@musictube369: ሰማኸኝ በለው 😔 ✍️ዛሬ እጅግ ልብ የሚነካና ለሀገራችን የሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ኪሳራ የሆነ አሳዛኝ ዜና ነው የሰማነው ላለፉት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግና ታሪክ በዜማዎቹ ጠብቆና አስፋፍቶ የቆየውና በቅፅል ስሙ «ሰሜ ባላገሩ» እየተባለ የሚጠራው አንጋፋው ድምፃዊ ሰማኸኝ በለው፣ በድንገት በገጠመው ህመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ሰምተናል እጅገሰ ያሳዝናል💔🥺 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ‹ቁምጣ የግሌ ነው› የሚለው ኩሩው ኢትዮጲያዊ እጅግ የምንወደው የባህል አምባሰደሩ ባህላዊ ሙዚቃን በመለው ኢትዮጲያ ካስተዋወቁ ግንባር ቀደም ሙዚቀኞች አንዱ የሆነው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) የተወለደው መስከረም 17 ቀን 1958 ዓም በባህር ዳር ወረዳ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ለሙዚቃ ድራማና ዳንስ ዝንባሌ ነበረው፡፡ ህዳር 11 ቀን 1978 ግሼ አባይ ኪነት የውዝዋዜ ባለሙያ ለመቅጠር ማስታወቂያ ሲያወጣ ሰሜ ሄዶ ይመዘገባል፤ በወቅቱ ግን ሰማኽኝ በባህር ዳር ዙሪያ አኢወማ ጽ/ቤት መዝገብ ቤት ውስጥ ይሰራ ነበር በ127 ብር ወርሃዊ ደሞዝ፤ ግሼ አባይ ኪነት ውስጥ ፈተና አልፎ ሲቀጠር ግን ደሞዙ 30 ብር ብቻ ነበር፡፡ ለሙያው የከፈልኩት ዋጋ ነው የሚለው ሰሜ ቁምጣ አድርጎ መድረክ ላይ በመውጣት በርካታ ባህላዊ ዘፈኖችን ተጫውቷል፡፡ በ1980ዎቹ አጋማሽ ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ የራሱን የባህል ምሽት ክለብና ባንድ በማቋቋም የሰራ ሲሆን ከአንጋፋው ድምፃዊ ይሁኔ በላይና አንሙት ጋር በመሆን በሰሩት ‹አንቱዬዋ› በተሰኘውና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀረበው ሙዚቃዊ ድራማ በስፋት ይታወቃል፡፡ በብዙዎች ዘንድ ከሚጫወጣቸው ዘፈኖች ከ50 በላይ የሚሆኑ ዘፈኖችን ዜማዎች መስራቱን የሚናገረው ሰማኸኝ በግሼ አባይ ኪነት ውስጥ ተወዛዋዥ ከነበረችው የአሁኑ ባለቤቱ ወ/ሮ ገበያነሽ አባተ ጋር ተጋብቶ አራት ልጆች አፍርቷል፡፡ ‹ሰሜ ባላገር› የሚለውን ቅፅል መጠሪያውን ማን እንዳወጣላት እንደማያስታውስ ለቁም ነገር መፅሄት የተናገረው ሰሜ ቁምጣ አድርጎ መድረክ ላይ ሲወጣና የባላገር ህብረተሰቡን ህይወት ለመወከል በመቻሉ ደስተኛ መሆኑን ገልጧል፡፡ ሰማኸኝ ከሙዚቃ ስራው በተጨማሪ ‹የባላገር ፍቅር› በተነሰኘውና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር በቀረበው የመድረክ ቴአትር ላይ ከእነ ቁምጣው በመሳተፍ ተውኗል፡፡ ከባህል ሙዚቃ ዘፋኞች ለባህሩ ቃኜና ለአሰፋ አባተ ልዩ አክብሮት ያለው ሰማኸኝ በ1990ዎቹ አጋማሽ ላይ የመኪና አደጋ ደርሶበት ነበር፡፡ ታዲያ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ሰኔ 8/2018 ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል፡💔 ሰማኸኝ በለው በኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ መድረክ ላይ ደማቅ አሻራ ካኖሩና ተለይተው ከሚታወቁ ታላላቅ የጥበብ ሰዎች አንዱ የነበረ ሲሆን፣ የገጠሩን ማኅበረሰብ ትውፊትና የሀገሪቱን የዘመናት ታሪክ የሚያንጸባርቁ በርካታ ተወዳጅ ሥራዎችን ለሕዝብ በማቅረብ ዘመናትን የተሻገረ ታማኝ አድናቂ ማፍራት የቻለ የባህል አምባሳደር ነበር። ሥራዎቹም የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ማንነት ሳይለቅና ከቀደመው ሥር ሳይነቀል ለወጣቱ ትውልድ እንዲተላለፍና በዘመናዊው የጥበብ ዓለም ውስጥ ሁልጊዜም ሕያው ሆኖ እንዲቀጥል በማድረግ ረገድ እጅግ የጎላ ሚና ነበራቸው። የዚህ ታላቅ ከያኒ ማረፍ በተሰማበት ወቅትም በርካታ አድናቂዎቹና የጥበብ ባልደረቦቹ ለሀገራዊ ቅርስና ለሙዚቃ ዕድገት ያበረከተውን በዋጋ የማይተመን አስተዋጽዖ በማስታወስ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘንና ክብር ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የፈጠራ ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለያዩ ቋንቋዎችን፣ ልማዶችንና የታሪክ ትረካዎችን ጠብቆ ለማቆየት እንደ ሰማኸኝ በለው ያሉ የጥበብ ሰዎች ያደረጉት ተጋድሎ ዘላለማዊ ሲሆን፣ ሰማኸኝ ባለትዳር እና የ4ልጆች አባት በቻላችን ስም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እነገለፅኩኝ ለወዳጅ ቤተሰቦቹ መፅናናት ተመኘሁ🙏 ነፍስ ይማር ! ሰማኸኝ በለው (1958-2018) 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #fyp #ሰማኸኝበለው #እንዴትነሽ #musictube369 #ethiopianmusic
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱️🅴
Region: ET
Monday 15 June 2026 19:30:52 GMT
Music
Download
Comments
it's me😎 :
it's so sad 💔
2026-06-16 04:44:05
26
@Wabii :
Rip
2026-06-20 13:02:44
0
ፋas :
🙏ሰሜ the legend
2026-06-16 06:28:31
8
Shamal :
😭😭😭😭😭uuffff
2026-06-18 18:23:00
1
➥𝗘𝗻𝗴𝗶𝗻𝗲𝗲𝗿➥♻️360🇸➥Ⓜ️⚡️ :
2026-06-16 14:19:38
3
berhanu🇪🇹21💞27🇪🇹 :
2026-06-16 10:53:34
5
Medi🦋 :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭ያሳዝናል
2026-06-16 20:33:43
2
Absalat cheru :
2026-06-17 17:58:42
1
ተጓዢ መንገደኛ :
ትዝታየ🥰🥰🥰
2026-06-16 14:40:47
4
BADGER_XAU_Fx :
seme legend 🥰🥰🥰
2026-06-16 13:56:36
1
Dj faya :
2026-06-16 17:21:43
2
YONI መርጡ :
nefse yemare wodema 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-17 13:48:47
1
ያየን የለም እንጅ ያላየነው የለም :
2026-06-16 07:13:54
2
Jason■♡♧w.r :
mottti kifffuuufifufifif
2026-06-16 10:15:53
1
Yaregal D :
ያሳዝናል ,RIP
2026-06-16 19:33:23
2
user6851766580080 :
ነብስ ይማር.....
2026-06-18 11:57:42
1
Mela Yene :
R.I.P
2026-06-16 21:22:24
1
M@tiktok :
so sorry heart touch ,for your death
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-06-16 15:52:14
1
sol ❤❤❤damotew :
ነፍስ ይማር ሰሜ
2026-06-16 17:29:16
1
asayetilahun5 :
RIP😭😭😭
2026-06-16 10:54:05
1
borex gizaw :
ስራዎቻቸውን እየተዉልን አለፉ 💔💔💔💔💔
2026-06-15 19:35:33
6
dggfg :
ነፍስ ይማር ወንድማችን
2026-06-16 16:52:35
1
kidi🍫 :
አይይ ሰሜ🥺😭😭😭
2026-06-16 12:21:54
1
Abrish@12 :
RIP
2026-06-16 11:49:19
1
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm
homepage.