@makda_16: አንድ ምሽት ከአያቴ ጋር በረንዳ ላይ ተቀምጠን ፀሐይዋ እየጠለቀች ነበር አያቴም ወደ ምትጠልቀው ፀሀይ አሻግራ እየተመለከተች በተረጋጋ ድምፅ እንዲህ አለችኝ… “ልጄ በህይወትሽ የምታገኛቸው ሰዎች ሁሉ አንድ አይደሉም አንዳንዶች ትምህርት ይሆኑሻል ፤ አንዳንዶች ደግሞ በረከት!! ችግሩ ግን ብዙ ጊዜ በረከታችንን እንደ ተለመደ ነገር እንቆጥረዋለን።” እኛ ሰዎች ንፁህ ልብ ስናገኝ እንደዋዛ እንለምደዋለን ያ ደግሞ ትልቁ ስህተታችን ነው ! እኔም ገርሞኝ “ለምን አያቴ?”ብዬ ጠየቅዃት እርሳም ፈገግ አለችና… “ምክንያቱም ንፁህ ልብ ያለው ሰው ሲወድሽ ከልቡ ነው ደህና መሆንሽን ሲጠይቅሽ ስለሚጠቅመው አይደለም ስለሚያስብልሽ ነው ፤ ሲጸልይልሽ እንድታውቂለት ሳይሆን እግዚአብሔር እንዲረዳሽ ነው፤ በስኬትሽ ሲደሰትልሽ ሳይቀናብሽ ነው። ምክንያቱም ንፁህ ልብ ያለው ሰው ሁልጊዜ ይቅር ይላል፣ ይረዳል፣ ይታገሳል። ከዚያም እኛን መሰል ሞኞች ‘እሱ እኮ እንደዛ ነው’ ብለን መልካምነቱን እንደ ግዴታ እንቆጥረዋለን። we stop appreciating what should have been protected.” እንደዚህ ያሉ ሰዎች በብዛት አይገኙም ንፁህ ልብ ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን አያስተዋውቁም በድምፃቸው ሳይሆን በተግባራቸው ይታወቃሉ። ስትወድቂ መጀመሪያ የሚደርሱት እነሱ ናቸው፤ ሲሳካልሽ ከልባቸው የሚደሰቱልሽም እነሱ ናቸው ስትሳሳቺ ለማሸማቀቅ ሳይሆን ለማቅናት የሚቀርቡሽም እነሱ ናቸው። ግን ልጄ… እኔን መሰል ሰዎች አንድ ትልቅ ስህተት እንሰራለን ሁልጊዜ የሚገኙልንን ሰዎች ለመልመድ እና እንደ ቀላል ለመቁጠር እንቸኩላለን ፤ዋጋቸውን ለመረዳት ግን እንዘገያለን!! Then she looked at me with tears in her eyes🥹and said “ ልጄ ንፁህ ልብ ያለውን ሰው ማግኘት ዕድል ነው፣ዋጋውን ማወቅ ደግሞ ጥበብ ነው። አንዳንዴ አበባ ሲደርቅ ውኃ ማጠጣት አይጠቅምም!! ሰላም የሚሰጥሽን ሰው ካገኘሽ እንደ ተለመደ እና ቀላል ነገር አትውሰጂው ምክንያቱም አንዳንድ በረከቶች አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚሰጡሽ።”❤️🩹
እጹብድንቅ
Region: ET
Thursday 02 July 2026 09:11:29 GMT
Music
Download
Comments
hilina etet :
endeza aynet lb yalachew betsebochhsh bcha nacheww🙏😍
2026-07-03 08:43:12
3
Sara :
Ewnet new 🥹❤️🩹
2026-07-02 12:12:57
0
betelhem :
ewenet new 👌🥰
2026-07-02 11:12:58
1
Hawi ze16🤍🦋 :
በረከቴ❤️
2026-07-03 04:06:24
0
𝗧𝗲𝘀𝘂 𝗹𝗮𝗹𝗮 :
damn
2026-07-05 22:26:22
0
misganw16 :
🙏
2026-07-06 06:22:18
0
Selam Kassaye :
የኔ ልቤ ንፁህ 🥰🥰🥰
2026-07-02 14:16:57
0
yabu_ye16 :
🥰
2026-07-02 19:24:53
0
Bez🌸 :
👍😥😍
2026-07-02 09:19:11
0
ጽዮናዊት✝️ :
🙏
2026-07-02 19:10:21
0
kidisteYemikael :
🤌
2026-07-02 13:29:54
1
AyanPkzQ :
🗨
2026-07-11 22:46:03
0
E Y U E L ࿇ :
.
2026-07-04 02:02:35
2
To see more videos from user @makda_16, please go to the Tikwm
homepage.