@tesemamukura: አንድ ሰው በእውነት እንደሚወድህ/እንደሚወድሽ እንዴት ታውቃለህ? ይህ ጽሑፍ አንድ ሰው በእውነት ሲወድህ የሚያሳዩ ምልክቶችን እና ፍቅሩ እውነተኛ መሆኑን እንዴት ማወቅ እንደምትችል ያስተምርሃል። አንድ ሰው ሲወድህ ታውቀዋለህ፤ ደግሞም በልብህ ይሰማሃል። ይህን የሚያረጋግጡ ብዙ ምልክቶች አሉ። ✅ ትኩረት አንድ ሰው ሲወድህ ትኩረት ይሰጥሃል። የምንወዳቸውን ነገሮች ትኩረት እንሰጣለን። ✅ እንክብካቤ አንድ ሰው ሲወድህ ስለ ደህንነትህና ስለ ደስታህ ያስባል። ስለ ሕይወትህ የማይጨነቅ ሰው በእውነት ላይወድህ ይችላል። ✅ ግንኙነት አንድ ሰው ሲወድህ ምንም ያህል ቢጠመድ ከአንተ ጋር መነጋገርን ይፈልጋል። የሚወዱትን ሰው ድምጽ መስማት ደስታ ነው። ✅ መስጠት ፍቅር በተፈጥሮው መስጠትን ያመጣል። ገንዘብ ባይሆንም እንኳ አንድ ሰው ሲወድህ የሆነ ነገር ይሰጥሃል። ፍቅር ሁልጊዜ ራሱን ለመስጠት ይፈልጋል። ✅ አብሮ ጊዜ ማሳለፍ አንድ ሰው ሲወድህ ከአንተ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ይናፍቃል። የምንወደውን ሰው መቅረብ እንፈልጋለን። ✅ መስዋዕትነት የፍቅር ትልቁ ማስረጃ መስዋዕትነት ነው። ፍቅር ራሱን ብቻ አያስብም። የምትወደውን ሰው ለማስደሰት ራስን መሰዋት ይፈልጋል። ✅ ትዕግሥት አንድ ሰው ሲወድህ በድክመቶችህና በችግሮችህ ውስጥ ታጋሽ ይሆናል። ✅ ጥበቃ አንድ ሰው ሲወድህ ከጉዳት ለመጠበቅ ይጥራል። ✅ ደግነት ፍቅር ደግ ነው። አንድ ሰው በቀለል እና በክብር ይይዝሃል። ✅ ልብን መክፈት አንድ ሰው ሲወድህ ስሜቱን ይገልጥልሃል። ድክመቶቹን እና ውስጣዊ ስሜቶቹን ለማሳየት አይፈራም። ✅ ድጋፍ አንድ ሰው ሲወድህ በሚችለው ሁሉ ይደግፍሃል፤ በስሜት፣ በመንፈስ፣ በገንዘብ ወይም በሌላ መንገድ። ✅ ኢንቨስትመንት አንድ ሰው ሲወድህ ከገና የተሻለ ሰው እንድትሆን በአንተ ላይ ጊዜውን፣ ጉልበቱንና ሀብቱን ያፈሳል። ፍቅሩ እውነተኛ መሆኑን እንዴት ታውቃለህ? ✅ ጊዜ ስጥ ማንም ሰው ጭምብል ለዘላለም ሊያደርግ አይችልም። ሰዎችን በጊዜ ፈትናቸው።ከጊዜ በኋላ እውነተኛ ማንነታቸው ይገለጣል። እሱ “ከልቤ እወድሻለሁ” ቢልሽ፣ አንቺ የሕይወቴ ብርሃን ነሽ ቢልሽ፣ ችግር የለም። ግን ጊዜ ስጪው።እሷም “ያለአንተ መኖር አልችልም” ብትልህ ችግር የለም። ግን ጊዜ ስጣት።ጊዜ እውነትን ያጋልጣል። ✅ በፈታኝ ጊዜ ነገሮች ጥሩ ሲሆኑ መውደድ ቀላል ነው። ነገር ግን ፈተና ሲመጣ ፍቅሩ ይፈተናል። በጣም ስትታመም፣ ፍቅሩ ይቀጥላል? ስራህን ስታጣ ወይም የገንዘብ ችግር ሲደርስብህ አብሮህ ይቆያል? ምንም ነገር በሌለህ ጊዜ አብሮህ ይሆናል ወይስ ይተውሃል? አትቸኩል።ጊዜ ስጥ።ጊዜ ገላጭ ነው። ከጊዜ በኋላ ፍቅሩ እውነተኛ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ታውቃለህ። ፍቅር ይጸናል።ፍቅር ታጋሽ ነው።ፍቅር አይቸኩልም። ❤️ ፍቅር ይኑርባችሁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ በጥበብና በንቃት ተመላለሱ። via Tsion Mathiyos
tesema
Region: ET
Monday 22 June 2026 15:15:13 GMT
Music
Download
Comments
dawit :
እውነት ነው
2026-06-22 19:29:01
0
To see more videos from user @tesemamukura, please go to the Tikwm
homepage.