@khaalidmaxamuud01:

Finoh 𝐞𝐝𝐢𝐭 𝐂𝐚𝐫
Finoh 𝐞𝐝𝐢𝐭 𝐂𝐚𝐫
Open In TikTok:
Region: SO
Sunday 21 June 2026 17:35:51 GMT
33
8
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @khaalidmaxamuud01, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

የጥበብ መድረክ🫂 ✍️በመጀመሪያ አውቃለሁ የግርማ በየነ እና የሙላቱ አስታጥቄ ስም አለማካተቴ ነውር ነው ግን በሌላ ዘርፍ እነዚህ ባለውለታዎች ቆየት ካላቱ ዘመናት የሙዚቃ አባቶች ጋር አካትቼ የኢትዮጵያን ሙዚቃ የጡት አባቶችን ያለማወዳደር እንደምናወሳቸው ቃል እገባለው🙏🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ዛሬ ይዤላቹ የመጣሁት የምርጥ 10  የሙዚቃ አቀናባሪዎች በእኔ በግሌ በደረጃ የተቀመጡ እና በራሴ ምንም የሙዚቃ እውቀት በሌለው አንድ ተራ ግለሰብ የተቀመጠ ደረጃ ነው ምን አልባት የማትስማሙበት እንኳን ቢሆንም ከተችት እና ከስሜታዊነት ነፃ ሆናቹ እንድትወያዩበት በማለት ወደዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን ፊት አውራሪ የኢትዮ ጃዝ አባት 🪘ክቡር ዳክተር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ አለም በግርምት እጁን በአፉ የጫነለት ከ40 አመት በላይ በልህቀት የከበረ ጀግና እንመለስ🙌   የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ የጡት አባት ሀገሩን ከጥግ እስከጥግ ባህሏን ጠንቅቆ የተረዳ የተደበቁት ወደፊት ያመጣ ባንዲራውን ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ በኩራት ያውለበለበ የማይደገም ታሪክ ሰሪ ሙዚቀኛ ብቻም ሳይሆን አስተማሪም ፈላስፋም ተመራማሪም የሆነው ሙላቱ አስታጥቄ 🙏 ውድ ቤተሰቦቼ ዛሬ ወደዚህ ወደእዛ ማለት የለም ታላቁን ሰው እናወሳዋለን እናመሰግነዋለን🙌🥰 በጅማ ከተማ በ1935 ዓ.ም ገፀ በረከት ሆኖ የተሰጠን ልዕለ ሰብ የሙዚቃ ሰው ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ💜 ለበርካታ ዓመታት ሕይወቱን ለሙዚቃ ጥበብ የሰጠው ሙላቱ በአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት እና በእንግሊዝ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት አስራ ስድስት ዓመት እስኪሞላው ድረስ ዘመናዊ ትምህርቱን ተከታትሏል። ከዚያም በእንግሊዝ አገር ወደሚገኘው ላንድስ ፌም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሄዶ ትምህርቱን እንደቀጠለ መረጃዎች ያስረዳሉ።  በሃያዎቹ የዕድሜው አጋማሽ ወደ ሰሜን አሜሪካ በመጓዝ በቦስተን በሚገኘው በርክሌይ ኮሌጅ የሙዚቃ ትምህርቱን በመቀጠል ሁለገብ የሙዚቃ ፈጠራ፣ ቅንብር እና የምርምር ሥራ ላይ ያተኮሩ ሥልጠናዎችን ለአራት ዓመታት ያህል ተከታተለ። ይህም በወቅቱ በኮሌጁ ይሰጥ የነበረ ከፍተኛ ሥልጠና ሲሆን፤ አርቲስቱንም የመጀመሪያው አፍሪካዊ ተማሪ ለመሆን አብቅቶታል።አርቲስት ሙላቱ በዚህ ሳይገታ በዚያው በአሜሪካ በሚገኘው ኸርትኔት ሞደርን ሚውዚክ ኮሌጅ ውስጥ ተጨማሪ የአራት ዓመታት ትምህርቱን አጠናቅቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የካልቸራል ስተዲስ መምህር የሆኑት አቶ ስሜነህ በትረየስ
የጥበብ መድረክ🫂 ✍️በመጀመሪያ አውቃለሁ የግርማ በየነ እና የሙላቱ አስታጥቄ ስም አለማካተቴ ነውር ነው ግን በሌላ ዘርፍ እነዚህ ባለውለታዎች ቆየት ካላቱ ዘመናት የሙዚቃ አባቶች ጋር አካትቼ የኢትዮጵያን ሙዚቃ የጡት አባቶችን ያለማወዳደር እንደምናወሳቸው ቃል እገባለው🙏🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ዛሬ ይዤላቹ የመጣሁት የምርጥ 10 የሙዚቃ አቀናባሪዎች በእኔ በግሌ በደረጃ የተቀመጡ እና በራሴ ምንም የሙዚቃ እውቀት በሌለው አንድ ተራ ግለሰብ የተቀመጠ ደረጃ ነው ምን አልባት የማትስማሙበት እንኳን ቢሆንም ከተችት እና ከስሜታዊነት ነፃ ሆናቹ እንድትወያዩበት በማለት ወደዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን ፊት አውራሪ የኢትዮ ጃዝ አባት 🪘ክቡር ዳክተር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ አለም በግርምት እጁን በአፉ የጫነለት ከ40 አመት በላይ በልህቀት የከበረ ጀግና እንመለስ🙌 የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ የጡት አባት ሀገሩን ከጥግ እስከጥግ ባህሏን ጠንቅቆ የተረዳ የተደበቁት ወደፊት ያመጣ ባንዲራውን ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ በኩራት ያውለበለበ የማይደገም ታሪክ ሰሪ ሙዚቀኛ ብቻም ሳይሆን አስተማሪም ፈላስፋም ተመራማሪም የሆነው ሙላቱ አስታጥቄ 🙏 ውድ ቤተሰቦቼ ዛሬ ወደዚህ ወደእዛ ማለት የለም ታላቁን ሰው እናወሳዋለን እናመሰግነዋለን🙌🥰 በጅማ ከተማ በ1935 ዓ.ም ገፀ በረከት ሆኖ የተሰጠን ልዕለ ሰብ የሙዚቃ ሰው ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ💜 ለበርካታ ዓመታት ሕይወቱን ለሙዚቃ ጥበብ የሰጠው ሙላቱ በአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት እና በእንግሊዝ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት አስራ ስድስት ዓመት እስኪሞላው ድረስ ዘመናዊ ትምህርቱን ተከታትሏል። ከዚያም በእንግሊዝ አገር ወደሚገኘው ላንድስ ፌም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሄዶ ትምህርቱን እንደቀጠለ መረጃዎች ያስረዳሉ። በሃያዎቹ የዕድሜው አጋማሽ ወደ ሰሜን አሜሪካ በመጓዝ በቦስተን በሚገኘው በርክሌይ ኮሌጅ የሙዚቃ ትምህርቱን በመቀጠል ሁለገብ የሙዚቃ ፈጠራ፣ ቅንብር እና የምርምር ሥራ ላይ ያተኮሩ ሥልጠናዎችን ለአራት ዓመታት ያህል ተከታተለ። ይህም በወቅቱ በኮሌጁ ይሰጥ የነበረ ከፍተኛ ሥልጠና ሲሆን፤ አርቲስቱንም የመጀመሪያው አፍሪካዊ ተማሪ ለመሆን አብቅቶታል።አርቲስት ሙላቱ በዚህ ሳይገታ በዚያው በአሜሪካ በሚገኘው ኸርትኔት ሞደርን ሚውዚክ ኮሌጅ ውስጥ ተጨማሪ የአራት ዓመታት ትምህርቱን አጠናቅቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የካልቸራል ስተዲስ መምህር የሆኑት አቶ ስሜነህ በትረየስ "ሙላቱ አስታጥቄ ማነው?" በሚል ርዕስ ስለ አርቲስቱ ሕይወት ያካሄዱት የዳሰሳ ጥናት እንደሚያስረዳው አርቲስት ሙላቱ በለንደን ቆይታው ኤድሞንዶሮስ ከተሰኘው የሙዚቃ ቀማሪ እና የላቲን ጃዝ ባንድ መሪ ጋር በርካታ ሙዚቃዎችን ተጫውቷል። አርቲስት ሙላቱ በተለያዩ የምሽት ክበቦች እና የቴሌቪዥን ሥርጭቶች ዝግጅቱን በማቅረብ የነበረውን የሙዚቃ ተሰጥኦ በተደጋጋሚ አስመስክሯል። ከዚህም አልፎ “ነፍስ ነሽ” የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበሙን “ፋራንክ ሆልዳና ኒያዝ አልሸሪፍ” ከተሰኙ አሳታሚዎች ጋር በመተባበር አቅርቧል። ወደ ሰሜን አሜሪካ ከተጓዘ በኋላ በ1958 ዓ.ም አፍሮ -ላቲን ሶል ቁጥር አንድና ቁጥር ሁለት አልበሞቹን ለማሳተም በቅቷል። በመጀመሪያው አልበም “አይፈራም ጋሜ አይፈራም”፣ “አልማዝ” እና “አክሱም” የተሰኙትን ኢትዮጵያዊ ሙዚቃዎችን ሲያካትት በሁለተኛው “ቆንጂት” እና “ከረዩ” የተሰኙትን አክሎበታል። ይህ አጋጣሚ ነበር ሙላቱ “ኢትዮ ጃዝ” የተሰኘውን የሙያ ልጁን ለመጠንሰስ የበቃው። በእሱ የተፈጠረው ኢትዮ ጃዝ ዛሬ በዓለማችን እንደ አንድ የሙዚቃ ስልት ተቀባይነት አግኝቷል። የኢትዮ ጃዝ ማዕከላዊ ሃሳብ የጃዝ ሙዚቃን ባህርያት ከአገር በቀል የኢትዮጵያ ሙዚቃ እና የሙዚቃ መሣሪያዎች ጋር ማንነታቸውን ሳይለቁ ማዋሃድ ነው። ሙላቱ እንዲህ አይነቱን የሙዚቃ ዘይቤና ስያሜ ለዓለም ካስተዋወቀበት ጀምሮ ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ አፍሪካ ለዓለም የሙዚቃ ባህል ያበረከተችውን አስተዋፅኦ ያለመሰልቸት ሲያስረዳና በሥራዎቹም ሲያረጋግጥ ኖሯል። ሙላቱ ለድምፃውያን ሙዚቃ በማቀናበር ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ሥራዎችን በመቀመርና በመሣሪያ ብቻ የተዘጋጁ ሙዚቃዎችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አስቀርጿል። ለዚህም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በተከታታይ የተቀረጹትን « ኢትዮ ጃዝ» እና «አስዮ ቤሌማ» የተሰኙትን በምሣሌነት መጥቀስ በቂ ነው።ሙላቱን ልዩ የሚያደርገው የተዋጣለት የመድረክና የስቱዲዮ ሙዚቀኛ መሆኑ ብቻ አይደለም። በተለያዩ የአገራችን ብሔረሰቦች ሙዚቃዎች እና አገር በቀል የሙዚቃ መሣሪያዎች ላይ የሚያደርጋቸው ዘርፈ ብዙ የምርምር ሥራዎችም ጭምር እንጂ። ከሰሜኑና ከመካከለኛው የአገራችን የሙዚቃ ባህል ባለፈ በኮንሶ፣ በወላይታ፣ በከፋ፣ በደራሼ፣ ጋሞ፣ አኙዋክ፣ በሱርማና በሌሎችም ብሔረሰቦች ሙዚቃ ላይ ምርምር አድርጓል። በጥበብ ውስጥ ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ የዘለቀው አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ የኢትዮጵያን ጃዝ ሙዚቃ ለማስተዋወቅ ዓለምን ዞሯል። ከታዋቂ ሰዎች ጋርም ኮንሰርቶችን አዘጋጅቷል። የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችንም አግኝቷል። በተለያዩ ኢንሳይክሎፒዲያዎች ታሪኩ መመዝገቡንም ነው የአቶ ስሜነህ ጥናታዊ ጽሑፍ ያስረዳል ።የኢትዮ ጃዝ አባት እየተባለ የሚጠራው አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በ97.1 ኤፍ ኤም ሬዲዮ የሚተላለፈው አፍሪካ ጃዝ መንደር የሬዲዮ ፕሮግራሙ ተወዳጅ ከሆኑ ፕሮግራሞች መካከል አንዱ ነው። የአርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ ለሙዚቃው ኢንዱስትሪ ላበረከታቸው አስተዋጽኦ የተሰጠው ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ እውቅናዎች • በሙዚቃ ትምህርት ታላቅ በሚባለው በርክሌይ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬትም ያገኙ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ • ከጅማ ዩንቨርስቲ የክብር ዶክትሬት • የህይወት ዘመን የክብር ሽልማት • በጀርመን አገር በስሙ መንገድ ተሰይሟል • የአብራውዝ ግራንት አሸናፊ • በአሜሪካም የበርክሊ የሙዚቃ ኮሌጅ የመጀመሪያው ጥቁር የሙዚቃ ተማሪ • “ብሮክን ፍላወር” የተባለው ፊልም ላይ ሙዚቃ በመሥራት ትልቅ አድናቆት ያተረፈ • የበርክሊ የሙዚቃ ኮሌጅ የአፍሪካ ትምህርቶች ክፍል አማካሪ • የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደር✨ ክብር ለታላቁ ሙላቱ አስታጥቄ 🙏🙏🙏 ለዛሬ አበቃሁ ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙌🙏 @musictube 🇪🇹 #fyp #ምርጥ10 #አቀናባሪ #musictube369 #ethiopianmusic

About