@etsegener.gebirem: 🌿🌹"#ቅዱስ_ያሬድ_ታሪክ_በአጭሩ"🎚️🤲❣️🌿 ♡#ወር_በገባ_11 ♡ ቅዱስ ያሬድ አባታችን እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናት የቅድስት ሀና መታሰቢያ ነው። እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ቤተሰብ🎚️🤲 ቅዱስ ያሬድ እናቱ ታውክልያ ( ክርስቲና ) አባቱ ይስሐቅ ( አብድዩ ) ይባላሉ። ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በሚያዚያ 5 ቀን 505 ዓ/ም ተወለደ ። አባቱም የአክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር ፤ ቅዱስ ያሬድ ገና በልጅነቱ /በ7 ዓመቱ/ አባቱ በሞት ስለተለየው እናቱ ወደ ትምህርት ቤት ልታስገባው ስለፈለገች አጎቱ አባ ጌድዮን ወደ ሚያስተምርበት ቤተ ቀጢን ጉባኤ ቤት አስገብታዋለች። ያሬድ ግን ከሌሎች ተማሪዎች አንጻር በትምህርቱ ደካማ ነበር፤ በዚህም ተስፋ ቆርጦ ወደ እናቱ መንደር መደባይ ሲመለስ በጉዞ ደክሞት ከአንዲት ዛፍ ስር አርፎ በነበረበት ሰዓት አንዲት ትል ተስፋ ባለመቁረጥ በመውደቅ እና በመነሳት በሰባተኛውም ወደዛፉ እንደወጣጭ ተመልክቶ፤ ያየውን በሕይወቱ ተርጉሞ ተስፋ መቁረጥን ትቶ ወደ መምህሩ ተመልሶ ትምህርቱን ቀጥሏል። ኋላም ትምርቱን በሚገባ እየተከታተለ ፤ አስቀድሞ አልገባ ያለውም ትምህርት ተገልጾለት ብሉይንን ከሐዲስ ኪዳን ተምሮ አጠናቆ በአጎቱ ወንበር ተተክቷል። ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊ የሆነው ዜማ ተገልጾለት በሦስት የዜማ ስልት ፤ ግዕዝ ፤ ዕዝል ፤ አራራይ በስምንት የዜማ ምልክቶች ድርሰቱን ደረሷል። ድርሰቶቹም ፦ 5 ሲሆኑ እነርሱም ፤ ድጓ ፤ ጾመ ድጓ ፤ ዝማሬ ፤ መዋሥዕት ፤ምዕራፍ ደብረ ሐዊ ከተባለው ተራራ ላይ በምናኔ ሕይወት ብዙ ዓመታትን ካሰለፈ በኋላ በጸለምት ዋሻ በ #ግንቦት_11 ቀን በ571 ዓ/ም ተሰውሯል። የቅዱስ ያሬድ ረድኤት በረከት በሁላችን ይደርብን🎚️ 🙏
ናታኔምነኝ የአንተው ባሪያ!ዕፀ_የኪዲዬልጅ_16♡
Region: AE
Thursday 18 June 2026 09:18:33 GMT
Music
Download
Comments
desalech.💖💖💖ቅድሰት,ኪደነ🙏🙏ምህረ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-18 15:51:47
0
mathrooshikalba :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-18 14:46:53
0
ማርያም ማርያም2121 :
🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-18 14:16:51
0
መሲ የማርያም ልጅ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-18 09:32:04
0
desalech.💖💖💖ቅድሰት,ኪደነ🙏🙏ምህረ :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-18 15:51:50
0
To see more videos from user @etsegener.gebirem, please go to the Tikwm
homepage.