@keri.traditional: 🛑🫑 የጉበት በሽታ እንዳለብን የሚጠቁሙ 13 ምልክቶች! | 13 Symptoms of Liver Disease! 🦠 ጉበታችን በሰውነታችን ውስጥ መርዛማ ነገሮችን ማስወገድ፣ ለምግብ መፈጨት የሚረዳውን ሀሞት (Bile) ማምረት፣ እና ሌሎችንም በመቶዎች የሚቆጠሩ ወሳኝ ተግባራትን ያከናውናል። ይሁን እንጂ አብዛኛዎቹ የጉበት በሽታዎች በሂደትና ቀስ በቀስ የሚመጡ በመሆናቸው፤ ጉበታችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት እስኪደርስ ድረስ ምልክቶቹ ላይታዩ ይችላሉ ✅🫑 ልናውቃቸው የሚገቡ 13 የጉበት ህመም ምልክቶች! | 13 Symptoms of Liver Disease You Should Know! 🦠 ―――――――――――――――――――――――――― 👉👉 ለራሳችንም ሆነ ለምንወደው ሰው ጤንነት ስንል ማወቅ የሚገቡን 13 የጉበት ህመም ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦ 1️⃣. የተለያዩ በሽታዎች፣ ግን ተመሳሳይ ምልክቶች! | Different Diseases, Similar Symptoms! በአጠቃላይ ከ100 (ከመቶ) በላይ የተለያዩ የጉበት በሽታዎች አሉ። ለእነዚህ በሽታዎች መከሰት ምክንያቶቹ ወይም መንስኤዎቹ የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ለምሳሌ፦ 🍋 የቫይረስ ወይም የባክቴሪያ ኢንፌክሽን 🍏 የአልኮል መጠጥ ከመጠን በላይ መውሰድ 🍊 አንዳንድ መድኃኒቶች 🍅 ህገ-ወጥ ወይም (አደንዘዥ) ዕጾች 🍈 መርዛማ ንጥረ-ነገሮች 🥭 ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና 🍎 የጉበት ካንሰር ይጠቀሳሉ። በሽታዎቹ እና መንስኤዎቻቸው የተለያዩ ቢሆኑም፤ አብዛኛዎቹ የጉበት ህመሞች ጉበትን የሚጎዱበት መንገድ ተመሳሳይ ነው። በዚህም ምክንያት የሚያሳዩዋቸው ምልክቶች ይመሳሰላሉ። 2️⃣. ድንገተኛ (Acute) እና የቆየ ወይም ሥር የሰደደ (Chronic) የጉበት ጉዳት! | Acute vs. Chronic! አንዳንድ ጊዜ የጉበት ጉዳት ወይም ሙሉ በሙሉ ሥራ ማቆም እና ተያያዥ ምልክቶች “በድንገት” (ፈጣን በሆነ መንገድ) ሊከሰቱ ይችላሉ። ይህ የሚሆነው ለምሳሌ፦ የአሲታሚኖፊን (Acetaminophen) መድኃኒትን ወይም ሌሎች የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ከልክ በላይ ሲወሰዱ፣ አንዳንድ የባህል መድኃኒቶች፣ ቫይረሶች፣ እና የሰውነት በሽታ መከላከል አቅም ራሱን በራሱ የሚያጠቃበት (Autoimmune) በሽታ ሲኖር ነው። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የጉበት በሽታ እና የጉበት ስራ ማቆም “ሥር የሰደደ” ወይም “ክሮኒክ” ነው። ይህም ማለት በሂደት፣ ረጅም ጊዜ ወስዶ ጉበትን ቀስ በቀስ እየጎዳ የሚመጣ በመሆኑ ምልክቶቹም ቀስ እያሉ ይታያሉ። 3️⃣. የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶች! | Early Liver Disease Symptoms የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶችን ላናስተውላቸው እንችላለን። ብናስተውላቸው እንኳ ምልክቶቹ ከምን እንደመጡ ለማወቅ ይከብዳል። ምክንያቱም የመጀመሪያዎቹ የጉበት ህመም ምልክቶች ግልጽ ያልሆኑና ከተራ ህመም ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው። ለምሳሌ፦ 🍓 የሆድ ህመም 🍓 የምግብ ፍላጎት መዘጋት ወይም መቀነስ 🍓 ከፍተኛ የድካም ስሜት ወይም የጉልበት (አቅም) ማጣት 🍓 ተቅማጥ። በቃ ዝም ብሎ ሰውነታችንን ህመም ህመም ሊለው ይችላል፤ ግን ለምን እንደሆነና ምክንያቱን በግልጽ ላናውቅ እንችላለን። 4️⃣. የቆዳ ወይም የዓይን ቢጫ መሆን (ጃውንዲስ)! | Yellow Skin or Eyes (Jaundice) ጉበታችን ይበልጥ እየተጎዳ ሲሄድ ግልጽ የሆኑ ምልክቶችን ማየት እንጀምራለን። ቆዳችን እንዲሁም የዓይናችን ነጩ ክፍል ቢጫ ሊሆን ይችላል። ዶክተሮች ይህንን "ጃውንዲስ" (Jaundice) ወይም (በአገራችን አጠራር የወፍ በሽታ) ይሉታል። ይህ የሚሆነው ከቀይ የደም ሴሎቻችን የሚወጣው "ቢሊሩቢን" (Bilirubin) የተባለው ቢጫ ንጥረ-ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሲከማች ነው። በተለመደው መደበኛ ሁኔታ ጉበታችን ይህንን ፈሳሽ አጣርቶ ያስወግደው ነበር። ነገር ግን ጉበት ሲጎዳ ሥራውን በአግባቡ መወጣት ስለማይችል፤ ቢጫው ፈሳሽ ንጥረ-ነገር መጠኑ በሰውነታችን ውስጥ ይበዛል ወይም ይጨምራል። 5️⃣. የቆዳ ማሳከክ! | Itchy Skin! የቆየ የጉበት ችግር ካለብዎት ከፍተኛ የቆዳ ማሳከክ ሊያጋጥምዎት ይችላል። ይህ የሚሆነው በቆዳዎ ላይ ምንም ዓይነት ሽፍታ ወይም አለርጂ ወይም ሌላ ምልክት ሳይኖር ነው። ማሳከኩ በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ እንቅልፍ ሊነሳዎት ይችላል፤ ቢያኩትም እንኳ ስሜቱ (ማሳከኩ) አይጠፋም ወይም አይተውም። ይህ ካጋጠምዎት ሊረዳዎ የሚችል መድኃኒት እንዲያዝልዎ ዶክተርዎን ወይም ሐኪምዎን ያማክሩ። 6️⃣. የሆድ ማበጥ/ፈሳሽ መቋጠር (አሳይትስ)! | Swollen Belly (Ascites)! ጉበታችን ላይ ጠባሳ ሲፈጠር (ሲሮሲስ) (Cirrhosis)፤ ወደ ጉበት የሚሄደውን የደም ዝውውር ስለሚዘጋው በዙሪያው ባሉ የደም ስሮች ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል። ይህ ደግሞ ፈሳሽ እንዲፈስና በሆድ ውስጥ እንዲከማች ያደርጋል። ፈሳሹ ጥቂት ወይም በጣም ብዙ ሊሆን ይችላል። ሆድዎ በጣም ትልቅ ሊሆንና እምብርትዎ ወደ ውጭ ሊወጣ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ይህ ፈሳሽ በባክቴሪያ ሊበከልና ኢንፌክሽን ሊያመጣ ስለሚችል የአንቲባዮቲክ መድኃኒት ያስፈልገዋል። ፈሳሹ በጣም ከበዛ ደግሞ በቱቦ አማካኝነት ሊፈስ ወይም ሊቀዳ ይችላል። መረጃው ሌሎች እዲደርስ ላይክ ሸር ኮፒ ሊክ አርጉ🙏

Kሪ organic 🌿☘️
Kሪ organic 🌿☘️
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 13 June 2026 10:29:01 GMT
336987
4349
62
369

Music

Download

Comments

amare.dasale
Amare Dasale :
fetari tebkegn
2026-08-09 08:59:57
0
shemu.seid
AYZAK :
ያረቢ ከአስከፊ በሽታ ከአስከፊ ችግር እና ከልብ ሰባሪ ሃዘን አንተ ጠብቀን አሚን
2026-08-08 19:24:34
6
sebah009
umusebah :
ጣፋጭ አዘዉትሮ መብላት ጥሩ ነዉ ይባላልዐእዉነት ነዉ?
2026-08-07 20:38:15
2
user2423029348550
سنرتى :
ያረብ አላህየ አንተ ጠብቀን
2026-08-08 06:45:10
5
oumu.hira
Merema nuru hira welo desi :
b medanitu mendnew
2026-08-08 06:42:28
2
user8295395039577
Tg Getachewu Eshete :
mn ayinet
2026-08-08 04:43:18
1
ekram9528
ሁሉን ቻይ :
ታው ችግር አትጥሩብን ደህናነን
2026-08-08 13:55:31
1
yilkal062
ዝምታ ወርቅነዉ :
ተጨማሪዉን እንፈልጋለን
2026-08-08 10:56:13
1
eyoursalm.nugusse
Eyoursalm Nugusse :
መድሃኔቱ ምን ድነው
2026-06-16 07:48:09
5
fx56445
☬ˢᏞᎪᎶfx☬ :
hepatomegale tebeye neber yegelale?aberaruleye bemareyam lijoch aluiye yeteshale hekemena edalageye yemeredaye yeleme🥺🥺🥺🥺
2026-08-08 00:26:03
1
user61574214256885
ቸላል :
Allah yitebiken
2026-08-09 09:48:36
0
user3681400968237
user3681400968237 :
መፍቴሄ ብቀመጥ
2026-07-18 01:45:33
1
nuniyatnu
❷Nuniyat❼ :
አይኔ ቢጫ ነው ግን ሌላው ምልክት የለብኝም
2026-08-09 12:34:34
0
1b2e3h
Behh :
yabesha medanit bewesd cheger alew
2026-07-18 15:42:22
1
muherllb
Muher€§ :
😳😳 yallah
2026-06-14 09:52:52
4
user96038679148455
አወል መሀመድ :
መደሃኒቱንም በዘዉ ብትነግሩን
2026-08-08 14:25:01
0
fruit191919
fruit 🍓 love 444🦋 :
fetary yetebken 🙏🙏
2026-08-09 13:22:31
0
heylsh2
Heylsh :
ምንድን ነው መድሀኒቱ
2026-08-08 17:41:12
0
kusse.aylete
kusse aylete :
አልበዛሞ
2026-06-23 11:24:52
2
123adona0
ADONAY ade MAMA :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰❤️❤️❤️❤️❤️❤️🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-08 17:50:47
0
sheme860
Shime862 :
ysanba areje blwegn nbr bfit ahulayi shto seshtgn yamgn mn tlgnalhe De
2026-07-19 22:43:24
1
adu34597
@adu :
እኔን ወፊ አሞኝ ሜዲካል ህክምና አለው
2026-06-13 16:47:38
4
wbab87
Abushe :
መፍትሔውስ ምንድነው ምልክቱ ላለበት
2026-07-09 19:24:48
1
user7775872093411
ye mariyam liji :
medant.ale
2026-07-25 09:20:45
3
sonisoni7912
M❤️B :
😢😢😢
2026-08-07 22:45:22
1
To see more videos from user @keri.traditional, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About