@yhbchawassa1952: #creatorsearchinsights YHBC Sunday Service⛪️ #እሁድ_የቃልና_የአምልኮ_ጊዜ (14–10–2018 ዓ.ም) በእግዚአብሔር ቃል፦ ፓስተር አፈወርቅ አበበ ርዕስ፦ መንፈስ ቅዱስ መነሻ ክፍል፦ ሐ.ሥራ 19፥1–20 መግቢያ፦ የኤፌሶን ቤ/ክ በእስያ ላሉ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት እናት ቤ/ክ ናች ብዙ አገልጋዮችና አስተማሪዎች እንዲሁም መሪዎች ይወጡባት የነበረች ቤ/ክ ነበረች። * ጳውሎስ ወደዚህች ከተማ ከመግባቱ በፊት አስቀድሞ አጵሎስ ገብቶ ነበረ፣ ይህም ሰው የእስክንድሪያ ሰው የሆነ የመፅሐፍ እውቀቱ የጠለቀ እና የበረታ ሰው ነበር። በዚህም ምክንያት ስለ ኢየሱስ በሚገባ የተረዳ እና ያወቀ ሰው ነበር። ሆኖም እውቀቱ ግን እስከ ዮሐንስ ጥምቀት ድረስ ብቻ ነበረ። የመንፈስ ቅዱስን ስራ ግን አልተረዳም ነበር። * መንፈስ ቅዱስ በሚመጣ ጊዜ ከነበርንበት ስፍራ ፈቀቅ፣ እልፍ ያደርገናል። አሜን! * በአጵሎስ አገልግሎት 12 ደቀመዛሙርትን አፍርቶ ነበር። (ሐ.ሥራ 19፥7) * ነገር ግን በአቂላ እና በጵርስቅላ ከቀድሞ ይልቅ የእግዚአብሔርን መንገድ(ስለ መንፈስ ቅዱስ) በገለጡለት ጊዜ፣ በነበረበት መቆየት አልፈለገም፣ ይልቁንም ወደ አካይያ እና ወደ ቆሮንቶስ ለመሄድ ተነሳ። * መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የተሰጠን ሰማያዊ ስጦታ ነው። * መንፈስ ቅዱስ ወደ ህይወታችን ሲመጣ አዳዲስ ነገር በህይወታችን ይሆናል። * በኤፌሶን ከተማ ምኩራብ አለ፣ ጎበዝ የሚባል መምህር አጵሎስ ነበረ። የኤፌሶን ከተማ ምን ትመስል ነበረ? #1, ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች የነበሩበት ከተማ ነው። * ስለዚህ ጳውሎስ ለዚህች ከተማ ከስብከት አስቀድሞ መንፈስ ቅዱስ ለዚህች ከተማ ያስፈልጋታል ብሎ አሰበ። , እልከኛ ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ ነበረች።(ሐ.ሥራ 19፥9) , ከተማይቱ አጋንንትና ክፉ መናፍስት የተቆጣጠሯት ከተማ ነበረች።(ሐ.ሥራ 19፥13) , አርጤምስ የተባለች ጣዖት ትምለክባት ከተማ ነበረች። ሐ.ሥራ 19፥27 "ሥራችንም እንዲናቅ ብቻ አይደለም፥ እስያ ሁሉ ዓለሙም የሚያመልካት የታላቂቱ አምላክ የአርጤምስ መቅደስ ምናምን ሆኖ እንዲቆጠር እንጂ፥ ታላቅነትዋም ደግሞ እንዳይሻር ያስፈራል።" * ስለዚህ እንዲህ ላለች ከተማ መሰበክ እና መነገር ያለበት ስለመንፈስ ቅዱስ ነው። ዮሐ 7፥37–39 "ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።" * በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተሳሳተ አመለካከት እና አስተሳሰብ የተጀመረው ዛሬ አይደለም ኢየሱስ በሚያገልግልበትም ዘመን ጋኔን አለበት ብለዋል፣ በሐዋርያትም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ ጉሽ(የሚያሰክር) መጠጥ ጠጥተዋል ብለዋል። * ጳውሎስ በከተማይቱ ያደረገው ሁለተኛው ነገር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ወንጌልን መስበክ ነበር። * ቃሉን የሚያፀና ድንቅ እና ተአምራት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መደረግ ጀመረ። የጳውሎስ አገልግሎት ውጤቱ ምን ሆነ? , በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ሆነ፤ ሐ.ሥራ 19፥17 " ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤" , የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤ ሐ.ሥራ 19፥17 "የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤" , እውነተኛ ተሐድሶ በአመኑ ሰዎች ዘንድ ሆነ፤ ሐ.ሥራ 19፥18 "አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።" * እውነተኛ ተሐድሶ በመንፈስ ቅዱስ አመካይነት ይመጣል። አሜን!!! , የጌታ ቃል አሸናፊ ሆነ፤ ሐ.ሥራ 19፥19–20 "ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ። እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።" YOUTUBE : https://www.youtube.com/channel/UCuNsT8SgIhau-u84nOvUAfw Facebook : https://www.facebook.com/profile.php?id=100064563617310&mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v Tiktok : https://www.tiktok.com/@yhbchawassa1952?_t=ZM-90XJq03HFm7... Telegram : https://t.me/YHBCHawassa በመወዳጀት ይከታተሉን፡ ፡ እናመሰግናለን!! #fyp #christiantiktok

Hawassa YeHiwot Birhan Church
Hawassa YeHiwot Birhan Church
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 22 June 2026 06:04:19 GMT
10760
1893
51
259

Music

Download

Comments

fsn0128
Fs² :
ቅዱስ የኔ አባ🖐️🖐️🙏🥰
2026-06-22 12:05:15
1
user6682906106955
jerrysilas :
Akeye yene wondm geta tsegawn yabzalh🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-22 11:28:13
1
emuyegeta3
emuyegeta3 :
ድንቅ ጊዜ ነበረን ክብሩን ጌታ ይውሰድ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-22 12:06:41
2
sselamawt
salina የእየሱስ ብቻቻቻ100% :
ተባርኩኩ🥰🥰🥰🥰
2026-06-22 08:41:36
1
birkteyjhon
@biruktey jhon :
sunday service 🥰🥰
2026-06-22 18:31:09
0
drxoru
drxoru :
አምልኮ ለጌታ!!!
2026-06-22 13:46:26
0
temesgenlegesse513
@Temu :
wooooow church...
2026-06-22 15:31:44
0
kidy582
kidy :
🙏🙏🙏🙏
2026-06-22 10:25:02
1
markozmt03
marko ZMT :
🥰🥰🥰
2026-06-22 06:42:01
1
lidyalemma2731
lidyalemma :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-23 04:25:53
0
userbibo42
@Bibo :
🥰🥰♥️
2026-06-23 04:08:13
0
zwdagim
Adisu❤️❤️king :
🤲🤲🤲🥰🥰
2026-06-23 08:26:48
0
beki7286
beki :
🥰🥰🥰🥰
2026-06-23 10:19:52
0
geni.ye.geta
Geni ye geta :
🥰🥰🥰
2026-06-23 06:26:49
0
yemisrach.dejene
Yemisrach Dejene :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-23 04:54:39
0
tige.man50
Tige man :
🥰🥰🥰
2026-06-23 04:49:51
0
tigsti.love
Tigsti Love :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-22 19:01:44
0
yafed.abreham
yafed abreham :
🥰🥰🥰
2026-06-23 07:39:30
0
habtamu.84
Habtamu✝️✝️❤️❣️ :
❤️❤️❤️
2026-06-22 20:39:33
0
hiraye6
hira :
🥰🥰🥰
2026-06-22 20:24:49
0
avisol8
Abenezer :
🔥🔥🔥
2026-06-23 12:30:10
0
yosi.man107
Yosi Man :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-22 16:59:31
0
betyyebalame
Betty,menase :
🙏🙏🙏🥰
2026-06-22 16:59:04
0
konjiye168
konjo✝️✝️ :
🙏🙏🙏
2026-06-22 16:03:08
0
abimerid0
@abimerid :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-22 06:08:41
0
To see more videos from user @yhbchawassa1952, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About