@chenchazukowebetekihnet: ✥መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ✥ እንኳን ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል አደረሰን፣አደረሳችሁ! ※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※ ቅዱስ ዮሐንስ ነቢያት፣ ቅዱስ ገብርኤልና አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት፣ ከሕፃንነቱ ጀምሮ ቅኑት እንደ ገበሬ፣ ጽሙድ እንደ በሬ ኾኖ እግዚአብሔርን ያገለገለ፣ ዓለምን የናቀ፣ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ የኾነውን ሰኔ ፴ ቀን ተወለደ፡፡ ዮሐንስ ማለት “እግዚአብሔር ጸጋ ነው” ማለት ነው፡፡ ትርጓሜ ወንጌልም መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን “ፍሥሐ ወሐሴት” (ተድላና ደስታ) ይለዋል፤ ወላጆቹ በእርሱ መወለድ ተደስተዋልና /ሉቃ.፩፥፲፬/ ※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※ ስንክሳር ዘወርኃ ሰኔ - ፴ - ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው ። ይህም በመድኃን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው ። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች ። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለእርሷ ደስ አላቸው ። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት ። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባላል አለች ። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት ። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት ። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባላል ብሎ ጻፈ ። ሁሉም አደነቁ ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው ። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሄድ ትንቢት ተናገረ ። ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንደሚገድሉትም ጭፍሮቹን ላከ ጭፍሮቹም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋር እንዲሔድና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው ። ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው መርኅ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው ። ጭፍሮቹም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት ። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ ። የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው ። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ ። በፊትህ ጐዳናህን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ ። ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር ከሴቶች ከተወለዱት መጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጠው የለም ብሏል ። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማንጻቱን ራሱን በዳሰሰው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና ። ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመንን መታሰቢያውን እናድርግ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※ የጨንቻ ዙሪያና ቆጎታ ወረዳዎች ቤተክህነት ሚዲያ
የጨንቻ ዙሪያ ቆጎታ ወረዳዎች ቤተ ክህነት ሚዲያ
Region: ET
Monday 06 July 2026 16:28:13 GMT
Music
Download
Comments
Eyob Getu :
yene abat
2026-07-07 04:53:41
0
ሰላሜ ባንቴ ነው የኔ ጌታ ❤️❤️💒❤️ :
❤️❤️❤️❤️
2026-07-07 11:34:16
0
Abel :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-07 04:51:06
0
አፍቅሮ ከመሮጥ ሰርቶ መለወጥ :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-07-07 03:44:13
0
mulune gudata abara :
🥰🥰🥰
2026-07-07 02:39:12
0
Bereket Bergene :
❤️❤️❤️
2026-07-07 20:17:20
0
To see more videos from user @chenchazukowebetekihnet, please go to the Tikwm
homepage.