@musictube369: ይሰማሽ 😑 ✍️..ያኔ ልጆች እያለን ሙዚቃ እንዲህ እንዳሁኑ ሳይበላሽ(better to say ሳይሞት) የሙዚቃ ፈርጦች የተነሱበት ወይም የደመቁበት፤ ትዝታን በህሊናችን ፍቅርን በልባችን አትመው ያኖሩበት ዘመን ነበር፤ 1990ዎቹ። በጊዜው የተሰሩት ሙዚቃዎች እንደዛሬ ዘመን ሙዚቃ ትናንት ተደምጠው ዛሬ የሚሰለቹ፤ ይሄን ሙዚቃ ማልሰማበት ቦታ የት ይሆን የማንላቸው፤ ብንደግማቸው ብንደጋግማቸው የማይሰቹን ናቸው። ምክንያቱም ላይረሱን በልጅነታችን ታትመው ልባችን በትዝታና በፍቅር ይወሰውሱታል እንጂ በ_ፍ_ፁ_ም!! አይሰለቹም👌 እኔም እነዚህን ሙዚቃዎች እንደመስማት የሚያስደስተኝ ነገር የለም። መንገድ ላይ ሳልፍ ብሰማቸው ቆም ብዬ አዳምጣቸዋለሁ፤ ከቸኮልኩም ከጀመረበት አንስቼ በልቤ ወይ በድምፄ እየዘፈንኩት እሄዳለሁ🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ታዲያ በ1990ዎቹ አጋማሽ ላይ ከታዩ ድምጻዊያን መካከል አንዱ ነው፡፡ ግጥም እና ዜማ ደራሲም ነው ፡፡ ከራሱ ባሻገር ለተለያዩ ድምጻዊያን ግጥም ና ዜማ ሰጥቷል የራሱን ህይወት የመሰሉ ውብ ሙዚቃዎችን በህንድ ከለር ተቀምምመው የተዋቡ አዲስ ይዘት የተላበሱ ተወዳጅ ስራዎችን ድንቅ አልበም አድርሶናል ወደ ዘጠናዎቹን ከሚመልሱን እጅግ ተወዳጅ ድምፃውያን አንዱ ነው ብዙ የህይወት ውጣ ውረዶችን በፅናት እና በትዕግስት የተሻገር ብርቱ ነው ድምጻዊ የዜማና የግጥም ደራሲ ጌታሁን ምተኩ (ጌቱ ኦማሂሬ)🙌🥰 📌በ90ዎቹ ተማሪ የነበሩ ልጆች ያሳለፉትን ገራሚና አይረሴ ገጠመኞችን ወደ ኋላ ሄደው እያወሱን ብዙዎቻችንን ትዝታ ላይ ይጥሉናል። ዛሬም አንድ ፈቀደ አማን የሚባል ወዳጄ ያን አይረሴ ጊዜ አስታወሰኝ። እንዴት ደግ ጊዜ ነበር ጃል? እናማ ይህው እኔም ያን ጊዜ መለስ ብዬ የዘጠናዎቹን የሙዚቃ ስራዎች ዛሬ ከተቀመጡበት በርብሬ በማውጣት ላስታውስ ወደድኩ፡፡ ያኔ ሙዚቃ በየቤቱ ፣ በየታክሲው ፣ በካፌው ፣ በየሆቴል ቤቱ ፣ በየበርጫ ቦታ በፍቅር ይደመጥ ነበር። አንጋፋው ሀይሉ ሙዚቃ ቤት ፣ የጋሽ ስታየሁ S.S እንዲሁም Al-Amir ሙዚቃ ቤት ዝነኛና ፈር ቀዳጆቹ ናቸው። ያኔ ያልተደመጠ ሙዚቃ የለም የዘጠናዎቹ ፈርጦች ምርጥ ድምፃዊያንን በሲዲ ገዝቶ አልያም ተውሶ ያልኮመኮመ ያለ አይመስለኝም። የቴዲ አፍሮን አቦጊዳን ዘፈን በፍቅር ያላደመጠ ፣ የጎሳዬ ተስፋዬን ቃል በቃል አብሮ "ያኔ ልጅ እያለን ሆነሽ ጎረቤቴ" እያለ ያልዘፈነ ፣ በአስቱካ ጣፋጭ ሙዚቃ በፍቅር ያልወደቀ ፣ በድምፀ መረዋው በማዲንጎ አፈወርቅ ያልተመሰጠ የ90ቹ ትውልድ የለም፡፡ በዘጠናዎቹ ተደምጠው የማይጠገቡ ተሰምተው የማይሰለቹ እንደ ወይን ጠጅ እያደሩ የሚጣፍጡ ፈፅመው የማይሰለቹ ጥዑም ዜማዎችን አበርክተውልናል ፡፡ የተወሰኑትን እንኳን የኋሊት በትዝታ ሄደን ብንቃኝ ያኔ እንደጉድ የተደመጠ፣ ከጫፍ ጫፍ የተሰሙና የተወደዱ ወደር የማይገኝላቸው አሁንም አመታትን አልፎ ስንሰማቸው እንደ አዲስ ይሆኑብናል፡፡ በአጠቃላይ ሁላችሁም የ 90ዎቹ ዘፋኞች ስለሰጣችሁን ለማይረሱና ዘመን ተሻጋሪ ጥዑም ዜማዎች በእጅጉ እናመሰግናችኋለን የትዝታችንና የታሪካችን ክፍል ናችሁና በፍፁም ልንረሳችሁም አንችልም፡፡ ........🙌🙏 📌እስኪ የምናስታውሳቸው የሙዚቃ መሀል እንደ ሰበዝ ከትውስታው መሀደር እንምዘዝና እናስታውስ.... .ቴዲ አፍሮ ( አቦጊዳ ) .ጎሳዬ ተስፋዬ ( ኢቫንጋዲ) .ቻቺ ታደሰ ( ኧረ ሸጋው ስምህ ማነው) .ታምራት ደስታ ( አንለያይም ) .ጥበቡ ወርቅዬ (አላማርርም) .ብስራት ጋረደው (ሳላምንበት) .ኤርሚያስ (ልረሳሽ አልቻልኩም ) .አስቴር አወቀ (ስኳር ስኳር ) .ፅደንያ ገ/ማርቆስ ( ቢሰጠኝ ) .አብዱ ኪያር ( መርካቶ ሰፈሬ ) .Hada haile ( i found the way ) .ይርዳው ጤና(አልገለጥ አለኝ ተጋርዶ ሰፈሯ) .ሀይማኖት ግርማ (ኦማሂሬ) .ትግስት በቀለ ( በደራው ከተማ ሞቅ ሞቅ ባለው) .ጌቱ (ኦማሂሬ) .አብርሽ ዘጌት ( እድሜዬን በሙሉ ስፈልግሽ ኖሬ ) .ቴዎድሮስ ሞሲሳ ( የጎረቤት ልጅ ወድጄ በአይኔ ) .ሄኖክ አበበ ( ለሰው አይታይም ለኔ ግን ይታያል ) .ዳዊት መለሰ ( ላክዳሽ ቃላ አለኝ ) .አበባና ትግስት ( እርጂኝ አብሮ አደጌ) .እየሩሳሌም(ጄሪ) ሀሎ አዲስ አበባ አዱ ገነት .ሳሳሁልሽ በረጋ ( እንዳልመጣ አድራሻህ ጠፍቶኝ ነው) .ጆኒ ራጋ (ቁልፉን ስጭኝ) .ታደለ ሮባና ብርሃኑ ተዘራ(ላፎንቴን) .መስፍን በቀለ ( ለምን በሷ ላይ ጣለኝ ) .ትግስት ወይሶ ( ቆጨኝ ) .ጌድዬን ዳንኤል ( ላፅናናሽ አቅሜ እንደሚችለው) .ወንድሙ ጀራ ( የኔ ጉዳይ) .ኒኒ ኧረ ስንቱ ተዘርዝሮ ይቻላል በሽ ናቸው.... ...ታዲያ እኔም ዛሬ ወደኋላ መለስ ብዬ ያንን ውብ ዘመን ከሚያስታውሱ ድንቅ አልበሞች መሐል አንዱ ከሆነው የጌቱ ኦማሂሬ 'እንደ ማቱሳላ' አልበም 'ይሰማሽ'ን ጋብዤያቹ አበቃሁ🙏😎 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #fyp #ጌቱኦማሂሬ #ይሰማሽ #ethiopianmusic #musictube369

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 06 July 2026 19:44:24 GMT
66708
4976
24
416

Music

Download

Comments

mekedsyhun
mekedsyhun :
2026-07-07 07:27:21
1
fikirtesirak
Fikirtesirak :
Gech🥰
2026-07-07 19:54:20
0
mamespecial1
mame awol :
ኤልያስ መልካና ዳግማዊ አሊ🙏🙏
2026-07-07 18:29:27
0
k_rise0
K_Rise :
ቀነን እንዳሳመርክልኝ ህይወትህ ይመር አቦ👏🥰
2026-07-07 11:21:46
1
king.19752
king 19 :
gatu
2026-07-07 12:47:19
1
kotolakassu
kotolakassu :
❣️❣️❣️
2026-07-07 15:51:24
1
bruk4932
Bruk### :
🥰🥰🥰
2026-07-07 15:46:55
1
abejenigussie645
Abeje Nigussie :
♥️♥️♥️
2026-07-07 10:59:58
1
tigi15082
Tigi :
❤️❤️❤️
2026-07-07 13:47:46
1
mamme.ertale
@Mamme Erta Ale🔥🔥 :
💞💞💞
2026-07-07 09:08:57
1
ermiyas_t
Ermiyas_t :
🥰🥰🥰
2026-07-06 20:31:20
1
user4934085482955
Tigi :
🥰🥰🥰
2026-07-07 05:47:08
1
red_devils____6
aman_man united 🔱 :
🥰🥰🥰
2026-07-06 20:30:55
1
edamm53
edamm53 :
🥰🥰🥰
2026-07-06 20:16:34
1
user8733991725361
Sentu Kasahun :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-07 17:38:33
0
kedirabdu444
ⓚነኝ ተስፈኛዉ444🙏 :
🥰🥰
2026-07-07 17:44:56
0
zedo3038
zedo :
🥰🥰🥰
2026-07-07 20:13:34
0
dagem5174072
dagemTadesse :
❤️❤️❤️
2026-07-07 18:04:52
0
abejenigussie645
Abeje Nigussie :
🥰🥰🥰
2026-07-07 11:00:01
0
moseid112
mosad :
❤️❤️❤️
2026-07-07 19:55:32
0
anu569956
anu :
🥰🥰🥰
2026-07-07 11:57:23
0
hayru.reda
H R 34 :
🥰🥰🥰
2026-07-07 18:56:19
0
aishuamin03
{aishu}♡☆♡🦋 :
❤️❤️❤️
2026-07-07 21:53:23
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About