@natnaelmekonnen2: Good News : የእናቱን አስክሬን በቤት አስቀምጦ፣ የእናቱን የመጨረሻ ምኞት እና ቃል ለማክበር ከቀብር በፊትም ሆነ ከቀብር በኋላ ለ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና የተቀመጠውን ታዳጊ ካሊድን ዛሬ በስልክ አግኝቼዋለሁ። ካሊድ ከሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ጋር ከእናቱ ሞት በኋላ ከባድ የሕይወት ሸክም ተሸክሟል። የወንድሞቹን እንክብካቤና የቤተሰቡን ኃላፊነት በልጅነቱ ትከሻ ላይ ለመሸከም ተገዷል። ካሊድን በአካል ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘናል። ከእርሱ ጋር በቀጥታ ከተገናኘን በኋላ ያለበትን ሁኔታ በተሻለ መልኩ ተረድተን፣ እኔና አንድ የቅርብ ወዳጄ ተመካክረን ካሊድና ወንድሞቹ እንዳይቸገሩ፣ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለማድረግ አስበናል። በዚህ አጋጣሚ ካሊድን እንዳገኝ በትጋት የተባበረኝን ወዳጄ ጋዜጠኛ ሲማ (ዳጉ ኦርጅናል) ከልብ ላመሰግነው እወዳለሁ። በተጨማሪም ካሊድ የሚማርበትን ትምህርት ቤትና ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ በስልክ አብረውኝ የተወያዩና ጠቃሚ መረጃ የሰጡኝን የኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤቶች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ዱጉማንም ልዩ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በመጨረሻም ካሊድን በአካል ከጎበኘን በኋላ ስለሚኖሩ ቀጣይ ሁኔታዎችና ስለምንደርጋቸው ነገሮች ይበልጥ መረጃ እናካፍላችኋለን። ካሊድን እንዳገኝ በመረጃ፣ በምክርና በቅን ልብ የተባበራችሁኝ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ። የእናንተ ሰብአዊነትና ቸርነት ተስፋ የሚሰጥ ነው። ምስጋናዬ ለሁላችሁም ይድረስ። 🙏🏾

Natnael Mekonnen
Natnael Mekonnen
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 20 June 2026 15:01:19 GMT
52856
3480
7
419

Music

Download

Comments

ayuloti
Ayu :
Thanks 🙏🙏🙏
2026-06-20 17:52:04
10
love12023
Edu 🌎🎀 :
🙏🏽🙏🏽
2026-06-20 15:20:47
3
ayuloti
Ayu :
Natiye Elizabehr yibarky 😭
2026-06-21 04:14:01
5
yohannesmekonnen0
jonny one Love 🇪🇹 🇨🇭 :
good Job bro 🥰🥰🥰
2026-06-20 15:05:45
6
getakonew1
Lin💫 :
Tebark 👏👏👏
2026-06-21 12:20:19
2
abduzemen
ዘመን ተሻጋሪው - Abdu Mohammed :
🥰🥰🥰
2026-06-20 16:39:49
3
malmelissa
ይሳኮር 🇪🇹🇪🇹 :
😭❤️
2026-06-21 14:56:28
2
To see more videos from user @natnaelmekonnen2, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About