@amharaprosperityparty: ዕዳን ወደ ምንዳ ያሸጋገረ ሰብዓዊ ልዕልና ‼ ፓርቲያችን ብልጽግና ለሰው ተኮር ተግባር እና ለሰብአዊ ልዕልና ያለው እምነት የማይናወጥ ነው፡፡ የፓርቲው የሰብአዊ ልዕልናን የማረጋገጥ ህልምም የሕዝብን የተረጋጋ እና ደስተኛ ሕይወት መፍጠር የሚያስችል ሰብአዊ ዐቅምን በማዳበር ላይ የተመሠረተ ነው። ድህነት እና ኋላቀርነት ሃገራችን ኢትዮጵያ ዕምቅ ሀብቶቿን አውጥታ የሕዝቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደኅንነት ማረጋገጥ እንዳትችል ነጻነታችንን ገፎ፣ የገዘፈ ታሪካችንን አኮስሶ፣ ለጥገኝነት ያጋለጠን ቁልፍ ሀገራዊ ችግር ነው። የሕዝብን መሠረታዊ (የመብላት፣ የመልበስ እና የመጠለያ) ፍላጎት የሚያሟላ አልነበረም። ይህም በድህነት ውስጥ የሚኖሩ፤ የሌሎችን እጅና ምፅዋት የሚጠብቁ ዜጎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል። ይሁን እንጂ ፓርቲያችን ብልጽግና ችግሩን ለመቅረፍ በወሰዳቸው ሰው ተኮር የለውጥ እርምጃዎች በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ በመፍጠር የበርካቶችን ህይወት እየለወጠ ነው። የክረምት በጎ ፈቃድ ንቅናቄ በአሁኑ ሰዓት ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሸጋገረ እና ሚሊዮኖችን በማስተባበር የዜጎችን ህይወት በመለወጥ ላይ ይገኛል። ይህ በጎ እንቅስቃሴ፣ ኢትዮጵያውያን በመተባበር እና በመረዳዳት ባህላቸው ላይ ተመስርተው የጋራ ችግሮቻቸውን በጋራ መፍታት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ ነው። በአማራ ክልልም በየዓመቱ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ በርካታ ሰው ተኮር ስራዎች እየተተገበረ ይገኛል። ለዚህ አብነትም በምስሉ እንደምንመለከተው በባህርዳር ከተማ የአረጋውያንን እና ዐቅመ ደካሞችን ቤት መልሶ በመገንባት በተጎሳቆለ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ህይወት የለወጠ፤ ከዕዳ ወደ ምንዳ የተሻገረ ሰብዓዊ ልዕልናን በተግባር ያረጋገጠ ድንቅ ስራ ተመልክተናል። ከጉስቁልና ወደ ልዕልና የሚያሻጋግር፣ ይህንን መሠል አርዓያነት በመከተልም መላ ህዝቡ ጉልበቱን፣ ጊዜውን እና እውቀቱን ለበጎ አድራጎት ስራ በስፋት እየሰጠ ይገኛል፤ ተጠናክሮ ሊቀጥልም ይገባል። 🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊 #amharaprosperityparty
Amhara Prosperity Party / APP
Region: ET
Wednesday 01 July 2026 08:32:17 GMT
Music
Download
Comments
Visit Ethiopia 🇪🇹 :
🥰🥰🥰
2026-07-01 09:02:57
0
hailie mengesha :
🌟🌟🌟
2026-07-01 13:25:56
0
To see more videos from user @amharaprosperityparty, please go to the Tikwm
homepage.