@sulamaties_media: በጣም ደስ ይላል። ድንበርና ዘመን ያልገደበው የዓድዋ ድል፦ የፔንስልቬንያ ምክርቤት ያሳለፈው ውሳኔ የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዳግም ከፍ አድርጓል! የአሜሪካው የፔንሲልቫኒያ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የዓድዋ ድል መታሰቢያን እውቅና የሚሰጥና ማርች 2 የድል በዓሉ በፔንስልቬንያ እንዲከበር የሚፈቀድ H.R 441 የሚል ስያሜ የተሰጠውን የውሳኔ ሀሳብ አጸደቀ። ምክር ቤቱ ባስተላለፈው የውሳኔ ሀሳብ ኢትዮጵያውያን በወቅቱ አፍሪካን ለመቀራመት ሲደረግ የነበረውን የኮሎኒ እንቅስቃሴን በጋራ በመሆን በማሸነፍ ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የአፍሪካ ሀገር መሆን መቻሏን በከፍተኛ አድናቆት በማውሳት፣ ዓድዋ የዓለም አቀፍ የነጻነት፣ የክብር እና የአንድነት ምልክት መሆኑን አንስተዋል። የውሳኔ ሀሳቡ አኩሪ የሆነው የዓድዋ መታሰቢያን ብቻ ሳይሆን በፔንስልቬንያ እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በጤና፣ በንግድ፣ በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር፣ በትምህርት እና በአገልግሎት ሰጪ ኢንዱስትሪ ይበልጥ እንዲጠናከር እንደሚሰራ አረጋግጧል። ከዚህ ምን አይነት ትምህርት እንቀስማለን? #አድዋ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር #habeshatiktok #አድዋ💚💛❤💪 #fcypシ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
Region: ET
Saturday 13 June 2026 19:37:43 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @sulamaties_media, please go to the Tikwm
homepage.