@engineerlemman: ማህበራዊ ሚዲያውን ያጥለቀለቀው የሽሽግ ቸኮል ዘፈን...🎤🎵🎧 ህዝቡ በተለይ ወጣቱ እጅግ በስሜት እየሰማው ይገኛል... ለምን ⁉️ "መሄደ ነው እንጂ.... ትንሽ ያበረደኝ... ኗሪ ሰው በሆንኩኝ እንዴት በነደደኝ" ይህ ስንኝ ጥልቅ የሆነ ፍልስፍና አለው፣ ኑሯችንን፣ ሃዘናችንና እውነታን ግልጽ አርጎ ያሳያል፣ በሽሽግ ቸኮል ድምጽና በባህላዊው ማሲንቆ ደግሞ ልዩ አርጎታል። "መሄደ ነው እንጂ ትንሽ ያበረደኝ" እዚህ ጋር "መሄድ" የሚለው ቃል የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ ኗሪ አለመሆኑን ያመለክታል። ድምጻዊቷ በዚህ ምድር ላይ የሚደርሰው በደል፣ ክፋት ወይም መከራ የጋለ እሳት ሆኖ እያለ፣ ቁጭቷን ያበረደላት ነገር ቢኖር "እኔም እኮ እዚህ ለዘላለም አልኖርም፣ ሄጅ ነኝ" የሚለው የእውነት ሃሳብ ነው። "ኗሪ ሰው በሆንኩኝ እንዴት በነደደኝ" በዚህች ምድር ላይ ለዘላለም የምኖር ቋሚ ሰው በሆንኩኝ ኖሮማ፣ የሚደርሰው ግፍ እና መከራ ያንገበግበኝ፣ እሳቱ ያቃጥለኝ ነበር ነገር ግን አለም አላፊ በመሆኗ ትንሽም ቢሆን ትጽናናለች...😢 ወጣቱ ዛሬ ለምን መረጠው...⁉️ በአሁኑ ወቅት ወጣቱ ትውልድ በኑሮ ውድነት፣ በሥራ አጥነት፣ በሰላም እጥረት እና በማህበራዊ አለመረጋጋት ግራ ተጋብቷል። በዙሪያው የሚያየው በደል፣ ግፍ እና የፍትህ መጓደል ልቡን ያናድደዋል። ይህ ስንኝ ደግሞ ያንን ውስጣዊ ቁጭት እና እልህ በቀጥታ ይገልጽለታል። ታዲያ ይህ ያለንበት ሁኔታ መቀየሩ ማለፉ እንደማይቀር ሽሽግ በድንብ አርጋ በአራት መስመሮች ነግራን አልፋለች፣ እሷም ተጓዥ ስለነበረች ወድ ማይቀረው አቅንታለች... 🙏🏿 ሽሽግን በደንብ ያወቅናት ቴዲ አፍሮ "400 መቶ ፍቅር" በሚለው ዜማው ላይ አብረው መዝፈናቸው(Featuring) ነው ነፍሽን ይማረው በስራዎችሽ ይኸው ዛሬም ከኛ ጋር ነሽ...

Builder Lemman
Builder Lemman
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 15 June 2026 07:10:11 GMT
14606
396
2
16

Music

Download

Comments

369.com93
🤡secret🤡 :
@ ₹@/#@×+#4=₹/٪₹@#@@××#₹::÷₹÷@#%/@4÷×@@:₹++@×/=÷
2026-06-15 15:38:28
0
prretie.gabi
🤎 :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-06-15 15:09:11
0
To see more videos from user @engineerlemman, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About