@mokannn: ዘሪሁን ተዝናኑ እንደፃፈው:- ተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ ( ዳኒ ፂሞ ) #በሰይፉ_ሾው Share ሼር በማድረግ ዳኒን ቅን ሰዎች እንዲያግዙት ተባበሩት 🙏 ★ ከፊልምና ቴአትር ስራ በቃኝ ብዬ የተውኩት ስለራበኝ ነው። ★ የኛ ስራ አንድ ጊዜ ይመጣና ፤ የሆነ ወራት ደግሞ ይጠፋል። ★ ወደ ጅማ ልሄድ ነበር። ቴዎድሮስ ተስፋዬ አንድ ስራ ይዞልኝ መጣ። ★ፂም የሌለው ሌላ ካራክተር ቢመጣ ፂሜን አንስቼው እሰራለሁ። ፂሜን ግን በጣም እወደዋለሁ። ★ #ልጄስ ተከታታይ ድራማ በአለም አቀፍ ደረጃ ታጭቶ ተሸልሟል። ★ ጀርባዬን ከ20 ዓመት በፊት ሰርጀሪ ተሰርቼው የህክምና ስህተት ተፈፅሞብኛል። ★ ሰርጀሪውን አበላሽተው ስለሰሩኝ ቤት ከተቀመጥኩኝ 1 ዓመት ከ10 ወር ሆነኝ። አንድ ቴአትር ግን ማስታገሻ እየወሰድኩኝ ነው የምሰራው። ★ ከህንድ የመጡ ሀኪሞች እኛ ጋር ና እንሰራሃለን ብለውኛል። ★ ወታደር ቤት ገብቼ ሳይመቸኝ ወጣሁ። ከወታደር ቤት ወጥቼ ወደትውልድ ሀገሬ ጅማ ድረስ በእግሬ ተጉዣለሁ። ★ ቴአትር መስራት የጀመርኩት ጅማ ውስጥ የምናገለግልበት ቤ/ክርስቲያን ነው። ★ ከዚህ በፊት ብየዳ ፣ ሸክም ( ወዛደርነት ) እና የመንገድ አስፓልት ስራ ሰርቻለሁ። ★ በዚህ ሙያ ስትኖር ይከብድሃል። ★ የእኛ ስራ መድረክ ላይ ተጨብጭቦልህ በእግርህ ወደ ቤትህ ትገባለህ። ★ ከጀርባ ህመሜ ጋር ተያይዞ በታክሲ መሄድ አልችልም። በራይድ እየተመላለስኩኝ ነው የምሰራው። ★ እንኳን ሰራሁት ብዬ የምኮራበት ስራ ልጄስ ተከታታይ ድራማ ነው። ★ ከቴአትር እጅግ ወድጄው የሰራሁት ደግሞ ሲራኖ ቴአትር ነው። ★ ከ10 በላይ ቴአትር ሰርቻለሁ። ፊልሞች ደግሞ ወደ 20 ገደማ ሰርቻለሁ። ★ እኔ እስካሁን አልሰራሁም ወይ እንድል ያደረገኝ ልጄስ ድራማ ነው። ★ ያንን ሁሉ ዓመት ሰርቼ በልጄስ ነው የታወቅሁት። ★ ስፖርት መስራት በጣም እወዳለሁ። ★ አብዛኛውን ጊዜ እኩይ ገፀ - ባህሪ ወክዬ ነው የምጫወተው። ★ ግሪክ ሀገር ሄደን ቴአትር ሰርተን ተመልሰናል። ★ በልጅነቴ ጭምት ነበርኩኝ። ብቸኛ ነበርኩኝ። ልጅነቴን ብዙም አልወደውም። ተወዳጅ የልጅነት ጊዜ የለኝም። ጓደኞቼ አይወዱኝም ነበር። ★ከተፈሪ አለሙ ጋር መስራት በጣም ደስ ይላል። ★ ካሉት ተዋንያኖች ውስጥ ከማንም ጋር ብሰራም ደስ ይለኛል። ★ ስታንት ማን የሚያስፈልጋቸውን ከበድ ያሉ ሲኖችን ራሴ ነኝ የምሰራቸው። ሰኔ 15 በብሔራዊ ቴአትር ቤት የሚታየውን ንጉስ አርማ ቴአትር ሙሉ ገቢው ለእኔ እንዲሰጠኝ ዝግጅት ለማድረግ የምትሯሯጡ የምታውቁኝም ፣ የማታውቁኝም በሙሉ አመሰግናችኋለሁ። በተለየ የማመሰግናት ሰናይት የምትባል አንዲት ወጣት ልጅ አለች። ሳትሰለች ስታስታምመኝ የነበረች ልጅ ናት። አመሰግናታለሁ። አርቲስት ሚኪያስ መሐመድ ለዳኒ ፂሞ 100,000.00 ( መቶ ሺህ ብር ) ሰጥቶታል። ሚኪ ባለታክሲው ይመችህ ✌ በተለያዩ የትወና ጥበቡ ያስደመመን ተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ ( ዳኒ ፂሞን ) ለመርዳት የምትፈልጉ ፦ 1000343965037 CBE ዳንኤል አሸናፊ Share ሼር በማድረግም ምርጡን ተዋናይ ሰው እንዲያግዘው እናድርግ 🙏 Dani Tsimo ተዋናይ ዳኒኤል አሸናፊ ፦ ለሰጠኸን ምርጥ ስራዎች እናመሰግናን። ከህመምህ አገግመህ ወደሙሉ ጤንነትህ እንድትመለስ ፈጣሪ ይርዳህ ! አክባሪህና አድናቂህ ዘሪሁን ተዝናኑ ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

Moka (Artist)
Moka (Artist)
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 15 June 2026 02:08:56 GMT
13055
157
2
63

Music

Download

Comments

abera_alemu
Abera :
እግዚአብሔር ይማረው ትልቅ ባለሙያ ነው
2026-06-15 09:16:57
2
tig19893
tig😎 :
እግዚአብሔር ይማርህ
2026-06-15 04:37:26
0
To see more videos from user @mokannn, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About