@aj.ethiopia: 62 ነፍሳትን ከአሰቃቂ አደጋ ያተረፈ ቆራጡ ሹፌር! ሰኔ 11 /10/2018ዓ.ም መነሻውን አአዲስአበባ መድረሻውን ደደብረማርቆስ በማድረግ ከጠዋቱ 12:00 ጉዞ የጀመረው ታታ ባስ ፍቼ ሲደርስ እጀባ ስለነበር ከኋላ የነበሩ ተሽከርካሪዎችን ለመጠበቅ ይቆማል። ከደቂቃዎች በኋላ ሁሉም ባሶች ተሰባሰቡ። ታጣቂዎች በፓትሮል ሲቀድሙ ሁሉም ባሶች ጉዞ ይጀምራሉ። የእኛ ባስ ከመሐከል ላይ ሆኖ በከፍተኛ መጠባበቅ ወይም መቀራረብ ጉዞው ይጀመራል። ትንሽ ተጉዘን አሊ ዶሮ እሚባል አካባቢ ቁልቁለቱ ላይ ስንደርስ የእኛ ሹፌር በተደጋጋሚ ክላክስ ያደርግ ጀመር። ሌሎች ከፊት ያሉ ባሶች ጥግ በመያዝ የእኛን ባስ ማሳለፍ ጀመሩ። ፍጥነቱ በጣም አይሏል። በመካከል ሲኖ አለ እሱን ለትንሽ አለፈው ።ሰው በሁኔታው ተደናገጠ ሁለቱም ረዳቶች ዘለው ወጡ ታኮ ማድረግ ጀመሩ ታታ ባሱ ግን ዘለለው አሁንም ሲያደርግ ይዘለዋል። በዚህ መንገጫገጭ ህዝብ እየጮሀ መዝለል ጀመሩ በቃ ሽብር ሆነ ግማሹ በመስኮት ይዘላል ግማሹ በበር ይዘላል እየዘለለ ወርዶ የተጋጋጠው ህዝብ ቁስሉ ሳይሰማው ድንጋይ እየተሸከመ ታኮ ማድረጉን ተያያዘው ጩኸቱ በርክቷል .. ሹፌሩ መኪናውን ከአስፓልት አውጥቶ ወደ ተራራው አንደረደረው። መንገዱን ቀይሶ ወደ ተራራው ከቀየሰው በኋላ ፍጥነቱ ቀነሰ። እኔ ግን ታማሚውን ወንድሜን ገድፌ ይዤ ነበርና የአምላክን ትዕዛዝ እየተጠባበቅኩ በመሀከል አማትባለሁ። በጎኔም ታማሚ ወንድሜን አበረታታለሁ። በመቀጠልም ከተራራው ጋር ከመጋጨቱ በፊት ህዝቡ ሁሉም ባለበት ማርያም፣ አላህ ማለቱን ቀጠለ። ወጣቱ እየዘለለ ወረደ ቀድመው በሩ ተከፍቶ ነበርና የዘለሉት ወደኋላ ብሎ ህዝብ እንዳያልቅ ድንጋይ እየተከተሉ በጎማው ስር ይወረውራሉ። ሹፊሩ ግን ምንም ሳይሸበር መኪናው በቅፅበት ቆመ። ግማሹ በደስታ ይጨፍራል። ከተራራው ማዶ አስፓልቱ ዳር ህዝቡ እየጮኸ ይመጣል። ቀድመው የዘለሉት ያሻሻሉ። ሆኖም ግን አንዲትም ነፍስ አልጠፋችበትም። ከቆመ በኋላ ሹፌሩ ወረደና ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ግማሹ ጀግናችን ይለዋል። ግማሹም በምን ቀን ነው እያለ ቀኑን ይረግማል። የተጋጋጠውም አርፈን ብንቀመጥ ይላሉ። በመቀጠል ሰዎች ተሰብስበው ሹፌሩን ሲጠይቁት ፍሬኑ እንደተበጠሰበት ሲናገር ሁሉም ጩሆ አለቀሰ። ግማሹም ሳመው፣ አደነቀው እኔና ወንድሜ ግን ይህንን ሁሉ በመኪናው ውስጥ ሆነን እንታደማለን። መኪናው አልተጎዳም ሆኖም ከፍቸ መካኒኮች መጠው ፍሬኑና አንዳንድ ቴክኒካዊ ችግሮች ተስተካክለው በሚሊሻዎችና በፀጥታ ሀይሎች እጀባ በድጋሚ መኪናው በሰላም ወጥቶ ጉዞ ጀመርነ። ደጀን ከመግባታችን በፊት አባይ በርሃ ላይ እያለን ቅፅበቶቹን ሁሉ አሰላሰልኩ ፍሬኑ ከተበጠሰ ቆይቷል እሱ ግን ዝምታን መርጧል። ምክንያቱም ሰው ከሰማ ተደናግጠው እየዘለሉ ይወድቁብኛል ብሎ ሰግቶ ነው ። ከዚህ ሁሉ በኋላ በጉዟችን ረዳቱ እየሳቀ ከኋላው በር እየተንደረደረ ሂዶ ሙዚቃ ከፈተ። ተሳፋሪው በደስታ እየጨፈረ ሰርግ አስመሰለው። አይይ'' የሰው ልጅ ሂወት ከሀዘን ወደ ደስታ እንደፔንዱለም መወዛወዝ ነው'' ያለው ፈላስፋ ልክ ነው። አባይ በርሃ፣ 🚌ደጀን እስከ ደብረማርቆስ እየተጨፈረ ደረስነ። አምላክ ይመስገነው ታማሚውን ወንድሜን በሰላም ይዤው ገብቼ ከቀናቶች በኋላ አምላክ አልፈቀደምና ከዛ ከመዓቱ ሁሉ አውጥቶ በክብር በተወለደበት ቀዬ አፈሩን ለመቅመስ በቃ ሁሉም ለበጎ ነው ወንድሜ አምላክ ያፅናህ አንተንስ አጠንህ ነበርንኮ የኔ ወንድም ምላክ ያፅናህ ወንድሜዋ። ተመስገን ሁሌም አምላክ የፈቀደው ብቻ ይሆናል።ስለእውነት እንዲህ አይነት ልበ ሙሉና ቆራጥ ሹፊሮችን ልናመሰግናቸው ይገባል። Via፦ Mitiku Essayas ከቤንሻንጉል መተከል

AJ Ethiopia
AJ Ethiopia
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 29 June 2026 08:14:40 GMT
185869
8424
189
308

Music

Download

Comments

dbbb733
Tiger :
ሰለ ሆነውም ስለ አልሆነውም እግዚአብሔር ይመስገን!!
2026-06-29 12:18:20
156
feryat006
tsehay 🦋369Nt :
ለምን አለቀስኩ በስመአም
2026-06-29 14:02:05
70
tebebe34
Bisrat :
tmesgn
2026-06-30 11:43:31
0
yeshi4573
yeshi :
ስለሆነው ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን
2026-06-29 16:40:03
21
abdu.nuri18
መንገደኛው :
ስላ ሁሉም አልሃምዱሊላህ
2026-06-29 16:28:34
20
hana.bale.kinewa
ንስሯ🦅🇲🇱🥰💪 :
ለምን አለቀስኩ በ እመብርሃን
2026-06-30 06:36:03
8
satenawu1221
@Gebinanawu1212 :
እግዚአብሔር ይመስገን
2026-06-29 13:15:11
20
user2378075016963
ሰላም ለኢትዮጵያ :
እግዚአብሔር ይመስገን ለሁሉም እልልልልል 💯❤️❤️❤️❤️❤️
2026-06-29 08:55:44
16
allahisone637
Miss Fendisha 🍿🇹🇷🇹🇷 :
ሱብሀን አላህ
2026-06-29 13:46:12
5
user996170124321
abraraw :
ጀግና ሹፌር🥰🥰🥰🥰
2026-06-29 12:04:11
6
gedam23ayalew
ምዕራፍ ሦስት@(3) :
እር ይመስገን ጀግና ሹፌር🥰🥰🥰
2026-06-29 13:00:28
6
user4462221366002
Dejen kefiLe :
ፋጣሪ አስቀድም 🥰🥰🥰🥰 ሳላደቅ አላልፍም ትለያለ
2026-06-29 11:42:35
6
tigistberhanu175
Tigistberhanu175 :
እግዝአብሔር ይመስገን
2026-06-29 17:12:28
4
solomon.tesfa7
@Solomon kingdom :
2026-06-30 06:45:14
1
m6062550
Mቾ💙 :
እግዚአብሔር ይመስገን🙏
2026-06-29 15:05:46
3
enkuhane
NEW LIFE 💯 :
ለምን አለቀስሁ😭
2026-06-29 13:51:58
6
user9547143914068
user9547143914068 :
ስለ ሁሉምነገር እግዚአብሔር ይመስገን።
2026-06-30 11:52:40
1
ambaw1219
one day :
wowowowo
2026-06-30 06:30:09
0
aklil.leake
Aklil Leake :
ኡፍፍፍፍ እግዝአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏
2026-06-29 13:05:36
17
user5775316182349
marshe :
ስለሆነውም ስላልሆነወም ስለሚሆነዉም እግዚአብሔር ይመስገን
2026-06-30 10:50:08
1
tesfayemamo09
Tesfaye mamo :
2026-06-29 11:49:53
3
meadonic
Aroma ♎⚖️💝 :
እድሜ ይስጥህ🙏🙏🙏
2026-06-29 18:37:17
1
ketema.kell2
Akilock :
amen
2026-06-29 13:52:55
2
user8249513741278
MAGEE :
2026-06-29 13:44:58
1
12mikaileabati
ሄሉ🦋 :
ተመስገን 🥰🥰🥰🥰
2026-06-29 13:23:01
1
To see more videos from user @aj.ethiopia, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About