@amsalu.c: እኔም እኔ ሆኘ ፡ ጦቢያ ተወልጀ ፤ የጦቢያ ዕጣ ሆኖ ፡ ሁሉን ማለት በጀ ፤ ከትናንት እስከ አሁን ፡ ምናልባትም ነገ ፤ ሀቁ እንደዚህ ቢሆን ፡ ሕዝብን ያልታደገ ፤ ጦቢያ ስትወለድ ፡ ኢትዮጵያዊ ሆነህ ፤ ከሞት የመረረ ፡ አንድ ዕዳ አለብህ ፤ ኃላፊነት ይዞህ ፡ ሀገር ወገን ስትመርጥ ፤ ክፉ አገዛዝን ፡ ልትታገል በዓመጥ ፤ አንተን የሚከተል ፡ አሳር መከራ አለ ፤ ተስፋህን የሚቆርጥ ፡ ከሾተል የሳለ ። ምን አገባኝ ብለህ ፡ ለራሴ ልሁን ካልክ ፤ ሕሊናህን መሸጥ ፡ መጣላትም ከአምላክ ፤ ግድ ይሆንብሃል ፡ የሕይዎት ዘመን ፍርድ ፤ እስክትባል ሞተ ፡ መቃብር እስክትወርድ ። እናማ! ፡ እናማ ሀገሬ ፤ በምድር ብቻ ሳይሆን ፡ የሰማዩም ክብሬ ፤ በነፍስ የምወርስሽ ፡ የጽድቅ ዐፅመ ርስቴ ፤ ከአምላክ የታደልኩሽ ፡ ስጦታ መክሊቴ ፤ ያንች በመሆኔ ፡ ለአምላክ አኮቴቴ ፤ የሥጋና የነፍስ ፡ ኑሮየ ሕይዎቴ ፤ የቅዱሳን ዓሥራት ፡ የድል አክሊላቸው ፤ የሚጋደሉላት ፡ በነፍስ በሥጋቸው ፤ የጀግና መከራ ፡ የእነ ቴዎድሮስ ፍዳ ፤ ቁም ስቅል ፈተና ፡ ደንታቢስ ባለ ዕዳ ፤ የእሾህ አሜኬሎች ፡ የቅጥረኞች ምንዳ ፤ ለሆኑባት ጠላት ፡ ለሆኑባት ባንዳ ። እናም ለዚህ ነበር ፡ በከንቱ የቀረሁት ፤ ሀገር ላንችው ስል ነው ፡ ያላልኩ ጎጆና ሚስት ፤ ሀገርና ሃይማኖት ፡ ከእናት አባት ጋር ፤ እናም ለራስ ሕይዎት ፡ ማሰብ ብሎ ነገር ፤ ከቶ አይታሰብም ፡ መምረጥ ግድ ይሆናል ፤ ከሀገርና ሃይማኖት ፡ ከራስ ከወላጅ መሀል ። እንዴት እንደሁ ሳላውቅ ፡ መቸ እንደመረጥኩኝ ፤ መቸ አወዳድሬ ፡ መቸ እንደወሰንኩኝ ፤ ለካ እምነት ሀገሬን ፡ መርጫቸው ኖሯል ፤ ቀን ላወጣላቸው ፡ ላበቃቸው ለድል ፤ ወላጅና እራሴን ፡ ጨርሶ እረስቸ ፤ ሀገር ብየ ቀረሁ ፡ ቢጤዎች አጥቸ ፤ እምነት ብየ ቀረሁ ፡ በመንጋው ተትቸ ፤ ውድ እናት አባቴን ፡ ሳላውቅ እረድቸ ። ምን ነበረ ቢቻል ፡ ሀገርን ወላጅን ፤ እኔ እራሴን እና ፡ አንዲት ሃይማኖትን ፤ እኩል መውደድ ቢቻል ፡ እኩልም ማገልገል ? መምረጥ ግድ ባይሆን ፡ አንድ ወዶ አንድ መጣል ፤ ሀገሬን እምነቴን ፡ ሲባል ጫር በአገዛዝ ፤ ምን ነበረ ባይኖር ፡ ቢቻል ሁሉን መያዝ ። የእኔ የሞት ሞቴ ፡ ኪሳራ ወዮታ ፤ ሳላይ ከቀረሁ ነው ፡ ሀገሬ ተነሥታ ፤ ሳላይ ከቀረሁ ነው ፡ ሕዝቧ እንባው ታብሶ ፤ ቤተክርስቲያን ላይም ፡ እሾሁ ተነቅሶ ። ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ሐምሌ 4, 2016ዓ.ም. አዲስ አበባ #ethiopian_tik_tok #tiktokviral #orthodox #tewahdo #amharatiktok💚💛❤️

Amsalu Gebrekidan Argaw
Amsalu Gebrekidan Argaw
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 14 June 2026 10:29:50 GMT
4173
268
11
23

Music

Download

Comments

frehiowtaddis
hiwot :
መልካም ልደት
2026-06-20 06:12:50
1
bekanchin
እስከ ማዕዜኑ ትረስዓነ እግዚኦ :
HBD to you God bless you forever
2026-06-15 07:47:16
1
danewtdanewt
ዳና የአፄዎቹ ዘር👑🇲🇱 :
🥰🥰🥰
2026-06-14 12:38:54
1
elenimamo460
elenimamo :
መልካም ልደት
2026-07-09 14:02:56
0
user6385096547921kaki
kaki :
🥰🥰🥰
2026-06-14 11:05:35
1
a09b10c
[ 𝗕𝗲𝗴𝗮𝘀𝗵𝗮𝘄 - 𝟮𝟳 ] :
🥰🥰🥰🥰
2026-06-14 21:37:30
1
abrham.zebene
Abrham Zebene :
🥰🙏🙏🙏
2026-06-14 18:34:42
1
kassahune9
kassahun :
🥰🥰🥰
2026-07-09 04:57:32
0
seyoum.mengesha7
Seyoum Mengesha :
🥰🥰🥰🥰🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰🥰
2026-06-16 09:53:00
1
maryam.enate441
ማርያም እናቴ🍋🍋🍋🍋🍋🍋 :
🥰🥰🥰🙏🙏🙏
2026-06-14 10:34:41
1
To see more videos from user @amsalu.c, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About