@amharicliterature: ፍቅር መጨረሻ አንቺ ከፍ ብለሽ ቀና ብዬ ሳይሽ ያመኛል አንገቴን አዘቅዝቄ ልዪሽ አውቃለሁ አትችይም አንቺም ማለት ቀና እኔን ዝቅዝቅ ማየት ታልሚያለሽና ጎረቤቶቻችን አይወዱም ግልፅ ነው እኛ ከፍ ብለን ሊያዩን ቀና ብለው እኛም አንወድም ለቅፅበት ለአንዳፍታ ቀና ብሎ ማየት የእነሱን ከፍታ ማንም ቀና እንዳይል እንዳይዝል አንገቱ ማንም እንዳይወጣ ከዝቅጠት ኡደቱ አንዱ አልፎለት ሌላው እንዳይግል ቅናቱ እንዳይናጋብን ማጣት አንድነቱ አንድ ላይ እንነስ ባንዴ እንስነፍና አብረን እንቁርቁዝ አብረን እንተኛና። ከዛሬ ጀምሮ ቃል ገባሁኝ ግቢ ዘመድ አዝማድ ልጥራ ጎረቤት ሰብስቢ ሁላችን በአንድነት ሆነን በጉባኤ ከዚህ ድንበር ላናልፍ እንግባ ሱባኤ። ተስፋ ያደረገ ተስፋው እንዲጠፋ ፈጥኖ የተራመደ ተፋጥኖ እንዲደፋ አንዳችን ለአንዳችን ጠባቂ ሆነነው አብረን እንቀመጥ እንዲሁ እንዳለንው። የአብሮ መኖራችን ዋናው መሰረቱ ከፍ ዝቅ አይልም እኩል ነው ፍጥረቱ መወዘት ይሻላል ፊት ለፊት ተፋጦ እንዳንረባበሽ አንዱ ከአንዱ በልጦ ታዲያ እንዴት ይደረግ? ምንድነው ብልሃቱ? ፍቅርን ለመጨረስ ይህ ነው አብነቱ። ጁላይ 29፣ 1996 ፓሪስ - ተፈሪ አለሙ (ፍቅርና ክብር) #የአማርኛ_ቋንቋና_ሥነጽሑፍ #አማርኛ #amharic #literature #poem የቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ https://t.me/amharic_language_and_literature የቲክቶክ ገጻችንን ይከታተሉ tiktok.com/@amharicliterature

የአማርኛ ቋንቋና ሥነጽሑፍ
የአማርኛ ቋንቋና ሥነጽሑፍ
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 01 July 2026 04:13:48 GMT
3171
171
4
25

Music

Download

Comments

user73755465042696
የትምወርቅ :
2026-07-02 17:15:56
0
babadriv14
babadriv14 :
🥰🥰🥰
2026-07-01 17:29:58
0
user106816615631
user106816615631 :
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-07-01 08:41:39
0
sami__girma
samig :
❤️❤️❤️
2026-07-01 19:41:01
0
To see more videos from user @amharicliterature, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About