@alfurqan449: #قران_كريم #allihamdullilah #امي #امي #الله የዐሹራእ ጾም‼ ========== (የነብዩ ﷺ ጉጉት እና የሰለፎች ጥልቅ ማስተንተን!) || ✍️ በእስልምና አስተምህሮ ውስጥ የሙሐረም ወር፣ በተለይም የዐሹራእ (የሙሐረም 10ኛ) ቀን እጅግ የላቀ ደረጃ አለው። ይህ ቀን ያለፈውን አንድ ዓመት ወንጀል የሚያስምር ታላቅ ጸጋ ነው። የዚህን ቀን ታላቅነትና ጾሙን በተመለከተ ትክክለኛ ሐዲሦችን እና የዑለማዎችን ድንቅ ንግግሮች ከነ ምንጫቸው እንመልከት፦ 1⃣ የነብዩ ﷺ ብርቱ ጉጉት፦ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ይህን ቀን ለመጾም ልዩ ጉጉት ነበራቸው። ታላቁ ሶሐባህ ዐብዱ-ል'ሏህ ኢብኑ ዐባስ ይህን የነብዩን ﷺ ጉጉት ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፡- «مَا رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَتَحَرَّى صِيَامَ يَوْمٍ فَضَّلَهُ عَلَى غَيْرِهِ، إِلَّا هَذَا الْيَوْمَ ؛ يَوْمَ عَاشُورَاءَ، وَهَذَا الشَّهْرَ. يَعْنِي شَهْرَ رَمَضَانَ.» «ነብዩ ﷺ ከሌላው አብልጠው የዚህን ቀን (የዐሹራእን) እና የዚህን ወር (የረመዿንን) ጾም ለመጾም እንደሚጓጉት ለሌላ ቀን ሲጓጉ አላየሁም።» 📚[ሶሒሕ አል-ቡኻሪይ፡ 2006፣ ሶሒሕ ሙስሊም፡ 1132] 2⃣ «ካለፈ አይመለስም!» 🎀 የቀደምት ሰለፎች ለዐሹራእ ጾም የነበራቸው ቦታ አስገራሚ ነበር። ታላቁ ታቢዒይ ሙሐመድ ኢብኑ ሺሀብ አዝ-ዙህሪ በጉዞ ላይ እያሉ የዐሹራእን ቀን ጾሙ። በዚህ ጊዜ ሰዎች ተገረሙና እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው፡- (… فقيل له: لم تصوم وأنت تفطر في رمضان في السفر ؟! فقال: إن رمضان له عدة من أيام أخر، وإن عاشوراء يفوت.) «በረመዿን ወር በጉዞ ላይ ሆነህ ጾም እየፈታህ፣ ዛሬ (በጉዞ ላይ) ለምን ትጾማለህ?» ተብለው ሲጠየቁ፤ «ረመዿን በሌሎች ቀናት (ተቆጥሮ) ቀዷ ይወጣል (ይከፈላል)፤ የዐሹራእ ጾም ግን ካለፈ ያመልጣል (ቀዷ አይወጣም)!» ብለው መለሱ።» 📚 [ሸዕቡል-ኢማን ሊል-በይሀቂይ፡ 3518] ⬇️ በእርግጥም የረመዿንን ጾም በህመም ወይም በጉዞ ምክንያት የፈታ ሰው በሌላ ጊዜ መክፈል ይችላል። የዐሹራእ ጾም ግን ዓመት ጠብቆ የሚመጣና ቀዷ የሌለው በመሆኑ፣ ይህ ታላቅ ምንዳ እንዳያመልጠን ሰለፎች እስከዚህ ድረስ ይጓጉለት ነበር! 3⃣ ዓመትን በዒባዳህ መዝጋትና በዒባዳህ መክፈት! 🎀 ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑ ረጀብ አል-ሐንበሊ አላህ በሰጣቸው ጥልቅ እይታ፣ የዓመቱ መጨረሻ (ዙል-ሒጃ) እና የዓመቱ መጀመሪያ (ሙሐረም) ወራት ውስጥ ስላለው ጾም እንዲህ ይላሉ፡- «من صام من ذي الحجة وصام من المحرم، فقد ختم السنة بالطاعة وافتتحها بالطاعة فيرجى أن تكتب له سنته كلها طاعة، فإن من كان أول عمله طاعه وآخره طاعة فهو في حكم من استغرق بالطاعة ما بين العامين.» «ከዙል-ሒጃ (ባለፈው ዓመት መጨረሻ) እና ከሙሐረም (በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ) የጾመ ሰው፤ ዓመቱን በዒባዳህ (በታዛዥነት) ዘግቶ፣ አዲሱን ዓመትም በዒባዳህ ከፈተ ማለት ነው። በመሆኑም ዓመቱ ሙሉ በዒባዳ እንዳሳለፈ ይጻፍለታል ተብሎ ተስፋ ይደረጋል። ምክንያቱም የመጀመሪያውም ሆነ የመጨረሻው ስራው አላህን መታዘዝ የሆነ ሰው፣ በሁለቱ ዓመታት መካከል ያለውን ጊዜ ሙሉ በዒባዳ እንዳሳለፈ ይቆጠርለታልና።» 📚 [ለጧኢፉል መዓሪፍ ሊብኒ ረጀብ] ⏱ የዚህ ዓመት የዐሹራእ ጾም ቀናት! 📅 ነብዩ ﷺ ዐሹራእን ጾመው፣ ከአይሁዶች ለመለየት ሲሉ ቀጣዩ ዓመት ከደረሰ 9ኛውንም ቀን (ታሱዓእን) አብረው እንደሚጾሙ ተናግረዋል። በመሆኑም፣ የዘንድሮውን የሙሐረም 9ኛ እና 10ኛ ቀን የጾም ቀጠሯችንን እንደሚከተለው አድርገን ይህን የዓመት ወንጀል የሚያስምር ታላቅ ጸጋ እንቋደስ፦ ✅ ታሱዓእ (9ኛው ቀን)፦ ረቡዕ፣ ጁን 24 ✅ ዐሹራእ (10ኛው ቀን)፦ ሐሙስ፣ ጁን 25 አላህ ያለፈውን ዓመት ወንጀላችንን የምንማርበት፣ አዲሱን ዓመትም በዒባዳና በኸይር የምንጀምርበት ያድርግልን! (እነዚህን ቀናት ጓደኛ እና ቤተሰባችሁ እንዳይረሱት ሼር በማድረግ የኸይር ሰበብ ሁኑ!) 🤍 t.me/MuradTadesse
Al furqan islamic chanal
Region: ET
Monday 22 June 2026 19:35:08 GMT
Music
Download
Comments
fu''💫😎😎 :
እንሻአለህ🤲🤲🤲
2026-06-23 19:44:16
0
የነ ገን ማን ያውቃል :
ኢንሻአህ❤❤❤
2026-06-23 19:40:02
0
user5452272927685 :
ኢንሻአላህ💜❤️💜❤️💜
2026-06-23 16:42:23
0
nishnish850 :
❤️❤️❤️
2026-06-22 21:48:35
0
mubarikredi1 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰😂😂😂
2026-06-23 03:29:04
0
Ziku :
🥰🥰🥰
2026-06-22 20:16:15
0
mohammes Ebrahim :
🥰🥰🥰
2026-06-23 12:40:39
0
To see more videos from user @alfurqan449, please go to the Tikwm
homepage.