@user7228529609712: Wooden Stage Scoreboard Set, 8 Colorful Pins Included, Wooden Board Game, Fun Table Games Accessories, Perfect for Family Game Night #boardgame #christmasgifts #pooltable #tabletopgames #playpensetup #holidaygames #ncaawalldecor #giftforboys #craftingwithkids #diamondpaintingtray

Home&DailyBoutique
Home&DailyBoutique
Open In TikTok:
Region: US
Tuesday 16 June 2026 02:07:37 GMT
17
0
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @user7228529609712, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

በሳል ሙዚቃ🙌🫡 1999 አ.ም በሙዚቃው ዘርፍ በአልበም ጥራት፣ይዘትም ሆነ ብዛት በርካታ የሙዚቃ አልበሞች ያገኘንበት ወቅት ነበር በወቅቱ የወጡ ስራዎች የጥራታቸው ከፍታ እድል ወይም ተራ ግጥምጥሞሽ አልነበረም የልፋት እና የላቀ ተስእጦ ውጤት ነው። ለሙዚቃ ወዳጅ እና አፍቃሪዎች ግን ጥሩ አጋጣሚ ነበር ። በዛ በ1999 አ.ም በጋ ወራት ከተለቀቁ አልበሞች መሀል የጥበቡ ወርቅዬ ሁለተኛ እንዲሁም የመጨረሻ አልበሙ የሆነው
በሳል ሙዚቃ🙌🫡 1999 አ.ም በሙዚቃው ዘርፍ በአልበም ጥራት፣ይዘትም ሆነ ብዛት በርካታ የሙዚቃ አልበሞች ያገኘንበት ወቅት ነበር በወቅቱ የወጡ ስራዎች የጥራታቸው ከፍታ እድል ወይም ተራ ግጥምጥሞሽ አልነበረም የልፋት እና የላቀ ተስእጦ ውጤት ነው። ለሙዚቃ ወዳጅ እና አፍቃሪዎች ግን ጥሩ አጋጣሚ ነበር ። በዛ በ1999 አ.ም በጋ ወራት ከተለቀቁ አልበሞች መሀል የጥበቡ ወርቅዬ ሁለተኛ እንዲሁም የመጨረሻ አልበሙ የሆነው "አላማርርም" የተሰኘው አልበም አንዱ ነው ። የአልበሙ መጠሪያ የሆነው "አላማርርም" ሙዚቃ መልእክቱ እንዲህ ያለ ነው ። የአግኝቶ ማጣትን ክብደት እና ህመም በማህበረሰባችን የጋራ ስሜት ከምንረዳቸው እና ተስማምተን ከምንጋራቸው ሀቆች አንዱ የአግኝቶ ማጣትን ህመም ነው ።ታዲያ በዚህ አላማርርም ሙዚቃ ላይ የተሳለውም ገፀ-ሰብ አግኝቶ ያጣ ሰው ነው ግና አጣሁኝ ብሎ የሚያማርር ሰው አይደለም ይልቁንም የበረታ ነው ማጣቱን በነገ ማግኘቱ ላይ ተስፋን የሰነቀ እራሱን ያበረታ እና በፈጣሪው ላይ የገዘፈ እምነት ያሳደረ ገፀ-ሰብ ነው። ቀጣዮቹም ስንኞች የሚያስተጋቡት ይህንኑ ነው .......... "ለጊዜው ሰው ቢያጣም ክብሩን በአንድ ጊዜ ያጣ ሰው ያገኛል እሱ ባለ ጊዜ አምላክ ባለው ጊዜ " "አላማርርም" አልበም የአፍላነት እድሜ ፍቅርን፣የአዲስ ህይወት ጅማሮን፣አስመሳይነትን፣ፍቅር እና እርቅን፣ትዳር እና ልጅን፣ፍቅር እና ወዳጅነትን፣አፍቅሮ ማጣትን እና ዝምታ ላይ መሰረት ያደረጉ 15 ሙዚቃዎችን ይዟል ። ይህ በ1999 አ.ም በናሆም ሬከርድስ አሳታሚነት ለአድማጭ የደረሰው የጥበቡ ወርቅዬ "አላማርርም" የሙዚቃ አልበም አብዛኛው ግጥም በሀብታሙ ቦጋለ የተደረሰ ሲሆን ታዋቂው ገጣሚ መሰለ ጌታሁን የ3 ሙዚቃዎችን ግጥም ሰርቷል አብዛኛው ዜማዎች በእራሱ ጥበቡ ወርቅዬ የተሰራ ሲሆን ደረጄ ዱባለ፣አማኑኤል ይልማ፣ሀብታሙ ቦጋለ፣ጎሳዬ ተስፋዬ በተቀሩት ሙዚቃዎች ላይ የዜማ አሻራቸውን አሳርፈውበታል ። ታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ዳግማዊ አሊ በሚማርኩ ቅንብሮች 14 ሙዚቃዎችን ያቀናበረ ሲሆን ሌላኛው ሁለገብ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ 1ሙዚቃ("ገባኝ አሁን ገና") በማቀናበር ተሳትፎበታል ። ጥበቡ ወርቅዬ ሁለተኛ እና የመጨረሻ አልበሙ ላይ ያለውን ሁለት ዘፈኖቹ ላይ የወከለውን አፍቃሪ ሰው ይለያል፤ (የለም አላልኩም አለ ግን አልተዘፈነለትም) ሁለቱም ዘፈኖች በግጥማቸው ክሊፕ አላቸው አንድ ታሪክ ይናገራሉ ፍፁም አፍቃሪነት ይታይባቸዋል፤ የመጀመርያው “ከአንቺ ባላገኝ እኔ ፍሬ አልቀይርሽም በሰው እኔ ሚዛን ደፍቷል ፍቅርዬ” “ ፍሬም ባናይ ባንታደል ሰላማችን ለምን ይጉደል ፅናት እምነት ፍቅር ካለን አብረን መኖር እንችላለን” (ግጥም መሰለ ጌታሁን) አንቺ ከምንም በላይ ነሽ የሚለውን በፈተና ወቅት እያረጋገጠላት ነው ሌላው “አላማርርም” አልበም ላይ ያለው የመጨረሻ ትራክ ደሞ “አንቺ አትሳቀቂ ሳይበቃኝ - ከበደኝ የሚል ቃል መቼ ወጣኝ አሁንስ መረረኝ ውይ በቃኝ - ሰለቸኝ የሚል ቃል መቼ ወጣኝ ያን ቆንጆ ትዝታ ደግ ደጉን ሰርዤ - ብተውሽ ምን ይላል አምላክ በመከራሽ ጊዜ ቀን ያመጣውን ነገር መውደዴን አይቀማኝም - ሁሌም ከጎንሽ ነኝ እኔ አትሰለችኝም” “ ድንገት ሆኖ እንጂ የወደቅሽው - መቼ ወደሽ አመጣሽው አልሄድም ፍቅሬ አይዞሽ - ቀን ጥሎሽ” ፍቅር በመካራ ውስጥ በተግባር የሚያሳይ አፍቃሪ በኦዲዮ ምስል ያለው ዘፈን ነው። ጥበቡ ወርቅዬ "አላማርርም" (1999 ዓ.ም) 1.አላማርርም ⭐ 2.ገባኝ አሁን ገና 3.ለምን በዬ 4.አንቺማ 5.ድንገት 6.ለኔ አላስብም 7.ሊገባ 8.አላንቺ አልኖርም 9.እየተያየን ተለያየን 10.ለማን ሆነና 11.እንዴት 12.ምን አረኩሽ 13.እባክሽን አስቢበት 14.ሄብዬ 15.ዝም *ሙዚቃ ቅንብር፣ ጊታር፣ ኪቦርድ እና ሚክሲንግ፤ -ዳግማዊ አሊ -ኤልያስ መልካ *ማስተሪንግ: አበጋዝ ክብረ ወርቅ *አብዛኛዎቹ አልበም ዉስጥ ያሉት ሙዚቃዎች የተቀናበሩት በዳግማዊ አሊ ነዉ። የጥበቡ ወርቅዬ የመጀመሪያ አልበም ሙሉ ለሙሉ ያቀናበረዉም እንዲሁ ዳግማዊ አሊ እንደነበር ይታወሳል ዛሬ ደሞ እኔም ከዚህ እንከን አልባ አልበም ላይ "አላማርርም" የተሰኘውን የአልበሙ መጠሪያ የሆነውን ጥልቅ መልዕክት ያለውን ውብ ዘፈን ጋበዝኳቹ🙏🙏 @𝙢𝙪𝙨𝙞𝙘𝙩𝙪𝙗𝙚🇪🇹 #fyp #ጥበቡወርቅዬ #የ90ዎቹ #አላማርርም #musictube369 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

About