@whatiff77: የነዳጅ እጥረት ከፈጠረብን አንዳጅ ድርጊቶች መካከል ዱርዬው አሸዋ ንግድ መስፋፋትና የአሸዋ ልኬት ቅሸባ ይገኝበታል። በተለምዶ ዱርዬው_አሸዋ የሚባለው ከወንዝ ከሚገኘው የታጠበ አሸዋ ሳይሆን በተለምዶ ዳካ የሚባለውን ከአለምጤና አካባቢ ተቆፍሮ የሚጫን አሸዋ መሰል ነገር ነው። ይህ አሸዋ በርካሽ ዋጋ አዲስ አበባ ይመጣል። የመተሃራና ሌሎች የወንዝ አሸዋም ይመጣና ሜዳ ላይ ይገለበጣል። ከዛም እንደ ግዢው ሁኔታ እየተቀላቀለ በሲኖዎች ላይ ይጫንና እላዩ ላይ ውሃ እስኪጠግብ ይለቀቅበትና ከመተሃራ ወይ ከአንዱ የወንዝ የመጣ አሸዋ ተብሎ በየፕሮጀክቱ ይራገፋል። በዚህም ይገነባል። አደጋ አለው! ይህ የአሸዋ ንግድን በስሱ እንዳጠናሁት በሚከተለው መልክ የገበያ ስርዓት ልኬትና ስያሜ ወጥቶለት የሚከናወን ነው ። ገዢው አያውቅም። አሸዋ አቅራቢ ሹፌሮች ተግባብተው ይተገብሩታል። ለእንባቢ ለማሳየት ያህል የሚከተሉት የአሸዋ ግብይት ቋንቋቸውና መለያቸው አቅርቤያለሁ:- ፩) ዳካ በዳካ :- ሙሉ ለሙሉ የዳካ ( ድክሞ) አሸዋ ውሃ ተርከፍክፎበት ለተንከራፈፈ ኮንቴ ወይም ምታም ለሆነ ፐርቼዘር በርካሽ በወቅታዊ ዋጋ 110,000.00 ብር አካባቢ ይሸጣል። ፪) ዳካ በበለጬ :- እዚህ ቦታ ላይ "በለጬ" የበርጫው ሳይሆን የዳካ አሸዋን ነጣና ገርጣ ያለ ቀለም የሚቀይር ቀጠንጠን ያለች አሸዋ መጠሪያ ነው። ይቺ በለጬ የምትባል አሸዋ ዳካው ላይ ተጨምራ ተማስሎ ውሃ ጠጥቶ ለገበያ ይቀርባል። ፫) 20 በ 80:- የሚባለው 20% የወንዝ አሸዋ 80% ዳካ ተቀላቅሎ የሚሸጥ ፬) 50 በ 50 :- ይህ ግማሽ የወንዝ አሸዋ ግማሽ የ ዳካ አሸዋ ቅልቅል ሲሆን ውሃ ጠግቦ መቀላቀሉ ለመለየት በሚከብድ ሁኔታ ለፕሮጀክት የሚቀርብ ሲሆን ከ 120ሺህ-130ሺህ ብር ለሳይቶች ይቀርባል። ሌላም....ሌላም ድብልቅልቅ ...... ፈተና ነው።አደጋ አለው! ወገኖቼ ይሄ ተግባር በድብቅ የሚከናወን ሳይሆን በቀን በጠራራው ጸሃይ ሳይቀር በሃላል እየተከናወነ ያለ ማንም ሰው ከጋርመንት ቱሉዲምቱ ሲሄድ ኮዬ አካባቢ ሲኖዎች እንደ ነዳጅ ቀጂ ተሰልፈው ወጠምሻ ወጣቶች በአካፋ እየቀላቀሉ የሚጭኑት አንዳንዶችም በሎደር ቀላቅላው ሲጭኑ እዛው ወንዝ ገብተው ውሃ አጠጥተው በሸራ ሸፍነው ወደ መሃል ከተማ ሲወስዱት የሚታይ ጉዳይ ነው። ይህንን ለመጻፍ የወሰንኩት ሰሞኑን በኮዬ መስመር ስጓዝ ከአሸዋ ማቀላቀያ ቦታዎች ጭኖ የወጣ መኪና ከፊት ለፊታችን ተጉዞ አንድ የተዘጋጀ አርማታ (Ready Mix) አቅራቢ ግቢ ሲገባ በመመልከቴ ነው። እንደ አንድ መሃንዲስ በዚህ መሰል አሸዋ የተሰራ ህንጻ በቸርነቱ እንጂ በስትራክቸሩ እንደማይቆም እርግጠኛ ነኝ። በተጨማሪም አንድ የአሸዋ ቅሸባ ላክልና ልውጣ። በትክክለኛው ልኬት የብዙዎቹ የሲኖ አሸዋ ልኬት 16.7 ሜኩብ አካባቢ ነው። ነገር ግን ጥቂት የማይባሉት የዱርዬው አሸዋ አቅራቢዎች መጫኛቸው ላይ በላሜራ የተለበጠ መቀነሻ አሰርተውበት የሚያቀርቡት አሸዋ ልኬት ከ12ሜኩብ አይበልጥም። ይህም በእያንዳንዱ ቢያጆ እስከ አራት ሜኩብ አሸዋ ይቀሸባል ማለት ነው። ይህም 25% ቅሸባ ነው። እናማ ገንቢና አስገንቢ ወገኔ ሆይ!!! አሸዋ ስትገዙ በተቻለ መጠን ከወንዝ መምጣቱን ተከታተሉ ከተራገፈ በኋላም ለክታችሁ ክፈሉ። በጥራትም በመጠንም እትቀሸቡ ንቁ! ከታች ያለው ፎቶ በከተማችን ካሉ የአሸዋ ማቀላቀያ ቦታዎች በአንዱ ያነሳሁት ነው። ምንጭ። ደሳለኝ ከበደ። ሲቪል መሀንዲስ፣ ገንቢ፣ አማካሪ። #viralvideo #fyp #tiktokviral #architecture #ConstructionTikTok

2018
2018
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 27 June 2026 17:23:00 GMT
19850
487
8
150

Music

Download

Comments

bekalu_777
መላጣው :
I remember a business providing well prepared, sampled and tested sand but it didn't take long to go out of business. any idea to collab or start the business again
2026-06-28 05:03:43
11
kasmankas0
kasslovedo :
nice, keep it up.
2026-06-28 03:37:21
6
amhaser
Amha Sertse :
The terrible greed/ demand supply gap!
2026-06-28 06:23:53
3
beki..066
beki. meko :
control government....
2026-06-28 05:58:35
3
tractors.for.renta8
don't take me seriously :
the detective keep it up
2026-06-27 22:14:25
3
pamfalonekal
ቃለአብ :
👍👍👍
2026-06-27 19:08:35
1
To see more videos from user @whatiff77, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About