@gurshapaje: በትግራይ ወጣቶች እየታፈሱ መሆኑ ተሰማ በትግራይ ክልል ወጣቶች ላይ እየተፈጸመ ስላለው እፈሳ በርካታ የጉርሻ ፔጅ ተከታታዮች በከፍተኛ ስጋት ጥቆማዎችን እያጋሩን ይገኛል። ጉርሻ ፔጅ ነገሩን ይበልጥ ለማጣራት ባደረገው ቆይታ፣ ከትምህርት ቤት እየተመለሱ ያሉ ወጣቶች በኃይል እየተወሰዱ መሆናቸውን ስማቸውን መግለጽ የማይፈልጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልናል። ዛሬ በመቀሌ ቀበሌ 06 ከትምህርት ቤት አካባቢ በተቀረጸና ለእኛ በደረሰን የቪዲዮ ማስረጃ ላይ እናቶች መሬት እያመቱ በከፍተኛ ጩኸትና ኃዘን ሲያለቅሱ ይታያል። ጉርሻ ፔጅ ከድሮም ጀምሮ በእርስ በእርስ ጦርነት የማያምን፣ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በተካሄደው ጦርነት ላይ እጁን ያላስገባ ሰላማዊ መድረክ መሆኑ ይታወቃል። የትግራይ ወጣቶች እንደማንኛውም ክልል ያሉ ወጣቶች የመስራት፣ የመለወጥና የማደግ ትልቅ እሳቤና ህልም ያላቸው በመሆኑ ይህ የወደፊት ተስፋቸው ሊቀጭ አይገባም ብለን እናምናለን። ስለሆነም የሚመለከተው የክልሉ አካልም ሆነ የፌዴራል መንግስቱ ይህንን ነገር በአስቸኳይ እንዲያስቆመው በትህትና እንጠይቃለን። ጠግበህ በልተህ እንኳን የበላህ የማይመስላት የትግራይ እናት አደይ አሁን ማልቀስ የለባትም። ቪዲዮው የጉርሻ ቲጂ ላይ አለ አሁን በረሃብና በልጅ መጥፋት ስቃይ ልቧ ሊሰበር አይገባም፤ ሰላምና እረፍት ያስፈልጋታል። ጉርሻ Page 🌴🌴🌴 https://www.facebook.com/share/p/18ATfTbT1q/?mibextid=wwXIfr

ጉርሻ
ጉርሻ
Open In TikTok:
Region: AE
Friday 03 July 2026 11:09:10 GMT
2645
76
4
13

Music

Download

Comments

selam.abuhay4
selam abuhay :
🥺🥺🥺
2026-07-03 12:50:29
0
bdejed
Helmona ❤️ :
🥺🥺🥺🥺🥺🥺💔💔💔💔💔
2026-07-03 12:59:36
0
To see more videos from user @gurshapaje, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About