ የሌለኝ ዱርዬ ነኝ🥺
2026-06-11 14:19:14
26
kidist 😊 :
ሙሉዉን አነበብኩት🥺
2026-06-11 12:28:52
29
مينا♾️ :
oww the last phrases "aytachu yemtkenubet aynur" it's so deep
2026-06-11 11:38:35
13
ጌታ እኮ ነው :
powerfull
2026-06-11 23:02:56
3
❤ ልብ ለልብ ❤ :
ሁሉን የሚችለው ባይኖር ምን እንሆን ነበር 🥺🥺🥺
2026-06-11 21:55:16
3
user1717012496875 :
Endew i never know such a perfect and gobez sew like you
2026-06-11 18:55:53
3
astu444 :
storytelling 👌👌
2026-06-12 12:42:55
1
@yared :
አለም 9 የማትሙላ 10
2026-06-11 16:07:43
1
Tigist Ayalew :
ሙሉቃል 🥰👌 Well said 👏👏
2026-06-13 07:41:20
0
user4523243344530 :
በማንም ላይ ፍርድ አይስማማኝም
2026-06-14 14:42:35
0
@yemeserach teketel kesamo :
በዚህ አለም ምንም ነገር ጎዶሎ ነው ዋናው በተሰጠን ማመስገን ነው😔😔😔
2026-06-12 12:04:23
0
lideya tadesse :
🥰🥰 mulu kal
2026-06-13 19:18:51
0
кυмє zιɴαω ✍️ :
ኧረ አንብቡ! ጌታን ለሆነ ጥያቄያችሁ መልስ ታገኛላችሁ 🥰 አንተ ግን ትለያለህ @Mulukal_ ሙሉቃል ✌️
2026-06-11 17:24:29
4
እንደቸርነትህ :
😇😇😇
2026-06-13 06:51:08
0
fre :
🥰🥰🥰
2026-06-13 14:42:01
0
fayee🍫 :
🥺
2026-06-13 00:46:06
0
Skip Name :
🥰🥰🥰
2026-06-13 19:34:04
0
Addi👸 :
🙏🙏🙏🥰🥰🥰
2026-06-11 11:33:11
0
To see more videos from user @mulukal_kal, please go to the Tikwm
homepage.