@santa_tad: የፍየል ግልገል እና የነብር ግልገል ጫካ ውስጥ ተገናኝተው ምንም ሳይጠራጠሩ፣ በፍቅር አብረው ውለው ወደየቤታቸው ተመለሱ። ... ቤት ሲገቡ ግን እናቶቻቸው ተቀበሏቸው፡ ስለውዎቻቸው ሲጠይቁ ፥ የነብር እናት "ያ የተጫወትከው ፍየል ይባላል፣ ምግባችን ነው፤ ለምን አልበላኸውም?" አለችው ልጇ። የፍየል እናት ደግሞ "ልጄ፣ ያ ዥንጉርጉሩማ ነብር ይባላል፣ ይበላናል! ለዛሬ ተርፈሃል" ስትል አስጠነቀቀችው። .. በማግስቱ እንደገና ተገናኙ። የነብር ግልገል እናቱ የነገረቻትን አስባ "ና እስኪ እንጫወት፣ እቀፈኝ" ስትለው፣ የፍየል ግልገል ግን ቀድማ ነቅታ ነበር። ራቅ ብላ ቆማ እንዲህ አለችው፡ "አንቺም እናትሽ ነግራሻል፣ እኔም እናቴ ነግራኛለች! ከእንግዲህ መጫወት የለም!" ... ፍርሃትና ጥላቻ አብረውኝ አይወለዱም፤ ከሰዎች የምንማራቸው እንጂ። ስንወለድ ነፃ ነበርን፤ ያለምንም ጥላቻ፣ ፍርሃትና ልዩነት የምንኖር ነበርን። ... ደግሞም አለም የሁለት ሀይል ማዕከል እንደመሆኗ ተኩላ አይጠፋምና እንደ ፍየሏ ግልገል የሰዎችን ተንኮል ቀድሞ ነቅቶ መራቅና ራስን መጠበቅ አስፈላጊም ነው።

Sintu/ የእኔ እይታ.
Sintu/ የእኔ እይታ.
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 04 July 2026 06:56:20 GMT
3590
146
3
18

Music

Download

Comments

geche.mane7
aso aso አሶሳ :
ሲገርም እውነት ነው ❤️❤️❤️
2026-07-04 14:24:24
2
mengeshamaru
mengeshamaru :
Amazing points raising bro.continue
2026-07-04 15:05:05
2
estifness
estif :
iwwunett ikkoo new wooww🥰🥰🥰🥰 wendime
2026-07-04 20:38:09
0
To see more videos from user @santa_tad, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About