@emlinhdoxinh38: #xuhuong

Em Linh Đồ Xinh 🤍
Em Linh Đồ Xinh 🤍
Open In TikTok:
Region: VN
Tuesday 23 June 2026 14:10:04 GMT
311
2
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @emlinhdoxinh38, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

በ15ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በጀርመን ኑረምበርግ ከተማ ውስጥ፣ አንድ 18 ልጆች ያሉት ድሃ ቤተሰብ ይኖር ነበር። ከእነዚህ ልጆች መካከል አልብሬክት እና ወንድሙ አልበርት (አንዳንዴም የቅርብ ጓደኛው ተብሎ ይነገራል) ታላቅ የኪነ-ጥበብ ችሎታ እና ስዕል የመማር ከፍተኛ ህልም ነበራቸው። ነገር ግን አባታቸው የሁለቱንም የትምህርት ወጪ መሸፈን አይችልም ነበር። ስለዚህ ሁለቱ ወንድማማቾች አንድ ስምምነት ላይ ደረሱ። ሳንቲም በማውጣት አንደኛው ወደ ማዕድን ማውጫ ገብቶ እየሰራ የሌላኛውን የትምህርት ወጪ ሊሸፍን፣ የተማረው ደግሞ ትምህርቱን ጨርሶ ስኬታማ ሲሆን ተመልሶ የሰራተኛውን ወንድሙን ትምህርት በስዕል ሽያጭ ገቢ ሊያስተምር ተስማሙ። ሳንቲሟ ተወረወረች፤ አልብሬክት አሸነፈ። አልብሬክት ወደ አካዳሚ ገብቶ ትምህርቱን ሲከታተል፣ ወንድሙ አልበርት ደግሞ ለአራት ዓመታት በአደገኛው የማዕድን ቁፋሮ ውስጥ እየሰራ ወንድሙን አስተማረ። አልብሬክት በትምህርቱ እጅግ የላቀና ስኬታማ ሰዓሊ ሆኖ ተመረቀ። ስዕሎቹም በከፍተኛ ዋጋ መሸጥ ጀመሩ። አልብሬክት ወደ ቤተሰቡ ተመልሶ ትልቅ የራት ግብዣ አዘጋጀ። በግብዣው ላይም ተነስቶ ለወንድሙ እንዲህ አለው፡-
በ15ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በጀርመን ኑረምበርግ ከተማ ውስጥ፣ አንድ 18 ልጆች ያሉት ድሃ ቤተሰብ ይኖር ነበር። ከእነዚህ ልጆች መካከል አልብሬክት እና ወንድሙ አልበርት (አንዳንዴም የቅርብ ጓደኛው ተብሎ ይነገራል) ታላቅ የኪነ-ጥበብ ችሎታ እና ስዕል የመማር ከፍተኛ ህልም ነበራቸው። ነገር ግን አባታቸው የሁለቱንም የትምህርት ወጪ መሸፈን አይችልም ነበር። ስለዚህ ሁለቱ ወንድማማቾች አንድ ስምምነት ላይ ደረሱ። ሳንቲም በማውጣት አንደኛው ወደ ማዕድን ማውጫ ገብቶ እየሰራ የሌላኛውን የትምህርት ወጪ ሊሸፍን፣ የተማረው ደግሞ ትምህርቱን ጨርሶ ስኬታማ ሲሆን ተመልሶ የሰራተኛውን ወንድሙን ትምህርት በስዕል ሽያጭ ገቢ ሊያስተምር ተስማሙ። ሳንቲሟ ተወረወረች፤ አልብሬክት አሸነፈ። አልብሬክት ወደ አካዳሚ ገብቶ ትምህርቱን ሲከታተል፣ ወንድሙ አልበርት ደግሞ ለአራት ዓመታት በአደገኛው የማዕድን ቁፋሮ ውስጥ እየሰራ ወንድሙን አስተማረ። አልብሬክት በትምህርቱ እጅግ የላቀና ስኬታማ ሰዓሊ ሆኖ ተመረቀ። ስዕሎቹም በከፍተኛ ዋጋ መሸጥ ጀመሩ። አልብሬክት ወደ ቤተሰቡ ተመልሶ ትልቅ የራት ግብዣ አዘጋጀ። በግብዣው ላይም ተነስቶ ለወንድሙ እንዲህ አለው፡- "አሁን ተራው ያንተ ነው ውድ ወንድሜ! እኔ ስዕሎቼን እየሸጥኩ አስተምርሃለሁ፣ አንተ ወደ ትምህርት ቤት ግባ።" ሆኖም አልበርት እያለቀሰ የተጎዱትን እጆቹን አሳየው። በማዕድን ማውጫው ውስጥ በነበሩት አራት ዓመታት ውስጥ የእጆቹ አጥንቶች ተሰብረው፣ ጣቶቹም እጅግ ተጎድተው ስለነበር ብሩሽ መያዝ ቀርቶ ብርጭቆ በቅጡ ማንሳት የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። ወንድሙን ለማስተማር ሲል የራሱን ህልም መስዋዕት አድርጎ ነበር። አልብሬክት የወንድሙን ውለታ እና የተጎዱ እጆቹን ለመዘከር፣ እነዚህን ሻካራና የተጎዱ፣ ነገር ግን ለወንድሙ በምስጋናየተዘረጉ የፍቅር እጆች በ1508 ዓ.ም. ሳለ። ይህ ስዕል የወንድማማችነት ፍቅር፣ የመስዋዕትነት ተምሳሌት ሆኖ እስከ ዛሬ ይኖራል።#mestilibra #bible #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #quran #ቤተእስራኤልነኝ

About