@hahu.digitals: ከቅጥር ሠራተኝነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት ለመሸጋገር የሚረዱ 5 መንገዶች 1. በሥራ ላይ ሳሉ የጎንዮሽ ንግድ (Side Business) ይጀምሩ የመደበኛ ሥራዎን ወዲያውኑ አይልቀቁ። የንግድ ሃሳብዎን ለመሞከርና ፋይናንስ ለማድረግ የሚቀበሉትን ደመወዝ በጎን ስራ ይጀምሩበት።ይህን ማድረግዎ የፋይናንስ ስጋትዎ ይቀንሳል፡፡ የንግድ ሥራን እየተለማመዱ ቋሚ ገቢ ማግኘት ይጀምራሉ፡፡ የንግድ ሃሳብዎን መሬት ላይ ካለው ፍላጎት ጋር ለማረጋገጥ ጊዜ ያገኛሉ፡፡ 2. ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ ክህሎት ያዳብሩ ሥራ ፈጣሪዎች ችግሮችን ይፈታሉ፣ እሴትንም ይፈጥራሉ። በመሆኑም የንግድ ተቋማት ለእሱ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑትን ክህሎት ያዳብሩ።ለምሳሌ እንደ ሽያጭ (Sales)፡ማርኬቲንግ (Marketing)፡የግራፊክስ ዲዛይን (Graphic Design)፡የቪዲዮ ኤዲቲንግ (Video Editing)፡የማስታወቂያ ጽሑፍ ዝግጅት (Copywriting) ወይም የድረ-ገጽ ልማት (Web Development) እና ሌሎችንም ጠቃሚ ስኪሎች መርጠው ይማሩ፡፡ 3. የግል ስምዎትንና ተቀባይነትዎን (Personal Brand) ይገንቡ ሰዎች ስለ ንግድ ተቋሙ ከማመናቸው በፊት ሰውን ያምናሉ። ስለዚህ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ዕውቀትዎን ያካፍሉ ፡ጠቃሚ የብሎግ ጽሑፎችን ይጻፉ፡አጋዥ የሆኑ ቪዲዮዎችን ይልቀቁ፡የሥራዎችዎን ጥራትና ውጤት ያሳዩ ይህን በማድረግዎ ለማስታወቂያ ከፍተኛ ገንዘብ ሳያወጡ አዳዲስ ዕድሎችን፣ ደንበኞችን እና አጋርነቶችን መሳብ ይችላሉ። 4. መሠረታዊ የንግድ እና የፋይናንስ ክህሎቶችን ይማሩ ብዙ የተካኑ ሰዎች በንግዱ ዓለም የሚከስሩት ስለ ገንዘብ አያያዝ በቂ ግንዛቤ ስለሌላቸው ነው። ስለዚህ ትርፍ እና ኪሳራ (Profit and loss)፡የገንዘብ ፍሰት (Cash flow)፡የዋጋ አተማመን (Pricing)፡ የሽያጭ ሂደት (Sales)፡ ደንበኛን የማፍራት ስልት (Customer acquisition) እና ሌሎችን አጋዥ ሞያዎችን ያዳብሩ፡፡ 5. ሥራ ከመልቀቅዎ በፊት በንግድዎ የሚያገኙት ገቢ ከደመወዝዎ ጋር እኩል መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ ብዙዎች የሚሠሩት የተለመደ ስህተት ሥራን ያለጊዜው መተው ነው። ስለዚህ ከንግድዎ የሚያገኙት ገቢ አብዛኛውን ወይም ሙሉ የኑሮ ወጪዎን በቋሚነት መሸፈን ሲጀምር ብቻ ሙሉ በሙሉ ወደ ንግዱ ለመዞር ያስቡ። ይሄን ሲያደርጉ የፋይናንስ ውጥረትን ይቀንሳሉ፡የተሻሉ ውሳኔዎችን ለመወሰን ይረዳዎታል፡ንግዱን ለማሳደግ ተጨማሪ ጊዜ ያገኛሉ:: ብዙ ስኬታማ ሥራ ፈጣሪዎች መጀመሪያ ሥራቸውን ለቀው ከዚያ ንግድ አልጀመሩም። ይልቁንም እየሠሩ ሳሉ ንግዱን ይገነባሉ፣ ደንበኞች ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፣ ከዚያም ንግዱ ራሱን መቻል ሲጀምር ሙሉ በሙሉ ከቅጥር በመውጣት ወደ ንግዱ ይገባሉ። ፎሎው ማድረግዎን እንዳይረሱ፡፡

Hahu Digitals
Hahu Digitals
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 16 June 2026 10:02:51 GMT
72491
1454
28
438

Music

Download

Comments

tilk463
Tt :
Nice
2026-06-17 09:19:51
1
gensinabo
gensina :
ewnet new
2026-06-17 11:40:53
1
haknew.t
Haknew T. :
thank u. who is this?
2026-06-17 09:50:53
2
user5239634076208
mesfin janbo :
በጣም በጣም ነው ። የማመስግ ነው🥰🥰🥰🥰 ok
2026-06-16 19:32:14
3
howme1919
howme :
yes good Lidia!
2026-06-17 13:15:02
1
natijunior32
Naቷ 💀 Og🎯 :
yes i✌
2026-06-16 11:24:37
2
love.share.company
የኪስ ሱናሜ :
10Q
2026-06-17 05:40:19
1
melkame21
melkame21 :
tahnk you
2026-06-17 08:38:31
1
user6915127341266
ሰው ውድ ነው :
Nice
2026-06-16 23:09:11
2
abdidegaga462
abdisha degaga :
yes
2026-06-16 17:36:35
0
ridwan.mustefa
Ridwan Mustefa :
ትክክል ለማድረግ ዝግጁ ነኝ👏👏👏
2026-06-17 08:12:58
1
sisay212716
sisay :
thank you it is good
2026-06-17 10:56:38
1
user4188181747566
john habesha :
you are best
2026-06-17 13:42:52
0
tadesset760
sanyii gelan :
true thanksgiving
2026-06-16 11:55:18
2
user3968279791380
yodita :
thanks🥰🥰🥰
2026-06-17 07:24:04
2
usererimy123
Erimias :
perfect❤️
2026-06-17 08:22:01
1
19nahi3
Nahom 44 :
thankyou so mach
2026-06-17 06:12:44
1
user8635735467424
user8635735467424 :
always true
2026-06-16 11:16:02
2
almaz2214
Almi resin art & crafts :
thanks dear🙏🙏🙏
2026-06-16 19:13:48
1
epha2400
Epha2400 :
ይህ ቻናል የጀመርኩትን የተቀጣሪነት ስራ የማቆን እቅዴን ለማሳካት ፍጥነቴን እንድጨምር የጀመርኩትን የግል ስራ እንዳጠናክር እየረዳኝ ነው። thanks
2026-06-17 11:25:33
1
negen.yawek.yelem
ይሁን ብያለው🤙 :
እኔግን በሙሎታይም ስለራሴ ስራ ማሰብ አለብኝ ብየ ቅጥር ልተው ነው እስኪ ምከሩኝ አንዳንዴ ደግሞ ይሄን ያክል አመት የለፋውት በተማርኩበት ለመስራት ነው ስለዚህ ለምን የሚል ጥያቄ ይመጣብኛል ።
2026-06-17 11:21:01
1
sa.efficient45
Cool (🌍) :
le drgitachuh Logo lisralachuh
2026-06-16 12:36:09
0
kedeererasi
ዮሴፍ ዋሴ :
ምስጋናየ ከፍ ያለ ነው ❤️
2026-06-17 06:35:28
1
desalegn.bulti5
desalegn bulti :
😍
2026-06-16 11:26:16
1
To see more videos from user @hahu.digitals, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About