@comeonhayati2: እንደምታፈቅረኝ አይኗ ላይ አውቅባታለሁ... እንስፍስፍ ናት።ለሰአታት እንኳ ተራርቀን ስንገናኝ ለወራት የተጠፋፋን ያህል ጥምጥም ትልብኛለች። ሁሉ ነገሯ እውነት ነው ...ማስመሰል አታቅም ፤እንደውም አንዳንዴ እንደት ትንሽዬዋ ልጃችን የምታየኝ ይመስለኛል።ስትንከባከበኝ አትሰለችም።ከፍቷት እንዳያት አትፈልግም!!ሳቋን እንጂ እንባ እና ህመሟን እንደሸሸገቺኝ ነው... አመመሽ እንዴ?? ደና ነሽ?? እላታለሁ የሷ መልስ ሁሌ ደና ነኝ ነው። ግን'ኮ ውሸቷን እንደሆነ አውቅባታለሁ፤ ብዙ ጊዜ በለሊት ተነስታ ሽንት ቤት ስታቃስት ደርሼባታለሁ። ጭራሽ ሰውነቷ እየመነመነ እየጠቋቆረች ስትመጣ ሀኪም ቤት እንድንሄድ ብለምናትም መልሷ እንደተለመደው ደና ነኝ ብቻ ነው። አንድ ቀን ግን ለስራ በጠዋት ስነሳ አጠገቤ አጣኋት። ብዙ ጊዜ ቀድማኝ ስለምትነሳ አልገረመኝም፤ እየጠራኋት ጓዳ ብሄድ መኝታ ቤት ብገባ የልጃችን ቤት ብፈልጋት የለችም። ቤቱ ፀጥ ረጭ ብሏል የቀረኝ ሽንት ቤት ነበር'ና ወደዛው ሳመራ ሽንት ቤቱ ገርበብ ብሎ ታየኝ ብዙም ሳይቆይ ትከሻዬን እየከበደኝ በሩን እንደከፈትኩት ፍቅሬ ተዘርራ አየኋት። በቅፅበት በድን ሆኜ ወደመሬት ተንሸራተትኩና ቶሎ ቶሎ እጠራት ጀመርኩ፤ ሰውነቷን እየናጥኩ ልቀሰቅሳት ሞከርኩ፣ እሷ ግን ቀድማኛለች! ሞታለች። ምን አመመሽ፣ ምን ቸገረሽ፣ ምን ልሁንልሽ፣ ሳልላት ሳላስታምማት ጥላኝ ጠፍታለች.... ፍቅርዬን ከቀበርኳት ሳምንት በኋላ ቤቱ በድኖ ሲያበድነኝ ለመፅናናት መፅሀፍ ቅዱሴን ገለጥኩ... የመጀመርያ ገፅ ላይ ብጣሽ ወረቀት ተቀምጣለች ደብዳቤውን አነበው ገባሁ... እንዲህም ይላል፤ "የኔ ውድ ባል እባክህ አትዘንብኝ ህመሜን ላንተ ከነገርኩህ ቀድመከኝ ትሞታለህ።እየተደበቅኩህ ህክምና ስከታተል ነበር ግን አልሆነም ሞት ግድ ነው...ለኔ ህይወት ማለት ሳቅህን ማየት ነው ።መታመሜን አውቀህ ብሞት ኖሮ ሞቴ እረፍ ሳይሆን ስቃይ ነው!!እንባህን ማየት ሲኦልን የማየት ያህል ያስፈራኛል... የኔ ውድ እኔ ብሞት እንኳ አለሁ ምክንያቱም አንተና ልጄ ሁለተኛ ነብሴ ናችሁ።እድሜ አጉድሎኝ ህይወትህን ስላጎደልኩብሽ ይቅር በለኝ...እንደገና 10ሬ ብፈጠር ማገባው አንተን ነው...የኔ ውድ ባል አደራ ራስህን አበርታ" የሚል ነበር፣ በቃ ተለያየን.........#vi#foryou #fyp
yuti estanbul 💜
Region: SA
Sunday 28 June 2026 02:25:42 GMT
Music
Download
Comments
Elu Ye :
🥰🥰🥰
2026-06-28 04:02:26
0
@👑 mita🦋 :
🥹🥹🥹
2026-06-28 03:12:49
0
ችሎማለፈእዴትዴሰይላል💌👌 :
😥😥😥
2026-06-28 02:42:41
0
🧿👸🏽أميرة الحبشة 🤍 :
🥰🥰🥰
2026-06-28 02:29:02
0
★彡Imran彡★ :
🥺🥺🥺
2026-06-28 06:07:10
0
To see more videos from user @comeonhayati2, please go to the Tikwm
homepage.