@henokabdu7: በቡድን በመደራጀትና ጨለማን ተገን በማድረግ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። *** አዲስ አበባ፤ ሰኔ 07 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ራሺያ ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ተጠርጣሪዎቹ ጨለማን እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ከሌሊቱ 7 ሠዓት አካባቢ ለቴሌኮም አገልግሎት የሚውል ከመሬት ስር የተዘረጋ ኬብል በተለያዩ መቁረጫዎች በመቆራረጥ ይዘው ከአካባቢው ሊሰወሩ ሲሞክሩ በስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላትና የአካባቢ ጥበቃዎች ትብብር ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን በልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የመከኒሳ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል። ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተገቢውን ምርመራ የማስፋት ተግባር እያከናወነ መሆኑን ገልጾ በቀጣይ ክስ እንደሚያስመሠርትም ጠቁሟል። በመሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ሀገርን ለከፍተኛ ኪሳራ የሚዳርግ ተግባር በመሆኑ ህብረተሰቡ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ሲመለከት እንደተለመደው በአካባቢው ለሚገኝ የጸጥታ ኃይል ጥቆማ መስጠት እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልእክቱን አስተላልፏል። * ዘገባ፦ም/ሳጅን ፍፁም በቀለ

Inspector Henok Abdu
Inspector Henok Abdu
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 14 June 2026 19:23:42 GMT
429
27
1
6

Music

Download

Comments

jemalhassen09
Jemal Hassen yassin :
👍👍👍
2026-06-14 19:28:40
1
To see more videos from user @henokabdu7, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About