@samuelbekele37: DW Radio ሳሙኤል በቀለ ይባላል። ሳሙኤል አዲስ አበባ ውስጥ ጎፋ መብራት ኃይል ኮንዶሚኒየም የሚባል ቦታ ቡና አፍልቶ መሸጥ ከጀመረ አንድ ዓመት ሆኖታል። የአንድ ሱቅ በራፍ ላይ ከፕላስቲክ የተሰራ ትንሽዬ ረከቦት ላይ ጥቂት ስኒዎችን ደርድሮ ፤ በጀበና ቡና አፍልቶ ይሸጣል። ከፊቱ ጥቂት ከፕላስቲክ የተሰሩ መቀመጫዎችን አዘጋጅቷል። “ሰዎች ስለእኔ ብዙ ይላሉ” ይላል ሳሙኤል፤ አፍልቶ የሚሸጠው ቡና ጥሩ ስለሆነ ወይስ ወንድ ሆኖ በረንዳ ላይ ቡና በማፍላቱ? ”መንገድ ዳር ሆኜ እንደዚህ ስለሰራሁ፤ እነሱ ሌላ ነገር አሰቡ።እንደሴት ነው የምትሄደው፤ እንደ ሴት ነው የምትሰራው፤ ምናምን ይላሉ። ምን ማድረግ እችላለሁ? ስድቡን ቻልኩት በቃ! እኔ ስራዬን ብቻ መረጥኩ፤ ምክንያቱም መንገድ ዳር ወጥቼ ብለምን ማንም ዳቦ የሚገዛልኝ ሰው ስለሌለ! ” ይላል። ሳሙኤል ወደዚህ ስራ ከመግባቱም በፊት ጎዳና ላይ ሊወድቅ እንደነበረ እና ስራ እንዳልነበረው ገልፆልናል። “መሄጃ ስላልነበረኝ፤ስራም ስላልነበረኝ ነው ስራውን የጀመርኩት። እንድጀምር ያደረገችኝ አንዲት እናት ናት፤ ደንበኛዬ ነበረች። ቡና ቤት ተቀጥሬ ስሰራ ፤ስራዬን አይታ ስለነበር ፤ እንደራስህ ስራ ነው የምትሰራው፤ ጎበዝ ነህ ብላ ለእኔ ስላዘነች ብር አግዛኝ ነው በእሷ ብር ይህን ስራ የጀመርኩት። እኔ አምስት ሳንቲም አልነበረኝም። እቃ አብራኝ ገዝታ ይቺን ስራ አስጀመረችኝ። ” ቦረና ውስጥ ዘመድ ቤት ይኖር እንደነበር የሚናገረው ሳሙኤል ምንም እንኳን ወላጆች ቢኖሩትም፤ በማናቸውም ዘንድ ልጆች ማግኘት ያለባቸውን ፍቅር እና እንክብካቤ አግኝቶ እንዳላደገ ይናገራል፤”ምንም ተደስቼ አላውቅም። ከልጅነቴ አንስቶ እስካሁን ድረስ በስራ ነው ያደኩት።ተቸግሬ፤ በርሃብ፤ ልብስ እና ጫማ የሚገዛልኝ አልነበረም። ካፌ ላይም ስሰራ ነበር። አጎቴ ቤት በነበርኩበት ጊዜ የቤት ወጪ ሸፍን ተብዬ እቃ እገዛለሁ። በልጅነቴ ነው እነሱ ጋር የመጣሁት። ወላጆቼ በህይወት አሉ፤ ግን ምንም ለእኔ የሚያደርጉት ነገር የለም። (ዘመድ ጋር )ከመጣሁም በኋላ እንደቤት ሰራተኛ ነው ያደኩት። ጨርሶ ትምህርት ቤት ሄጄ አላውቅም። ”
ሳሚ ኮፊ
Region: ET
Sunday 21 June 2026 07:57:27 GMT
Music
Download
Comments
maki love :
ዳይ ወደ ቻሌጅ
የተሻለ ቤት ተከራይቶ ሰራተኛ ቀጥሮ እሱም እያስተባበር እሚሰራበት ቻሌጅ ይጀመርለት
2026-08-08 17:38:21
231
christian orthodox :
በርታ ወንድሜ ማንንም እንዳትሰማ እግዚአብሔር ይረደሃል🙏🙏🙏🙏
2026-06-21 15:31:12
155
Jerry :
ጀግና ነርታ አይዞህ እግዚአብሔር ከሚሰሩት ጋር ነው 🙏
2026-06-22 10:51:09
84
meski 🔥 :
ለታርክ ይቀመጥ ይሄ ምን አለች በለኝ የተሻለ ቦታ ትደረሳለህ በፈጣሪ ፊቃድ🙏🙏🙏🙏
2026-08-09 21:18:24
58
liya :
ቻሌጅ ይጀመር
2026-08-10 01:37:39
19
salme :
ትልቅ ደረጃ ደርሰህ እንደማይህ ተስፍ ኣለኝ 🥰🥰🥰🥰
2026-06-22 05:19:18
37
Genet Eshetu :
የኔ ጀግና ስራ መስራት አያሰድብም ተሳዳቢዎቹን እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው አንተ ግን ወደኋላ ንደትመለስ የሚያሳፍረው መስረቅ ነው በርታልኝ
2026-08-08 10:02:06
18
lully_mood❣️ :
ajoka hawey srah kbret eyu 🥰
2026-06-21 17:53:09
22
Eyu Biru :
የኔ ጀግና ወንድሜ ኣይዞህ በርታ ማንንም እንዳትሰማ ተባረክ
2026-06-22 03:33:33
17
ሓቂ ንናገር ፣ :
በርታልን ወድሜ🥰🥰🥰
2026-06-21 16:26:52
12
Meri Jer :
ሳሚ ጀግና❤️❤️
2026-06-22 20:24:27
3
መአዛ :
🥰ጀግና ነህ በርታ ሰው አውርቶ ሲጨርስ ዝም ይላል ማንንም እንዳትሰማ ነገ ሌላ ቀን ነው 🥰🥰🥰🥰
2026-06-22 15:00:37
9
Addisu Zewde( ilu Gore Saabee :
ስበዛ ጠንካራ አስተማሪ ልጅ ነው አቅም ያላቹ ወገኖች ድጋፍ ብታደርጉለት🤲🤲🤲
2026-08-11 05:33:08
5
Aki Tekle :
emebeten endanta jegna lefito ader alayehum berta ye esraeil kdus alelik sile beletikachew new maninm atsma shkor hawey💕💕💕💕🙏
2026-07-30 15:24:13
2
አለም :
ጀግና ውንድሜ
2026-08-01 20:07:57
1
Rooney :
በርታ ወንድሜ ሁላችንም ችግርን አይተን ነው ያሳለፍነው እንደሚያልፍልክ እርግጠኛ ነኝ❤️🙏
2026-06-23 13:26:48
6
Morning MOVERS :
አይዞን🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-23 15:31:57
1
tigwuhib :
ጎበዝ በርታ ሳሙኤል አንድ ቀን ትልቅ ቦታ ትደርሳለህ።🙏🙏🌺🌺
2026-08-05 19:57:54
2
hame fkr :
challenge yejemerelet
2026-08-10 08:30:18
2
Marta Tekle :
ነገ የተሻለ ይሆናል 🥰🥰
2026-06-23 06:59:33
3
Kidist Hailu :
ጀግና ነህ በርታ ነገ የትልቅ ሆቴሎች ባለቤት እንደምትሆን አልጠራጠርም ሰውን አትስማ ስራህን ብቻ ስራ ነገ የተሻለ ቀን ነው
2026-07-16 19:21:02
3
atie :
berta gobez🥰🥰🥰
2026-06-21 16:06:33
4
fiker :
ወንድሜ በርታ አየዞህ ሰውን አትስማ ብዙ ያወራል 🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-23 10:15:27
2
hayati ንቃት ቡና :
አንተ ጀግና ነህ በርታ የሰዉ ወሬ እንዳሰማ
2026-08-10 06:58:10
4
To see more videos from user @samuelbekele37, please go to the Tikwm
homepage.