@user6005583568486: #ከሽራሮ አዲ-ፀፀር ግንባር እስከ ወሎ ቤተ አማራ ሰንሰለታማ ተራሮች! የአሳምነው ትውልድ ቀየ ላስታ ያፈራችው የጦር ጠበብት አርበኛ ሻንበል ወዳጀ ደሴ! ከፊቱ ላይ የሚታዩት የፈተና መስመሮች፣ የቆሰለው እግሩ እና በልቡ ውስጥ ያለው የህዝብ ፍቅርን ለተመለከተ ሰው አርበኛው በወገን ፍቅር የነደደ መሆኑን ይገነዘባል። አርበኛ ሻንበል ወዳጀ ደሴ፡ ከወጣትነት እስከ ጉልምስና እድሜው ድረስ ሙሉ ሕይወቱን ለአማራ ህዝብና ለሀገሩ ዳር ድንበር የገበረ የዘመናችን አንፀባራቂ ጀግና ነው። በ1982 ዓ/ም የድሮውን መከላከያ ሠራዊትን ተቀላቅሎ ለ14 ዓመታት ያህል በበረሃና በጋራ ሸንተረሮች ላይ ደሙንና ላቡን አፈስሷል። ፍርሃትን ፈፅሞ የማያውቀውና ጀግንነት መለያው የሆነው የዛኔው ወጣቱ ተዋጊ አርበኛ ሻምበል ወዳጄ፡ በየግንባሩ በሚያስመዘግባቸው አስደናቂ ጀብዱዎች የመቶ አለቃ ማዕረግ ሊያገኝ ችሏል። ወዳጀ ደሴ ተዋጊ ብቻ አልነበረም። የጦር ሜዳ ስልትን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ የጠላትን ካምፕ የሚያናጋ ደፋር አዋጊ ጭምር እንጂ። ከ1990ዎቹ መጀመሪያዎች ጀምሮ በነበረው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በታሪካዊው የሽራሮ ግንባር—አዲ ፀፀር ላይ ምድር በባሩድ ስትናወጥ፣ ሻንበል ወዳጀ ከባድ ተጋድሎ በማድረግ በውጊያ በመቁሰል ጭምር ለእናት ሃገሩ ታላቅ ታሪክ ፅፏል። በህክምና ቦርድ ተሰናብቶ ወደ ትውልድ ቀዬው፣ ወደ ታሪካዊቷ ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ፣ ላሊበላ ከተማ ተመለሰ። ሻንበል ወዳጀ ደሴ ለ20 ዓመታት በላሊበላ ምድር ከቆሰለ እግሩ ጋር እየታገለ፣ የሰላም ህይወትን መራ በዚህ ቆይታዉ ላሊበላ ከተማ ዉስጥ የተሻለ ህይወትን ይመራ ነበር። ነገር ግን ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ደጃፉን አንኳኳ። በ2013 ዓ.ም የሰሜኑ ጦርነት ሲቀሰቀስና "ሀገር ተወረረች፣ ህዝብህ አደጋ ላይ ወደቀ " የሚለው ጥሪ በመላ አማራ ክልል ላይ ሲያስተጋባ፣ አርበኛው ቤቱ ሊቀመጥ አልቻለም። የቆሰለ እግሩን ረሳው፤ ሽበት የወረረውን ራሱን በኩራት ቀና አድርጎ የአማራ ልዩ ሃይልን ተቀላቀለ። በወጣትነቱ ያካበተውን የጦርነት ልምድ በመጠቀም፣ ወጣቶቹን እያደራጀና እየመራ በጦርነቱ ግንባር ቀደም ተጋድሎን በማድረግ አይሰበርም የተባለዉን ባላጎ ምሽግን ከጓዶቹ ጋር ሆኖ በመስበር ደማቅ ታሪክን በደሙ ፃፈ። የብልፅግናው አገዛዝ የአማራ ልዩ ኃይልን ለማፍረስ በወሰነ ማግስት፣ አርበኛ ሻንበል ወዳጀ ደሴ የታገለለትን አላማ አሳልፎ ለመስጠት አልፈቀደም ነበር። ወዲያውኑ በላሊበላና አካባቢው ወደሚንቀሳቀሰው የነጻነት ጋሻ አሳረኛዉ ፋኖ ተቀላቀለ። በዚህ የሽምግልና እድሜው እሱ ለወጣቶቹ ፋኖዎች፦መካሪና ዘካሪ ነው—በችግር ጊዜ ተስፋ እንዳይቆርጡ የልብ ብርታታቸዉ ነው ፣ የውጊያ ስልትንና ጥበብን ያካፍላቸዋል። አሁንም ድሩስ አዋጊና ተዋጊ ነው። የጦር መሳሪያውን ይዞ በግንባር ቀደምትነት ይሰለፋል። የማይበገረው፡ የጦር ጠበብቱ፣ የአማራው አለኝታ በአሁን ሰዓት በአፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ 303ኛ አሳምነው ኮር በከፍተኛ አመራርነት እያገለገለ ይገኛል። አርበኛ ሻንበል ወዳጀ ደሴ የአሁኑ 303ኛ ኮር እዚህ መድረስ ታላቅ አብርክቶ አድርጓል። ከሻለቃ ብርጌድ ከብርጌድ ክፍለ ጦር ከክፍለ ጦር ኮር ድረስ እስከሚደርስ የላስታ ሰንሰለታማ ተራሮች ሳይበግሩት ተንቀሳቅሶ አደራጅቷል። ሻንበል ወዳጀ ከላስታ እሰከ መቄት ፣ከመቄት እስከ ዋድላ፣ከዋድላ ራያ ፣ ከራያ አንባሰል ድረስ በመንቀሳቀስ የፋኖ አደረጃጀት አሁን ላይ እዚህ መድረስ ትልቅ ስራ ሰርቷል። ከ1982 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ—ከወጣትነት ጉልበት እስከ ጉልምስና እድሜዉ ለአማራ ህዝብ ህልውናና ክብር ሲል ትውልድ የሚኮራበት ደማቅ አሻራ እያስቀመጠ ይገኛል። የእሱ ሕይወት የአንድ ሰው ታሪክ ብቻ አይደለም፤ የህዝብ ፅናት፣ የነጻነት ጥማትና የማይበገረው የአማራ ማንነት መገለጫ እንጂ። #catsoftiktok #ሸዋ_ጎንደር_ወሎ_ጎጃም💚💛❤_አንድአማራ_አንድ_ኢትዮጵያ #አርበኛ_ሻንበል_ወዳጁ_ደሴ
ገኒ የማርያም ልጅ
Region: SA
Friday 19 June 2026 16:40:05 GMT
Music
Download
Comments
የሸዋው መብረቅ :
2026-06-19 16:58:43
0
የእናቴ ናፋቄ :
2026-06-19 17:18:19
0
ሚካኤል አባቴ 🙏🙏🙏❤️ :
💪💪💪💪
2026-06-19 20:19:49
0
kidst 21 :
💪💪
2026-06-20 09:18:45
0
የሺ ላሊበላ የፋኖዎቹ እህት💚💛❤🇬🇧 :
💪💪💪💪💪
2026-06-19 21:08:57
0
tade @ye :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-20 07:16:21
0
ሳይንቴዋ)(እሙ)✊ :
❤️❤️❤️
2026-06-19 23:32:01
0
dagem :
🥰🥰🥰
2026-06-19 22:32:30
0
Mahi :
😁😁😁
2026-06-20 07:34:45
0
@Abay anawti :
🥰🥰🥰🥰❤️❤️🥰❤️🥰❤️🥰❤️🥰❤️
2026-06-20 11:12:35
0
geraman43 :
🥰🥰🥰
2026-06-19 18:46:40
0
Badriya :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-19 17:58:26
0
ŠŬŠŨ አማራዊት 💚💛❤️ :
🥰🥰🥰🥰
2026-06-19 17:16:04
0
ብሩክ ራያ ዩቲዩብ :
👌👌👌
2026-06-19 16:45:25
0
###አሳረኛው ፍኖ አሳር የወለደው## :
👍👍💪💪💪
2026-06-20 17:35:59
0
To see more videos from user @user6005583568486, please go to the Tikwm
homepage.