@matvij9617:

Matvij sea shebherd
Matvij sea shebherd
Open In TikTok:
Region: UA
Friday 12 June 2026 06:53:46 GMT
200
8
0
1

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @matvij9617, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ሰኔና ሰኞ ታሪካዊ አመጣጡና ያስከተላቸው ዳፋዎች! --- ዓለም ከተፈጠረበት ወይም የቀን መቁጠሪያ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሰኔ እና ሰኞ በአስገራሚ መንገድ በየተወሰነ ዓመት ይገጥማሉ። የሰኔ እና ሰኞ ነገር አስገራሚነቱ በዚ’ ይጀምራል። ሌላ አስገራሚ ነገር እናክል። ሰኔ እና ሰኞ በ5 እና በ6 አመታት ልዩነት ይመጣና ቀጥሎ በ5እና6 በመደመር በየ11 አመት ይመጣል፤ ይህም አንድ አበቅቴ ይሆናል። ሰኔ እና ሰኞ ሌላም አስገራሚ ባህሪ አለው። በመቶ አመት ውስጥ ሁለት ጊዜ በጎዶሎ፤ ሁለት ጊዜ በሙሉ ቁጥር እያከታተለ ይመጣል። ከሌሎች ወራት በተለየ፤ ሰኔ እና ሰኞ በፈረንጅ ካላንደር ከገጠመ፤ በሳምንቱም በኢትዮጵያ ካላንደርም ሰኔ እና ሰኞ መልሶ ይገጥማል። የሰኔ እና ሰኞን ግጥምጥሞሽ… እንደዋዛ ፈዛዛ በጨዋታ መልክ የሚያልፉት ሰዎች የመኖራቸውን ያህል፤ በአውደ ቀመር የተካኑ፤ ስለመጥዕቅ በምጥቅ እና በጥልቅ የሚያውቁ የጥንት አባቶች ግን፤ ነገሩን በዋዛ የሚያዩት አይመስልም። ቀን ቆጥረውና አመታት አስልተው ሰኔ እና ሰኞ የሚገጥምበትን አመት፤ በጥንቃቄ እንድናልፈው ይመክሩናል። እኛም እንደሊቃውንት አባቶቻችን፤ የባህረ ሃሳብን እውቀት እና ቀመር መሰረት አድርገን በአገራችንና በአለማችን የተከሰቱ የሰኔ እና የሰኞ ግጥምጥሞሽን፤ ትንሽ በትንሽ እንጨዋወታለን። በኢትዮጵያ ክፉ ቀን የምንለው… ረሃብ፣ በሽታ እና ጦርነትን ነው። የሰው ብቻ ሳይሆን የከብት በሽታ ጭምር… የኑሮ ሚዛን የሚያዛባበት አጋጣሚ አለ። በ1880 ዎቹ መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ አስከፊ ረሃብ ሲቀሰቀስ፤ በስተበኋላም ብዙ ቸነፈር ሲወርድ፤ ሰኔ እና ሰኞ ገጥሞ ነበር። የከዋክብት ስነ ፈለግ እውቀት የነበራቸው አባቶችም፤ የሰኔ እና ሰኞን ግጥምጥሞሽ ከከዋክብቱ ተጽዕኖ ጋር ቀምረው፤ መጪውን የረሃብ ወይም የጦርነት ዘመን በትክክል ይተነብዩ ነበር። ዛሬ የምናደርገው… የቻልነውን ያህል አውደ ታሪክ ፈትሸን፤ “በእርግጥ ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም ምን ተፈጠረ?” የሚለውን ይሆናል። ከዚያ በፊት ግን አጼ ምኒልክ፣ አባታቸው ንጉሥ ኃይለ መለኮት፣ ልጃቸው ንግሥት ዘውዲቱ፣ እቴጌ ምንትዋብ፣ እቴጌ መነን… ሁሉም ከሰኔ እና ሰኞ አንድ አመት በፊት ወይም በኋላ ነው ህይወታቸው ያለፈው። ይህን ያህል ስለደጋጎቹ ካወጋን፤ ሌላውን ታሪክ በግርድፍ ፈጠን ቀልጠፍ ብለን እናወጋችኋለን። ወደ ዝርዝር አውደ ታሪካችን ከመግባታችን በፊት፤ ጥቂት ስለሰኔ እና ሰኞ አስገራሚ ባህሪ እንግለጽላቹህ። ሰኔ እና ሰኞ በ5 እና በ6 አመት፤ ከዚያም ከ11 አመታት በኋላ ይመጣል። ከ11 አመታት በኋላ የሚመጣው ሰኔ እና ሰኞ፤ በአገሪቱ ላይ የጦርነት ወይምየበሽታ ወይም የረሃብ ደመና ሊመጣ እንደሚችል ያመላክታል። እናም ለሚቀጥሉት አመታት ዝግጅት ካልተደረገ፤ በ3ኛው አመት ላይ የከፋ ቸነፈር ይወርዳል። ለምሳሌ ከ11 አመታት በኋላ… በ1880 ሰኔና ሰኞ ገጠመ። ዝግጅት ስላልተደረገ በሚቀጥሉት ሁለት እና ሶስት አመታት ከሃምሳ ሺህ በላይ ሰዎች በረሃብ ቸነፈር አለቁ። እንዲህ እንዲህ እያልን ባለፉት 200 አመታት የሆነውን ነገር አብረን እንመልከት። ከአንቀጹ በፊት ያስቀመጥነው አመት ሁሉም እንደፈረንጆች የቀን አቆጣጠር ሲሆን፤ ዝርዝር ታሪኩን ደግሞ ስንገልጽ በኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር እያልን ጽፈነዋል። >> የሰኔ እና ሰኞ መጥፎ ግጥምጥሞሽ ተምሳሌቶች ፦ 1812 በዚህ አመት ሰኔ እና ሰኞ ገጠመ። የንጉሥ ሳህለስላሴ አባት …መርድ አዝማች ወሰንሰገድ በዚህ አመት ከጦርነት በኋላ በብርቱ ቆስለው ሞቱ። 1829 በኢትዮጵያ ከፍተኛ ረሃብ ሆነ። ረሃቡን ተከትሎ የኮሌራ በሽታ በመምጣቱ በተለይ በሸዋ እጅግ ብዙ ሰው ሞተ። 1846 የዚህን አመት ሰኔ እና ሰኞን ተከትሎ፤ የሸዋ ንጉሥ የነበሩት፤ የምኒልክ አያት ንጉሥ ሳህለስላሴ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። 1857 በ19ኛ ክፍለ ዘመን ከነበሩት የሰኔ እና ሰኞ አበቅቴዎች መካከል፤ ይሄኛው አንደኛውና ተጠቃሽ ዘመን ነው። በኢትዮጵያ አቆጠጠር 1849 ዓ.ም መሆኑ ነው። ጥንቃቄ፣ ዝግጅት፣ ጸሎት እና ግዝት ካልተደረገ በቀር፤ አበቅቴ ላይ የሚያርፈው ሰኔ እና ሰኞ በተከታታይ አመታት የሚያመጣው ቸነፈር ከበድ ያለ ይሆናል። ይህ ዘመን የአጼ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ነው። በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1849 ሰኔ እና ሰኞ ከገጠመ በኋላ፤ አጼ ቴዎድሮስ በእጃቸው ያለውን እያጡ የነበረበት ፈታኝ ዘመን ነበር። በጎጃም ደጃች ተድላ ጓሉ፣ በሸዋ ሰይፉ መሸሻ፣ በሰቆጣ ዋግሹም ገብረ መድህን፣ በጎንደር ጋረድ ክንፉ እና ግንባሮ ካሳ፣ በትግራይ ደጃች ንጉሴ… አምጸውባቸው፤ ወሎ እና ቤጌምድርም አልገዛም ብሎ ያስቸገረበት ወቅት ነው። የጎንደር ቀሳውስት ተሰብስበው፤ ለአጼ ቴዎድሮስ አዲስ የመንግስት አሰራር እንዲከተሉ በድፍረት የተናገሩበት ሁኔታ ተከስቷል። ከዚያ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሸዋ መኳንንት የሚገደሉት ተገድለው፤ የተቀሩት እጃቸውን የተቆረጡበትን አጋጣሚ እናስታውሳለን። ሌላው ቀርቶ በአመቱ የአጼ ቴዎድሮስ ሚስት፤ እቴጌ ምንትዋብ በ1851 ዓ.ም ሞቱ። ቀጥሎም የእንግሊዝ ወኪል ፕላውዴንን የአጼው ዘመድ ጋረድ ክንፉ በጦር ወግተው ገደሏቸው። ከዚያም እንግሊዛዊ አማካሪያቸው፤ ጆን ቤል ሞተ። ከዚህ በኋላ የነበረው ምስቅልቅል በቃላት ብቻ ተገልጾ የሚያልፍ አይደለም። ካልተዘጋጁበት በቀር፤ የአበቅቴው ሰኔ እና ሰኞ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ተከታታይ የችግር ቸነፈሮች አልፈዋል። 1863 በአሜሪካ ደግሞ የርስ በርስ ጦርነት የተጀመረበት፤ ሲሆን፤ በጦርነቱም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ሞተዋል። 1868 አጼ ቴዎድሮስ April 17, 1868 (1860 ዓ.ም) ህይወታቸውን ያጠፉበት አመት፤ ሰኔ እና ሰኞ የገጠመበት አመት ነበር። 1891 – ከአንድ አበቅቴ ወይም ከ11 አመት በኋላ የሚመጣው የሰኔ እና ሰኞ ግጥምጥሞሽ አስፈሪ ነው። ከአበቅቴው በኋላ ጥንቃቄ እና ዝግጁነት ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነ ግን በሁሉም የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደምናውየው አይነት የረሃብ እና የበሽታ ውሽንፍር ይከሰታል። በዚህ ዘመን በቂ ዝግጅት እና ጥንቃቄ ባለመደረጉ በአገሪቱ ታይቶ የማይታወቅ አስከፊ ነገር ሆነ። ይህ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ “ክፉ ዘመን” በመባል ይታወቃል። በሰሜን ከአክለ ጉዛይ ጀምሮ ቤጌምድርን ጨምሮ፤ ሸዋ እና ሃረር… እንዲሁም እስከ ደቡብ ድረስ የዘለቀ ረሃብ እና በሽታ ተስፋፋ። የአምበጣ መንጋ ሳር ቅጠሉን፣ ጥሬ እህሉን ሁሉ ጨረሰ። በዚህ እንዳይበቃ… የኮሌራ፣ የተስቦ እና የፈንጣጣ በሽታ ህዝቡን እያሰቃየ ጨረሰው። በዚህ ምክንያት የአጼ ምኒልክ የንግሥና በአል ጭምር ለሌላ ጊዜ ተዛወረ።

About