@goldenadvise4: በቻይና ከተማ ውስጥ በሚገኝ ታዋቂ የጋብቻ ገበያ መካከል አንዲት ሴት ቆማ ነበር። በዙሪያዋ ያሉት ትላልቅ ሰዎች ልጆቻቸውን ለማጋባት የሚስማማቸውን ወንድ ሲፈልጉ እሷ ግን ሌላ ነገር ትታስብ ነበር ። ዕድሜዋ 38 ዓመት ነው ። ጥሩ ሥራ አላት፣ በዓመት 500,000 ዩዋን ያህል ታገኛለች ። ቤት አላት ፣ መኪና አላት ፣ ብዙዎች ለማግኘት የሚመኙትን ሕይወት ገንብታ ነበር። ነገር ግን በዚያ ቀን ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው ነበር። "ለምን?" ብላ ራሷን ጠየች ከዛም ድምፆን ከፍ አድርጋ ። "ሁሉንም ነገር አግኝቻለሁ፤ ጠንክሬ ሠርቻለሁ፣ ራሴን ገንብቻለሁ። ግን ለምን አሁንም በዕድሜዬ ብቻ እገለላለሁ ብላ ጮከች?" ለጥቂት ሰከንዶች ውስጥ የገበያው ጫጫታ ፀጥ አለ። ምክንያቱም የጠየቀችው ጥያቄ የእሷ ጥያቄ ብቻ አልነበረም። ብዙ ሴቶች በልባቸው የተሸከሙት ጥያቄ ነበር። በቻይና ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ ያሉ ያላገቡ ሴቶችን "ሸንግ ኑ" ወይም "የቀሩ ሴቶች" ተብለው የሚጠሩበት አስተሳሰብ አለ። ብዙዎች ይህን ቃል እንደ ቀላል መግለጫ ያዩታል፤ ግን ቦታው ላይ ላሉ ሴቶች ቅስም ሰባሪ ቃላት ነው ።😭 ወንዶች ትምህርትሽን ያያሉ፣ ሥራሽን ያያሉ፣ ሀብትሽን ያያሉ፤ ከዚያ ግን ዕድሜሽን ብቻ በማየት ውሳኔ ይሰጣሉ።,ብላ እየጮሀች ተናገረች💔 በዚያ ቀን የፈሰሰው እንባ የአንዲት ሴት እንባ ብቻ አልነበረም። ሕልሟን ለማሳካት ዘመናቸውን የሰጡ ሴቶች ሁሉ እንባ ነበር። በማኅበረሰብ አጉል መለኪያዎች የወደቀች የተጨነቀች ሴት እንባ ነበር። ቪዲዮው በፍጥነት ተሰራጨ። ብዙዎች ሲመለከቱት የተመለከቱት አንዲት ሴት አልነበረችም፤ ራሳቸውን ነበር። ያልተነገሩ ህመሞቻቸውን፣ ያልተመለሱ ጥያቄዎቻቸውን እና በውስጣቸው የተሸከሙትን ብቸኝነት ነበር ያዩት። ምናልባት የታሪኩ ትልቁ ትምህርት ይሄ ይሆናል፤ ሰውን በዕድሜው፣ በሀብቱ ወይም በማኅበረሰብ መለኪያ መመዘን ቀላል ነው፤ ግን የልቡን ዋጋ ማየት ከባድ ነው።😭 እውነተኛ ፍቅር ዕድሜን አይቆጥርም። ቤትና መኪናን አይመዝንም። እውነተኛ ፍቅር ሁለት ልቦች በመተማመን፣ በመከባበር እና በመደጋገፍ የሚገነቡት ግንኙነት ነው። ስለዚህ ሰውን በዕድሜው ሳይሆን በልቡ ተመልከቱት። ምክንያቱም ዘመን ውበትን ሊቀይር ይችላል፣ ሀብትም ሊጠፋ ይችላል፤ ግን እውነተኛ ፍቅር እና ቅን ልብ የሚቆዩ ሀብቶች ናቸው❤❤❤❤ ምንጭ:- ባሲ አስገራሚ እውነታዎች ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ ❤️❤️እወዳቹሃለው❤️❤️ #fyp #fypシ #foryoupage #foryou #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ወርቃማ ምክሮች
Region: ET
Saturday 20 June 2026 07:00:57 GMT
Music
Download
Comments
fikade :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-20 16:52:47
0
To see more videos from user @goldenadvise4, please go to the Tikwm
homepage.