@amharicliterature: የኔ ውብ ከተማ! ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር፣ ካለሠው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር? የኔ ውብ ከተማ ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር፣ የኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር፣ የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር፣ የሠው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡ ህንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ፣ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ፣ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ? እኔ ውብ የምለው፣ የሰውን ልብ ነው፡፡ ምን ቢነድ ከተማው ተንቦግቡጎ ቢጦፍ፣ ቢሞላ መንገዱ በሺ ብርሀን ኩሬ፤ …………………. በሺ ብርሀን ጎርፍ፡፡ ምን ያደርጋል? ምን ያሳያል? ካለ ሰው ልብ ብርሀን፣ ያ ዘላለማዊ ነበልባል ያ የተስፋ ሻማ፣ ጨለማ ነው ሁሉም፣ ጨለማ፣ ጨለማ። (በዓሉ ግርማ፣ ኦሮማይ፣ 1974) #creatorsearchinsights #poem #fyp #ethiopian_tik_tok #የአማርኛ_ቋንቋና_ሥነጽሑፍ

የአማርኛ ቋንቋና ሥነጽሑፍ
የአማርኛ ቋንቋና ሥነጽሑፍ
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 19 June 2026 03:35:04 GMT
1451
65
1
11

Music

Download

Comments

henok0686
Henok :
😭😭😭😭
2026-06-19 22:45:44
0
To see more videos from user @amharicliterature, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About