@zelealem.official: 🌱ደግነት ከልብ ውስጥ ያለ ርህራሄና ያለማቋረጥ ራስን ለመስጠት መፍቀድ ነው።ደግነትህን ለማሳየት የኔ ጥረት ትንሽ ናት አትበል፡፡ የቻልከውን ካደረክ ያንተ ትንሽ የብርሃን ጭላጭል ትህትና ልክ እንደሻማ ሌሎች ያንተን ብርሃን የሚቀበሉ እልፎች አሉ።የትም ሁን ማንም ሁን ያቅምህን በጎ ለማድረግ ግን አትስነፍ።ደግነት እንደ ጥሩ ሽቶ ነው ከአንዱ ተነስቶ ወደ አንዱ ይጋባል።ለመስጠት የልብ ቅንነት እንጅ የግድ ሃብታም መሆን አይጠበቅብህም፡፡ ደግሞ ማንም ሰው ልስጥ ካለ የሚሰጠው አያጣም፡፡ 🌱ደግነት የገንዘብ ጉዳይ አይደለም።ደግነት በያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ያለ ርህራሄ ነው።ለወላጅ ከመታዘዝ፣ለቤተሰብ መልካም ልጅ ከመሆን ይጀምራል።ደግነት ፍቅረኛን ከመረዳት ፣ፍቅረኛን ከማክበር፣ከመንከባከብ፣ለፍቅረኛ ከመታመን፣ለአፍቃሪ ትሁት ከመሆን፣ቅን ከመሆን፣አዛኝ ከመሆን፣ታማኝ ከመሆን፣አርዐያ ከመሆን ይጀምራል።ደግነት ለጓደኛ ጥሩ ሰው ከመሆን ይጀምራል።እያንዳንዱ ሰው በዙሪያው ላለ ሰው ደግና መልካም ሰው ቢሆን አለም ገነት ትሆን ነበር። 🌱ደግነት ማለት ሰጥቶ መቀበል ሳይሆን ሰጥቶ ድጋሜ መስጠት እንጂ ለመቀበል መስጠት አይደለም። ደግነትን ምረጥ ደግነት ልብ ውስጥ የሚመነጭ ሀዘኔታና መራራት እንጂ በማስመሠል የሚደረግ ተውኔት አደለም ፤ ደግነት ደግ መሆን ነው።ደግ ማለት በሁኔታዎች ሁሉ እኔ ብሆንስ ብሎ ማሠብ፤ እኔ በሱ /በሷ ቦታ ብሆን ብሎ ማዘን ነው።ደግነት ስለ ራስ ብቻ ሳይሆን ስለሌሎች ማሰብ ነው ። 🌱በመልካምነት ያተረፈ እንጂ ያጎደለ የለም፤አይኖርምም! _ መልካምነት ትርፉ ጊዚያዊ ሳይሆን ዘላቂ ነው።አናንተ የደግነት ምሳሌዎች ያለቀሰ እንባ አባሾች፣የተራበ አጉራሾች፣የታረዘ አልባሾች፣ተስፋ የቆረጠ አፅናኞች፣ሚስኪኖችን ፣ የቲሞችን በቻላችሁት የምትፈቅዱ፣የምታስቡ፣የምትረዱ፣የምጠይቁና የደስታቸው ምክንያት ለሆናችሁ ሁሉ አናንተንም ፈጣሪ በማያልቀው ቸርነቱ ያስደስታችሁ❣️ 🤌🏾ሁሉም ሰው ይማርበት ዘንድ ሸር አድርጉት🫶🏽 እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን🙏 እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው።

ስለ እናት
ስለ እናት
Open In TikTok:
Region: US
Saturday 13 June 2026 19:31:37 GMT
6493
450
17
54

Music

Download

Comments

user6z7b6kdfrn
𝙝𝙡𝙞𝙣𝙖💙 :
እኔ እዚ ቤት ስገባ የሚሰማኝ ስሜት💔 ወንድሜ እንዳንተ ያሉ ያበዛልን🥰
2026-06-14 03:20:01
1
b125544.ethiopian
b125544 ethiopian tik tok prot :
አሜንንን
2026-06-14 05:48:35
0
heyewet.yiketlal
Ruhama Yemariam Lij :
exactly
2026-06-13 19:36:16
0
mama426813
Z💤💐💐 :
እውነትነው።
2026-06-14 02:57:22
0
giru089
ጓል ራያ ራዩማ :
ትክክል
2026-06-14 01:38:17
0
amalge.degil
አግዚአብሔረ እረኛየ ነው✝️⛪️🙏 :
ትክክል🙏🙏🙏🥰🥰
2026-06-13 23:48:26
0
joseph35309
musa :
hallelujah
2026-06-13 19:33:58
0
haymi228
ላያስችል አይሰጥም :
እናተ ባለደግ ልቦች አምላክ ከፍታችሁን ያሳየን🥰
2026-06-14 02:53:58
0
astermekonen0
Astu ydgl maryme lej💒✝️ 🆘️ :
yes🙏
2026-06-13 19:37:16
0
haymanotmesfn1
haymi2116121923 :
አሜን
2026-06-13 21:21:34
0
yewbdar1653
Yewbdar 🦋🦅 :
Amen❤️🙏
2026-06-13 19:52:56
0
user454861509
Abrsh🇪🇹🇨🇦 :
እውነት ነው ። ግን ሐበሻ አንተን እንደፈለገ ሲያደርግህ ብቻ ነው ሰላንተ ሰላንተ ደግነት የሚያወራው ኖ ያልክ ቀን ስምክን ማጥፋት ይጀምራል
2026-06-13 20:10:04
4
azeb010
Azeb🦋 :
🥰❤️😍
2026-06-13 20:30:36
0
penk057
ቀመር🌙 :
🥰🥰🥰
2026-06-13 19:40:21
0
etayzer2
Etayzer✨🦋 :
🥰🥰
2026-06-13 19:34:58
0
abegaloveata3
እግዚአብሔር ይመስገን! :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-14 05:26:26
0
To see more videos from user @zelealem.official, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About