@amen29211619: ##የያዕቆብ_ሌሊት ያድርግልን ማለት ምን ማለት ነው? መጀመሪያ ያዕቆብ ማነው!? ቅዱስ ያዕቆብ የይስሐቅ ልጅ ማለትም የአባትችን የአብርሃም የልጅ ልጅ ነው። የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ርብቃን አገባ ርብቃም መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራትምና አባታችን ይስሐቅ ስለ ሚስቱ እግዚአብሔርን ለመነ እግዚአብሔርም ተለመነው፥ርብቃ ሚስቱም ፀነሰች። ልጆቹም በሆዷ ውስጥ ይገፋፉ ነበር ርሷም፦እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔ ምኔ ነው አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች። እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፦ሁለት ወገኖች በማህፀንሽ ናቸው፥ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል ታላቁም ለታናሹ ይገዛል። ትወልድ ዘንድ ዘመኗ በተፈፀመ ጊዜም፦እነሆ በማህፀኗ #መንታ ነበሩ። በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ፥ሁለንተናውም ጠጉር ለብሶ ነበር ስሙም #ዔሳው ተባለ። ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር ስሙም #ያዕቆብ ተባለ። አባታቸው ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበር እናታቸው ርብቃ ግን ያዕቆብን አብልጣ ትወደው ነበር ስለዚህም አባታቸው ይስሐቅ በሸመገለ ጊዜ በጣም አርጅቶ ነበርና ለሚወደው ልጁ ሊባርከው (ሊመርቀው) አሰበ። ነገር ግን እናታቸው ርብቃ የዔሳውን ምርቃን ለያዕቆብ በመምከር የዔሳውን በረከት አስወሰደችበት። ዔሳውም በጣም ተናዶ ወንድሙ ያዕቆብን ለመግደል ወሰነ (በረከቱ) ወስዶበታልና፦ እናቱ ርብቃም ይህ የታላቁ ልጇ የዔሳውን ቃል ደረሰላት ታናሹንም ልጇን ያዕቆብንም አስጠርታ እነሆ ወንድምህ ዔሳው ሊገድልህ ይፈቅዳል። ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ ተነስና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድለት ጥቂት ቀናት በዚያው ተቀመጥ ብላ አሳመነችው። ያዕቆብም እሺ ብሎ መንገዱን ጀመረ። ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፦ፀሐይም ጠልቃ ነበርና፥ከዚያ አደረ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሳ፥ከእርሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ራሱም ወደ ሰማይ ደረሰ፥እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበርና። እነሆም፥እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥እንዲህም አለ፦የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህችን አንተ የተኘህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጥሃለሁ ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምስራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ የምድርም አህዛብ ሁሉ ባንተ በዘርህም ይባረካሉ። እነሆም እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፥በምትሄድበትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ወደዚችም ምድር እመልስልሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና። ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነስቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው እኔ አላወቅሁም ነበር አለ። ፈራ፥እንዲህም አለ፦ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም ይህም የሰማይ ደጅ ነው። ያዕቆብም ማልዶ ተነሳ፥ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥በበላዩም ዘይትን አፈሰሰበት። ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያንች ስም ሎዛ ነበረ። ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ቢሆን፥በምሄድበትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥ ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል። ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአስር እጅ አነዱን እሰጥሃለሁ። ብሎ ቃል ገባ። ➕ ስለዚህም እኛም የያዕቆብ ሌሊት ያድርግልን የምንባባለው እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳን መላእክቱ ከኛጋር እንዲያድርና ጥሩ የሰላም እንቅልፍ እንዲያስተኛን ቅዱሳን በህልማችን መላእክትን እንዲያሳየን ከመጥፎ ህልም እንዲጠብቀን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዲሆን ከመጥፎ አጋንንት እንዲጠብቀን #የያዕቆብ_ሌሊት ይሁንልን እንላለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን!!! ለበለጠ ኦሪት ዘፍጥረት (26_30) አንብቡት

Alem✝️🦋🦋
Alem✝️🦋🦋
Open In TikTok:
Region: CA
Saturday 20 June 2026 23:46:16 GMT
15366
1839
87
159

Music

Download

Comments

kidiyyen1621
yonas :
እናመሰግናለን 🙏 የአቆብ ለሊት ያድርግልን
2026-06-21 08:51:34
8
sewayehu.sewayehu
ሂዋን የኪዳኗ ልጅ :
ቃለ ሂወት ያሰማልን🙏🙏🙏
2026-06-21 20:28:08
2
maryamey953
maryamey :
amen amen amen kalehiwet yesmealna
2026-06-21 21:14:44
0
egziabher.eregnaye1
Egziabher eregnaye newu :
ቃለ ህይወት ያሠማልን🙏🙏🙏👏
2026-06-21 21:38:24
1
yared.girmay71
Yared Girmay :
Amen 🙏 kalehiwet yasemaln 🙏🥰🙏
2026-06-21 20:36:20
1
user4695585329473
victor :
Amen Anen Amen Kale Hiywoten Yasemalen Tsega Bereketuen Yalebeselen 🥰🥰🥰
2026-06-21 20:43:20
1
boll94301gmail.com
• ÐĀŴĄ ● :
አሜን 🙏
2026-06-21 18:47:13
1
shumoyteka
ጭለይ ወዲ :
አሜን🙏🙏🙏
2026-06-21 14:33:38
1
leykundemek0
🍒ባላገሯ🍒➏➒ :
ቃለሂወትን ያሠማልን 🥰❤️
2026-06-21 17:04:33
2
welloyewa17
አበባ :
ቃለህወት ያሰማልን🥰🥰🥰
2026-06-21 09:07:50
4
hiraaberaa
hira ❤️ :
አሜን🙏
2026-06-21 17:58:35
1
ayu75624
باايبتتت :
ቃለህይወትያሰማልን
2026-06-21 17:19:37
1
samson.samson22
Samson😎😎 :
ቃለሂወት ያሰማልን🙏🙏🙏
2026-06-21 17:08:31
1
smike61
ስምከ ሕያው ዘኢይመውት :
አሜን🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-21 12:35:07
1
abebamisge
Abeba :
አሜን አሜን አሜን
2026-06-21 10:17:57
1
joyko860
Jo :
where to get all verses 🥺???
2026-06-21 11:07:08
1
m349422
ሠላሜ ነሽ ድንግል✝️🛐♥️ :
ቃለህይወትን ያሠማልን እግዚአብሔር ይስጥልን አሜን፫🙏🥰🥰
2026-06-21 11:10:01
1
danchye.b
Banchye🍋🍋🍋 :
አናመስግናለን🥰
2026-06-21 06:59:56
1
user4116268023474
የባላዋ ቀበጥ🌹🌹🌹 :
ትልቁ ራእይ ያየ ኣባት ስለ ሆነ🙏🙏
2026-06-21 07:43:11
1
mimmii12.21
mimi@1221 :
ameen ameen kale hiwoti yasemalen 🙏🥰🥰🥰🥰
2026-06-21 08:05:38
1
joyko860
Jo :
ameen
2026-06-21 11:06:52
1
watermelon632
𝑖𝑡 "𝑠 𝑚𝑒 ✝️ :
ቃለ ህይወትን ያሠማልን እግዚአብሔር ይስጥልን 🙏🥰😘
2026-06-21 17:55:13
1
mekdi.yemariam3
mekdi yemariyam❤️💝💚😘 :
kalehwet yasemaln 🙏🙏🙏🙏🙏
2026-06-21 11:03:24
1
barikoti.mesifen
waabii,salalele :
🙏🙏🙏🙏🥰🥰😏😏😏😏tebarkuu
2026-06-21 10:26:31
1
To see more videos from user @amen29211619, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

Trying Johnnie Walker Red Label Blended Scotch Whiskey 🥃 Johnnie Walker Red Label Review | Is It Worth the Hype or Just Bar Rail Filler? | Bottle Hunters Reviews In this episode of Bottle Hunters Reviews, we’re going back to one of the most iconic—and polarizing—blended scotches in the world: Johnnie Walker Red Label. Known for its fiery personality and global reach, this is the entry point to the Johnnie Walker lineup. But how does it really hold up on the palate? We give Red Label a proper tasting, break down its flavor profile, and talk about where it shines (and where it burns). 🔥 Tasting Breakdown: Type: Blended Scotch Whisky ABV: 40% (80 proof) Nose: Light smoke, malt, pepper, and citrus Palate: Spicy bite, toasted grain, hint of smoke, slight fruitiness Finish: Short to medium, with lingering heat and peat Best Use: Highballs, cocktails, or over ice — not built for sipping neat Our Take: Johnnie Walker Red Label isn’t here to be smooth and elegant—it’s here to punch. While it may not satisfy the single malt purists, it absolutely delivers in mixed drinks. A solid choice for whisky & soda fans, but tread carefully if you're sipping it neat. 🧊 Try it in a Scotch & Ginger, and let us know what you think! 💬 What's your go-to Johnnie Walker label? Comment below and subscribe for more affordable whisky breakdowns. #JohnnieWalker #RedLabelReview #ScotchWhisky #BottleHuntersReviews #BudgetScotch #WhiskyTasting #JohnnieWalkerRed #BlendedScotch #WhiskyCocktails #HangoverForecast

About