@ahmedtech257: በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 5 ዓመታት ተጀምረው የነበሩ ብዙ የንግድ ድርጅቶች ከስረው ከገበያ ወጥተዋል፡፡በርካታ ምክንያቶች ሊኖሩ ቢችሉም ዋና ዋናዎቹን ልንገርህ፡፡ 1. ደካማ የገንዘብ አያያዝ ብዙ ነጋዴዎች የግል ገንዘባቸውን ከንግድ ገንዘባቸው ጋር በመቀላቀል ለተለያዩ ወጭዎች በማዋልና ትርፍና ኪሳራቸውን ባለመለየት ወዲያውኑ ለኪሳራ ይዳረጋሉ፡፡ ስለዚህ ለንግድህ ማንቀሳቀሻ ሚሆን የብቻ አካውንት ክፈት ፡ብሩን መልሰህ ኢንቨስት አድርገው እንጅ አትብላው፡፡ ወጪዎችን እና ትርፍን በአግባቡ መቆጣጠር አስፈላጊ ነው፡፡ 2. የገበያ ጥናት ማነስ አብዛኛው ሰው ሌሎች ሲነግዱ ስላየ እና ያዋጣል ስለተባለ ብቻ ዘው ብሎ ወደ ንግድ ይገባል ፡፡በዚህ ምክንያት ወዲያውኑ ከስሮ ይወጣል፡፡ጎረቤትህ ሸቀጣ ሸቀጥ ሲሰራ ስላየህ አንተም ዘለህ አትግባ፡፡መጀመሪያ የደንበኞችን ፍላጎት በደምብ ተረዳ አጥና፡፡ስለዚህ ምትሸጣቸው ነገሮች ተፈላጊ መሆናቸውን መርምር፡፡ሱቅህን አንተን ሊገዙህ የሚችሉ ሰዎች ከሚበዙበት ቦታ አካባቢ ላይ ማድረክህን አትርሳ 3. ከፍተኛ ፉክክር በጣም ብዙ ፉክክር ያለበት ቢዝነስ ውስጥ መግባትም ለኪሳራ ይዳርጋል፡፡ከሰፈርህ 50 የቡቲክ ሱቅ መኖሩን እያወቅህ አንተም ከጎን ሂደህ ምትከፍት ከሆነ በቃ እየከሰርክ ነው፡፡ከአንተ በፊት የጀመሩት ፡ደምበኛ ይዘዋል ፡ተለምደዋል ፡የገበያውን ስልት ተረድተዋል፡፡ስለዚህ አንተ ሂደህ ስትገባ ከ50 ልምድ ካላቸው ነጋዴዎች ጋ መወዳደር አትችልም፡፡ የተለየ ነገር ይዞ አለመቅረብም ሌላኛው ችግር ነው፡፡ ሌላው ትንሽ ካፒታል ይዘህ ከጠንካራ ነጋዴዎች መሀል አትግባ ፡፡ 4. ደካማ አመራር እና ዕቅድ ግልጽ የሆነ የንግድ እቅድ አለመኖር ሌላኛው ችግር ነው፡፡ ንግድህ ጠንካራ እንዲሆን በእቅድ መመራት አለብህ፡፡ሱቅ የከፈትከው የት ለመድረስ አስበህ ነው የሚለውን ጥያቄ በእቅድህ መመለስ አለብህ፡፡ 5. በብዙ ካፒታል መጀመር የብዙ ሰው ችግር ብዙ ብር ስላለው ብቻ በርካታ ገንዘብ በማውጣት ንግድ ይጀምራል፡፡በጣም ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ማንኛውም ቢዝነስ ሲጀመር በትንሽ ተጀምሮ ነው ቀስ እያለ ማደግ ያለበት፡፡ለምሳሌ 100 ሺህ ብር ቢኖርህ በ50 ሺህ ጀምረህ ቀሪውን ለባክ አፕ አቆየው፡፡ ለምሳሌ ብትከስር፡ንግድህ አደጋ ቢያጋጥመው፡ንግዱን ባትችልበት ፡ሌሎች እቃዎችን ቀስ እያልክ መጨመር ብትፈልግ የግድ ያስቀረኸው ገንዘብ መኖር አለበት፡፡ምናልባትም ስለማታውቅ ነው እንጅ ሙሉ በሙሉ ባላቸው ገንዘብ ምንም ሳያስቀሩ ንግድ የጀመሩ ሰዎች አብዛኛዎቹ ከስረው ከገበያ ወዲያው ይወጣሉ፡፡ስለዚህ በትንሽ ጀምረህ ንግዱ ሚያዋጣ ከሆነ ቀስ እያልክ እየጨመርክ ትሄዳለህ፡፡ ስለዚህ ንግድህ እንዳይከስር በትንሽ ጀምር፡ተፎካካሪዎችን ሁልጊዜም አጥናቸው፡እቅድ ይኑርህ፡ከመጀመርህ በፊት ገበያውን በደምብ አጥናው፡፡ በል ፎሎው አድርግ
AhmedTech
Region: ET
Monday 29 June 2026 09:09:28 GMT
Music
Download
Comments
Learn :
🥰🥰🥰🥰
2026-06-29 10:59:48
0
Jo ❤ :
🥰🥰🥰
2026-06-29 10:09:33
0
Siraaj Hashim Mohammad :
🥰🥰🥰
2026-06-29 12:56:07
0
To see more videos from user @ahmedtech257, please go to the Tikwm
homepage.