@silentwarrior_et: . . እንግዲህ ካንቺ መለየት ግድ ከሆነ በኋላ፣ እኔነቴ ምን እንደሚመስልና በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለሁ በአጭሩ ልንገርሽ። ካንቺ መለየት ማለት ለእኔ ዝም ብሎ አንድን ሰው መራቅ ሳይሆን፣ የህይወትን ትርጉም ማጣት እንደሆነ አሁን ነው የተረዳሁት።   ቀናት ይመጣሉ፣ ያልፋሉ። ነገር ግን ለእኔ ጠዋትና ማታው ምንም ልዩነት የላቸውም። አንቺ ከሌለሽበት ማለዳ ይልቅ ጨለማው ይሻለኛል፤ ምክንያቱም በህልሜ እንኳ አንቺን የማገኝበት እድል ይኖረኛል።   አንቺ የሌለሽበት ቤት ለእኔ ባዶ አራት ግንብ ብቻ ሆኖብኛል። በየጥጉ ያንቺ ሳቅ፣ ያንቺ ትዝታና ድምፅሽ እያስተጋባ ብቻዬን ያሰቃየኛል።   በሰዎች ተከብቤ እንኳ በመሀላቸው የለሁም። ሁሉም ያወሩኛል፣ ይስቃሉ፤ እኔ ግን ውስጤ የናፈቀሽ ልቤ ካንቺው ጋር ስለቀረ ዝምታን መርጫለሁ። ሰው አካሉ እያለ ነፍሱ ልትሞት እንደምትችል ያወቅኩት አንቺን ካጣሁኝ በኋላ ነው። ፈገግታዬ ከፊቴ ላይ ከጠፋ ቆየ፣ ውስጤ ግን ሁልጊዜም ያንቺን ስም እየጠራ ያለቅሳል። በጣም የሚገርመው፣ ጊዜ ሁሉንም ነገር ይፈውሳል ይላሉ። ነገር ግን እኔ ጋር ጊዜ የቆመ ነው የሚመስለው። ካንቺ ጋር ያሳለፍናቸው ጊዜያቶች በትዝታ እየመጡ ልቤን በየቀኑ አዲስ ስብራት ይሰብሩታል። አንቺን ማጣት ማለት በህይወት እያሉ እንደመሞት ያህል ከባድ እንደሆነ እያየሁት ነው። ምንም እንኳ ዛሬ እኔ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብሆንም፣ ያንቺ መደሰትና ሰላም መሆን ሁልጊዜም ጸሎቴ ነው። እኔን ያጣሽበት ቀን ላንቺ የደስታ ይሁን አይሁን አላውቅም፤ ለእኔ ግን የህይወቴ የመጨረሻው አስደሳች ምዕራፍ ያበቃበት ቀን ነበር። አሁንም ቢሆን… አንቺን ያጣሁበት ይሄ ባዶ ህይወቴ በየቀኑ ያንቺን መመለስ እየተመኘ ይጠብቅሻል። 😓

Silent Warrior ⚔️
Silent Warrior ⚔️
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 22 June 2026 05:41:57 GMT
89280
4627
102
813

Music

Download

Comments

tezube
ኤምራኬል🦋🦋🦋 :
ሁላችንም ታመናል ግን እየኖርን ነው?
2026-06-23 15:47:26
107
abielove.05
መንገደኛው🚶💚💛♥️🐦‍⬛🦜🐦🕊️ :
ወይኔ ለካ ሁላችንም ልባችን ውስጥ ተመሳሳይ እረመጥ ተዳፍኖ አለ
2026-07-23 17:38:16
3
amir.amix1
Amir(ኣስሊ)🌟⭐️✨✍️✍️✍️ :
ወንድም እሷ ለምን እና በምን ምክንያት እንደኣጣሃት ባላቅም እሷ ኣንተን እነዲህ ሁና ኣይታ እንደ ኣንተ በትዝታ ዉስጥ እየኖረች ትሆነለች እጣፍንታቹ ኣንድ ከልሆነ መለያየቱ ተቀበለዉ እና ሂወትህን ኑር የእናት ሞትም ይረሳ የለ በርታ በል ወንድም
2026-08-01 14:08:56
2
shelermansheler
ሺለሩ :
ሰሚ በሌለበት ማውራት እራስን ማድከም ሆኖብነውጂ ሁላችንም ባዶነን
2026-08-07 06:43:55
1
abdusadke2
A aziz abdu :
no words🥺
2026-06-23 21:44:49
5
hayoti73
@hayoti🥺...▩ :
🥺ናፋቃኛለች
2026-06-28 23:48:08
3
moni_1132
🍁𝗠𝗼𝗻𝗶💃✈️🇹🇷 :
ደና ነኝ
2026-06-24 06:28:45
7
y7059121gmail.com
Yoni(19)☦️ :
2026-06-24 08:48:05
2
yiba.man63
yiba man :
gen lmn
2026-06-29 20:40:00
1
shikur.seid.mekur
foriver UNITED :
ለህትም ይሆናል አደል😢😢😢😢
2026-06-30 14:45:21
2
emawus7
SUMU🍫 :
Kal yelegnm 💔😥
2026-06-22 17:07:15
6
yeshigold
yeshi gold :
🥺
2026-06-25 05:19:37
1
To see more videos from user @silentwarrior_et, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About