@tkursewmedia444: እንዴት ብየ እንደማስረዳችሁ አላውቅም። የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የሚሊኒየም ተማሪዎች ታውቁታላችሁ። የግቢው 2ኛ ባች ተማሪ ነበርን። ከኔ ጋር 3 አመት አንድ ክፍል ተምረናል። ከክፍላችንም ከዲፓርትመንታችንም ቶፕ ስኮረሮች አንዱ ነበር። በጣም ፈጣንና ተግባቢ ልጅ ነበር። ከተመረቅን በኋላ ኮሌጅና 2ኛ ደረጃ ት/ ቤቶች ላይ እያስተማረ መሆኑን በተባራሪ መረጃ መስማቴን አስታውሳለሁ። ከአመት በፊት አአ መርካቶ አካባቢ ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ያደረጉ ወገኖችን የመመገብ ፕሮግራም ላይ በድንገት አየሁት። ደነገጥኩ። መመሳሰል እንጂ እሱ አይሆንም ብየ ራሴን ተጠራጠርኩ። ግን እርግጠኛ መሆን ፈለኩኝ። ድንኳን ስራው ላይ በተለመደ ቅልጥፍና ይሳተፋል። አለባበሱና አካላዊ ሁኔታው ግን ተጎሳቁሏል። ይቅርታ ጠይቄ ጠራሁት። ጠየኩትም። አስሜ ደና ነሽ ? አልኩኝ። እንደ ልጅነታችን ምንም የተለየ ነገር እንዳልተሰማኝ ሆኘ። አስታወሰኝ። አይኑን ሰበር እያደረገ ግን ያ ፈገግታውን እያሳየኝ ሁሴና ብሎ የቀድሞ የክፍል ጓደኛየ ጠራኝ። አቅፌ ሰላም አልኩት። ብዙ ላቆየው አልፈለኩም። ምን እየሰራ እንደሆነ ጠየኩት። የሆነ በጎ አድራጎት ላይ አለኝ። በጣም ጥሩ ነው አስሜ በርቺ በቃ ፣ እሁድ እሁድ ጠዋት ጃሊያ ት/ቤት ውስጥ ስፖርት ስለምመጣ እንገናኛለን ብየ ተለያየን። ያለበትን ዝርዝር መናገር ስላልፈለገ ነው አለመጠየቄ። ከዚያ በኋላ አላየሁትም። ባለፈው ሳምንት የማላውቀው ቁጥር ተደወለ። ሁሴና ደና ነሽ ? የሚል የደከመ ድምጽ። አስሜ ነኝ። አስሜ. ... ስል ሚዛን ቴፒ። ስልክሽ ጠፍቶች እናንተ ቢሮ አካባቢ ሂጀ ተቀብየ ነው። በሰላም ነው የጠፋሽው ? ሁሴና ከባድ ችግር ውስጥ ገብቻለሁ። ታምሜ አማኑኤል ገብቸ ነበር። አሁን እግዚያብሄር ይመስገን ጤናየ ተመልሷል። ግን ያለሁት ጎዳና ላይ ነው። የምለብሰው ፣ የምቀምሰው የለኝም አለኝ። ደንግጫለሁ ፣ አዝኛለሁ። ግን ጉብዝናውን አስታውሸ አበረታሁትና በአካል እንድንገናኝ ጠየኩት። ስልክ ስለሌለው ቋሚ አድራሻው አዲሱ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በታችኛው በኩል ነኝ አለኝ። ወዲያው አንድ ክፍል ከተማርናቸው ወንድሞች ኸይረዲ እና ጌትነት ጋ ደወልኩ። በአካል አግኘውና እናውራበት የሚል አወንታዊ መልስ ሰጡኝ። እናም ትላንት ማክሰኞ ተገናኘን። ያሳለፈውን መከራ ሁሉ እያነባ ተረከልኝ። ወይኔ አቅም ማጣት ! ብቻ አንድ ወንድሜ ጋ ደውየ ወደ ስራ የሚመለስበትን አጋጣሚ እንደሚፈልግና እንደሚያግዘው ልብ የሚያሞቅ መልስ ሰጠኝ። ወንድም በየ ቦያው ይኑር አቦ። ከዚያ አስሜ ካለበት ስሜት እንዲወጣ የድሮ ትዝታዎችን እያነሳን እንባችን እስኪወርድ ስንስቅ ስንጫወት ቆይተን ተለያየን። ያላነሳነው ተማሪና መምህር አልነበረም።ሳቁን ስላየሁ ፣ ተስፋውን ስለሰማሁ ተደስቻለሁ። ስንለያይ ግን ከባድ ነበር። የሚደግፈኝ ምርኩዝ ካገኘሁ እነሳለሁ አለኝ። ለጊዜው ግን ጎዳና ላይ ክረምቱን አልቻልኩትም ፣ ልብስ ፣ ጉርስ ተቸግሬያለሁና እገዛ እፈልጋለሁ ለምታውቃቸው ሁሉ ንገርልኝ ብሎኝ ይቺን ፎቶ አነሳሁት። ፎቶ ላይ ኮስተር ስትል ፈገግ በያ እያልኩ አሳኳት። አስማማው ጌትነት የጎጃም ቡሬ ልጅ ነው። ሌላው ከባድ ነገርና ህይወቱን ያመሰቃቀለው እናትና አባቱ በእርስ በርስ ጦርነት ሂደት ውስጥ መገደላቸውን ነግሮኛል። አግብቶም አንድ ልጅ እንደወለደና ከሚስቱም ከልጁም እንደተላያየ አውርቶኛል። መረጃዎቹ ያሏችሁ ማረጋገጫም ብትሰጡን። ሚዛን ቴፒ የተማራችሁ ያስተማራችሁ ፣ የምታውቁትና ያዘናችሁለት ሁሉ ወንድማችንን ወደሚገባው ቦታ እንመልሰው። መምህርነትን ይወዳል ፣ በብቃትም ያስተምራል። ©Hussein Gizaw
ጥቁር ሰው ሚዲያ Tkursew
Region: ET
Wednesday 01 July 2026 13:33:17 GMT
Music
Download
Comments
Eagle :
እግዚአብሔር ይርዳው ሁሉን ቻዩ አምላክ
2026-07-02 00:58:44
7
anwar :
2026-07-01 23:08:40
3
Carlos :
I am sorry t9 hear this.
2026-07-01 18:14:37
2
ברקת אספאו🇨🇬🇮🇱 :
ዋናዉ ጤና👌
2026-07-02 13:38:22
0
Garasuu Bachoo :
ተባረክ
2026-07-02 13:11:28
0
han :
አይዞን
2026-07-02 10:55:22
0
Beki_21 :
Egziabher yirdaw🙏🙏🙏
2026-07-02 10:02:35
0
መብራት :
አይዞን እድልህን ይክፈት ልህ በርታልኝ አዓለም ፍታው አይድልችም ❤️
2026-07-02 09:04:59
0
pass at life :
ፈጣሪ ይርዳህ አይዞን ወንድሜ
2026-07-01 18:39:30
1
biniyam ethiopia :
አይዞህ ወንድሜ የማያልፍ የለም
2026-07-01 22:02:32
1
zelalem tsehay :
ቸባረክ
2026-07-02 09:00:04
0
Abreham :
Account
2026-07-01 23:25:13
0
user5298150881758 :
አይዝህ
2026-07-01 21:08:00
1
Zzeweekend :
እሽ
2026-07-01 18:54:05
0
anwar :
2026-07-01 23:08:45
2
Carlos :
am sorry to hear this he was very intelligent
2026-07-01 18:14:55
2
Ashu :
ቴፒ ካምፓስ 2000-2002 ነበርኩ
2026-07-02 03:10:28
0
Deme :
አይዞህ ወንድሜ
2026-07-01 19:34:51
0
Mahamed Husen :
በምድር መኖር ከበደበቃ
አሳዛኝ ታሪክነው
2026-07-01 15:07:31
9
heni man :
አይ ሠው መሆን ከባድ ነው ወንድሜ አይዞንንን
2026-07-02 04:58:19
1
Healthy leaf 🍃 :
errr wegen enrdawe ayeozhe becha bezhe zemen ayeseram copy paste please 🙏
2026-07-02 04:34:01
1
ድጋፌነህ :
ማን ተማር አለው
2026-07-02 09:47:31
0
forever :
ዓለም እንዲህ ናት
2026-07-02 11:25:37
0
Biruk Alemayehu :
እግዚአብሔር ታሪክህን ይቀይረው
2026-07-02 11:33:50
0
ebba :
i know him and you too. i am so sad to see him in a such disturbing condition.😳😳
2026-07-01 18:40:13
1
To see more videos from user @tkursewmedia444, please go to the Tikwm
homepage.